ለጤና አገልግሎት ዘላቂነት ባለው የህግ ውክልና ዙሪያ ተዘውትረው የሚነሱ ጥያቄዎች
FAQ
ለጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ማለት ምን ማለት ነው?
ለጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ማለት እንደ አጋጣሚ ሆኖ ርሶ በራሶ ላይ ውሳኔ የመወሰን አቅም ባይኖሮት እርሶ ስለሚያገኙት የጤና አገልግሎት ሌላ ውሳኔ ለሚሰጥ ሰው ውክልና የሚሰጡበት ሰነድ ነው፡፡ ይህንን ግለሰብ (የእርሶ ተወካይ) ምን አይነት የህክምና አገልግሎት ማግኘት እንደሚፈልጉ መመሪያ ይሰጠዋል፡፡
ለጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና እንዲኖረኝ ለምን ማሰብ ይኖርብኛል?
ምን አይነት የህክምና አገልግሎት ማግኘት እንደሚፈልጉ እና እንደማይፈልጉ የመወሰን መብት አሎት፡፡ እንዲያገኙ ስለሚያስቡት የጤና አገልግሎት አይነት ልዩ ፍላጎት ካሎት የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና እርሶ በአካልም ሆነ በአእምሮ አለመቻል ለዶክተርዎ ምን እንደሚፈልጉ መግለፅ ቢያቅትዎ እንኳ ፍላጎትዎ እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡
ስለሚያገኙት የጤና አገልግሎት ልዩ ፍላጎት ባይኖሮትም እንኳ፣የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና እርሶ ካልቻሉ አንድ የሚያምኑት ግለሰብ እርሶን ወክሎ የህክምና ውሳኔዎችን እንዲያደርግ ያስችላል፡፡
የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ከሌለኝ ምን ይፈጠራል?
የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ከሌሎት እና ለዶክተርዎ የሚፈልጉትን የህክምና አይነት ለመግለፅ እርሶ በአካልም በአእምሮም ውሳኔ የመስጠት አቅም የሌሎት ደረጃ ላይ ከሆኑ በእርሶ የህክምና አገልግሎት ላይ ውሳኔ ለመስጠት በቅደም ተከተሉ መሰረት የሚከተሉት ግለሰቦች ህግ ፈቃድ ሰጥቷቸዋል፡፡
- በርስዎ በፍርድ ቤት የተሾመ ሞግዚት ወይም ጠባቂ
- የህግ ባለቤትዎ ወይም አብረው የሚኖሩት አጋርዎ
- ትልቅ ልጅዎ
- ትልቅ ወንድም ወይም እህትዎ
- የቅርብ ጓደኛዎ ወይም
- ለርሶ ቅርብ የሆነ ጎረቤትዎ
የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና እንዴት ይሰራል?
የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ለመስጠት የተወሰኑ ግለሰቦች ወይም አንድ ግለሰብ(የእርሶ ተወካይ ሆኖ የሚጠራ(የሚጠሩ)) እርሶ መወሰን በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ከሆኑ ስለሚያገኙት የጤና አገልግሎት ውሳኔ እንዲሰጡ የሚል ወረቀት ይፈርማሉ፡፡
ተወካዬ ምን አይነት ውሳኔዎችን መወሰን ይችላል?
ተወካይዎ በጣም ሰፊ የሆነ የህክምና አገልግሎት ውሳኔዎችን መወሰን ይችላል የሚከተሉትን ጨምሮ፡
- እርሶን ነርሶች ቤት ወይም ሆስፒታል ስለማስገባት ወይም ስለማስወጣት፡
- የትኛው አይነት ህክምና ወይም መድሀኒት መውሰድ እንደሚፈልጉ እና እንደማይፈልጉ፡ እንዲሁም
- የእርሶን የህክምና መረጃ ማን ማየት እንደሚችል፡፡
ተወካይዎ እነዚህን ውሳኔዎች ማድረግ የሚችለው እርሶ በራሶ መወሰን የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ከሆኑ ብቻ ነው፤ ተወካይዎ እነዚህን ውሳኔዎች በሚያደርግበት ወቅት የእርሶን ፍላጎት ተከትሎ መሆን ይኖርበታል፡፡
ተወካዬ እኔ የምፈልገውን ነገር እንዴት ሊያውቅ ይችላል?
በፅሁፍ ማስቀመጥ ይኖርቦታል፡፡ የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና በሚሰጡበት ወቅት የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡
- በህይወት ለመቆየት ዶክተርዎ ማሽን መቼ እንዲጠቀም እንደሚፈልጉ እና እንደማይፈልጉ መግለፅ
- ምግብ እና ውሀ የሚያቀርብልዎ የመመገቢያ ቱቦ መቼ እንዲገጠም እንደሚፈልጉ እና እንደማይፈልጉ መግለፅ
- በሚሞቱበት ወቅት አካልዎ ምን እንዲደረግ እንደሚፈልጉ ለተወካይዎ መንገር
- መለገስ የሚፈልጉት አካል ካለ መግለፅ እና
- አስፈላጊ ከሆነም ህጋዊ ሞግዚቶ እንዲሆን የሚፈልጉትን ሰው ስም መጥቀስ ናቸው፡፡
ከዚህ በታች ሊጠቀሙ የሚችሉትን ቅፅ ይመልከቱ፡፡
ተወካዬ እንዲሆን ማንን መምረጥ አለብኝ?
ማንኛውንም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ እና ዶክተሮ ወይም የህክምና አገልግሎት ሰጪዎ ያልሆነ ግለሰብ መምረጥ ይችላሉ፡፡ ተወካይዎ የቤተሰብዎ አባል፣ ጓደኛዎ ወይም የሀይማኖት አማካሪዎ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሊያምኑት የሚችሉት አይነት እና ፍላጎትዎን ሊያሟላ የሚችል ሰው መምረጥ ይኖርቦታል፡፡
ፍላጎትዎን ከተወካይዎ ወይም ተወካዮችዎ ጋር መወያየት ይኖርቦታል፡፡ ምንም እንኳ ማድረጉ በጣም አስቸጋሪ እና አሳዛኝ ቢሆንም የሚመርጡት ሰው ለእርሶ ውሳኔ ለመወሰን ፈቃደኛ የሆነ ግለሰብ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርቦታል፡፡
ከአንድ በላይ ተወካይ መምረጥ እችላለሁ?
አዎ፡፡ ህጉ ከአንድ በላይ ተወካዮችን ማለትም ተባባሪ-ወኪሎች(ሁለት ግለሰቦች በአንድ ላይ እንደ እኩል ሆነው የሚያገልግሉ) ወይም ተከታታይ ወኪሎች (ሁለተኛው ተወካይ አንደኛው ተወካይ በአጋጣሚ መወሰን የማይችል ከሆነ ተክቶ የሚያገለግል) እንዲመርጡ ይፈቅዳል፡፡
ነገር ግን ከአንድ በላይ ተወካይ ከመረጡ ግራ መጋባት ወይም ግጭት ኪፈጠር ይችላል፡፡ ለምሳሌ፤ በድንገተኛ አደጋ ወቅት የህክምና አገልግሎት ሰጪዎ አንዱን ተወካዮን ብቻ ሊያገኝ ይችላል ወይም ተወካይዎችዎ የእርሶን ፍላጎት ስለማሟላት እርስ በእርሳቸው ላይስማሙ ይችላሉ፡፡
የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ከአንድ በላይ ለሆኑ ወኪሎች ከመስጠት በፊት ሊያስገኝ ስለሚችለው እና ሊያሳጣ ስለሚችለው ነገር (እንዲሁም ሊያሳጣ የሚችለውን ነገር ስለመፍታት) ከጠበቃ ጋር መወያየት ብልህነት ነው፡፡
ተወካዬ ልክ እንደእኔ እንዲያደርግ ይጠበቅበታል?
በጭራሽ፤ ወኪሎ እንደ እርሶ እንዲያደርግ ህግ አያስገድደውም፡፡ ነገር ግን፤ ወኪሉ ለመስራት ቢመርጥ, እሱ ወይም እሷየእርሶን ፍላጎት መከተል አለባቸው፡፡
ወኪሌ ለሚያደርገው ወይም ለምታደርገው ነገር በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ?
በጭራሽ፤ በ "መልካም እምነት" ላይ ተመስርተው እስካደረጉ ድረስ እና በእርሶ መመሪያ መሰረት እስከፈፀሙ ድረስ ህጉ እሱን ወይም እሷን ለተግባሩ ወይም ለተግባሯ ከመከሰሰስ ይጠብቃል፡፡
ስለ ጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ሀሳቤን መቀየር እችላለው?
አዎ፡፡ ሀሳብዎን ከቀየሩ፤ በእጆ ላይ ያለውን የውክልና ቅፅ ግልባጭ በሙሉ ማስወገድ እና ሀሳብዎን ስለመቀየርዎ ለሁሉም ግልባጩ ለሚኖራቸው ሰዎች መንገር ይኖርቦታል፡፡ ከዚያ በኋላ አሁን ላይ ያሎትን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ አዲስ የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ማዘጋጀት ይችላሉ፡፡
የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ከፈረሙ በኋላ ጋቢቻ ከፈፀሙ አዲስ ያገቡትን ግለሰብ እንደ ወኪሎ ቀድመው አስገብተው ካልሆነ በስተቀር ውሉ ወዲያውኑ ከአገልግሎት ውጪ(በህግ ተቀባይነት የሌለው) እንደሚሆን ሊያውቁ ይገባል፡፡
ማንም ሰው ከኔ ላይ "ሶኬቱን እንደማይጎትት" በምን አውቃለሁ?
በእርሶ የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ላይ ዶክተርዎ በህይወት እንዲቆዩ በምን አይነት ሁኔታ ላይ ማሽን ወይም የመመገቢያ ቱቦ መጠቀም እንዳለበት እና እንደሌለበት መግለፅ ይችላሉ፡፡ ወኪልዎ ፍላጎትዎን ማክበር አለበት፡፡
በጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና እና በህይወት የመቆየት ኑዛዜ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?
በጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና በራስዎ መወሰን በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ሲሆኑ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ግለሰቦች እርሶን እንዲወክሉ ማድረግ እና ውሳኔ እንዲሰጡ ያስችላል፡፡ በህይወት የመቆየት ኑዛዜ በአጭሩ ውስን በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ የተወሰነ አይነት አገልግሎቶች ውስጥ ስለመግባት እና ስለመውጣት ያሎትን ፍላጎት ብቻ ይይዛል ለምሳሌ በመጨረሻዎቹ የህይወት ቆይታ ግዜያት ውስጥ ከሆኑ ወይም ቋሚ በሆነ ኮማ ውስጥ ከሆኑ፡፡ በጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ሰፋ ይላል ምክንያቱም በየትኛውም ሁኔታ ላይ ሆነው የሚፈልጉትን አይነት የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በህይወት የመቆየት ኑዛዜ ዙሪያ ተዘውትረው የሚነሱ ጥያቄዎች ይመልከቱ ፡፡
የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና እና ገንዘብ ነክ ወይም አጠቃላይ ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?
የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ስለ እርሶ ስለሚያገኙት የጤና አገልግሎት ሌላ ሰው መወሰን አንዲችል ስልጣን ይሰጣል፡፡ ገንዘብ ነክ ወይም አጠቃላይ ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ከገንዘብ ጋር በተያያዙ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ እንደ እርሶ ሆኖ ሌላ ሰው መወሰን እንዲችል ስልጣን ይሰጣል፡፡ ሁለቱንም ማለትም የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና እና ገንዘብ ነክ ወይም አጠቃላይ ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና እንዲኖሮት ማድረግ ይችላሉ እንዲሁም ለእያንዳንዱ የተለያየ ወኪል ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በአጠቃላይ ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልና ዙሪያ ተዘውትረው የሚነሱ ጥያቄዎች ይመልከቱ፡፡
የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልናለማዘጋጀት መጠቀም የምችለው ቅፅ ይኖራል?
አዎ፡፡ ጠቅ ያድርጉ እዚህ ጋር የጤና አገልግሎት ዘላቂነት ያለው የህግ ውክልናን በህይወት ከመቆየት ኑዛዜ ጋር አቀናጅቶ የያዘ ቅፅ፡፡