Website Survey

የፍርድ ቤት ትእዛዝ መስጠት በዲሲ- የፍቺና የማሳደግ ጉዳዮች

Authored By: D.C. Bar Pro Bono Center

Contenido

Information

የፍርድ ቤት ሰነዶችን ሲያስገቡ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች በሙሉ ግልባጭ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ግልባጩ እንዲደርሳቸው ማድረግ ያለበት ፍርድ ቤቱ ሳይሆን ኃላፊነቱ የእርሶዎ ነው፡፡ ይህም ሂደት አገልግሎት ይባላል፡፡ የተለያዩ ሁኔታዎች የተለያዩ አገልግሎቶች ይኖራቸዋል፡፡

የጥሪ እና ክስ አገልግሎት

የፍች ወይም የሞግዚትነትን ጉዳይ በተመለከተ መጀመሪያ ፍርድ ቤት የምታስገቡት ሰነድ ክስ ይባላል፡፡ ክስ ፍርድ ቤት ሲያስገቡ የሚሰጥዎት ፎርም ጥሪ ይባላል፡፡ አስፈላጊውን የፍርድ ቤት አቤቱታ በድረ ገጽ www.dcbar.org/pleadings ወይም በዲሲ ከፍተኛ የቤተሰብ ፍርድ ቤት መካከለኛው ቅጽ መሙያ ማዕከል በ (500 Indiana Avenue NW, room JM-540), ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል እስከ ከምሽቱ አስራ አንድ ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጥሪው ግልባጭ እና ክሱን ጉዳዩ ለሚመለከተው ለሌላኛው ወገን ማድረስ አለብዎት፡፡

ጥሪውን እና ክሱን ከታች በተጠቀሱት በአንዱ መንገድ ማድረስ ይኖርብዎታል፣

  1. በሰው በኩል፡ በጉዳዩ ውስጥ የሌለ ለዓቅመ ዓዳም የደረሰ ሰው ለሌላው ወገን ጥሪውን እና ከሱን በእጅ እንዲሰጥ ይጠይቁ፡፡ይህንን እራስዎ ማድረግ አይችሉም፡፡ ጓደኛ፣ ቤተዘመድ፣ ወይም በዚህ ጉዳይ የሚያገለግል ባለሙያ እንዲሰጥልዎት መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ሌላው ወገን ሊገኝ በሚችልበት በማንኛውም ቦታ፣ ለምሳሌ በቤቱ፣ በሥራ ቦታ ወይም መንገድ ላይ ሊሰጠው ይቻላል፡፡
  2. በሌላ እቤቱ ውሰጥ በሚኖር ሰው፣ በጉዳዩ ውስጥ የሌለ ለዓቅመ ዓዳም የደረሰ በቤቱ ውስጥ በሚኖር ሰው በእጁ እንዲሰጠው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ይህንን እራስዎ ማድረግ አይችሉም፡፡ጓደኛ፣ ቤተዘመድ፣ ወይም በዚህ ጉዳይ የሚያገለግል ባለሙያ እንዲሰጡልዎት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  3. በተረጋገጠ ፖሰታ የተመላሸ ደረሰኝ ባለው፣በተረጋገጠ ፖሰታ የተመላሸ ደረሰኝ ባለው ጥሪውን እና ክሱን መላክ ይችላሉ፡፡ እርስዎ ይህንን ፖስታ ቤት በመሄድ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ደብዳቤው ከደረሰ በኋላ ፖስታ ቤቱ ተመላሽ ደረሰኝ ("አንዳንዴ አረንጓዴ ካርድ ተብሎ ይጠራል") ይልክልዎታል፡፡ ደብዳቤውን በመኖሪያ ቤቱ አድራሻ መላኩ ይመረጣል፡፡ ሌላው ወገን ወይም ለዓቅመ ዓዳም የደረሰ በቤቱ ውስጥ የሚኖር ሰው አረንጓዴውን ካርድ ፈርሞ መቀበል አለበት፡፡

ክሱንና ጥሪውን ለማድረስ ምን ያህል ጊዜ ይኖረኛል?

60 ቀኖች ይኖርዎታል፡፡ ተጨማሪ ጊዜ ካስፈለገዎት የቤተሰብ ፍርድ ቤት መካከለኛው ቅጽ መሙያ ማዕከል ጥሪውን እና ክሱን ለማስገባት ተጨማሪ 60 ቀኖች መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የሁለተኛውን ጥሪ የመጀመሪያው ጥሪ የጊዜ ገደብ ከማለቁ በፊት መጠየቅ አለብዎት፡፡ ከዛ በኋላም ተጨማሪ ጊዜ ካስፈለገዎት ዳኛውን በጽሁፍ መጠየቅ አለብዎት፡፡

ጥሪውን እና ክሱን ማድረሴን በምን አረጋግጣለሁ? ሌላው ወገን

ከተሰደደለት በኋላ የአገልግሎት ምስክርነት በቤተሰብ ፍርድ ቤት መካከለኛው ቅጽ መሙያ ማዕከል ማስገባት አለብዎት፡፡ ይህም በመሀላ የተደገፈ መቸ እና እንዴት እንደተላከ የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ ይህንን የምስክርነት ቃል ካላስገቡ ፍርድ ቤቱ ጉዳይዎን አያንቀሳቅሰውም፡፡

የምስክርነት ወረቀቱ እንዳገባቡ የተለያዩ አስፈላጊ ድርጊቶች አሉት፣

  1. በሰው በኩል፣ ለዓቅመ ዓዳም የደረሰ ጥሪውን ያደረሰው ሰው የምስክርነት ሰነዱን ይሞላል፡፡.
  2. በሌላ እቤቱ ውሰጥ በሚኖር ሰው፣ ለዓቅመ ዓዳም የደረሰ ጥሪውን ያደረሰው ሰው የምስክርነት ሰነዱን ይሞላል፡፡
  3. በተረጋገጠ ፖሰታ የተመላሸ ደረሰኝ ባለው፣ የምስክርነት ሰነዱን እርስዎ ሞልተው አረንጓዴ ካርዱን ማያያዝ አለብዎት፡፡.

ጥሪውን እና ክሱን ካልሰደዱ እና የአገልገሎት ምስክርነቱን ሞልተው በተፈላጊው ጊዜ ውስጥ ካላስገቡ ጉዳይዎ ሊዘረዝ ይችላል፡፡ እንደገና እንደ ኣዲስ መጀመር ይኖርብዎታል፡፡

ሌላውን ወገን ማግኘት ባልችልስ?

ሪውን በጋዜጣ ማሳተም ወይም መለጠፍ ይችላሉ፡፡ መጀመሪያ ግን ሌላውን ወገን ለማግኘት ጥረት ማድረግ አለብዎት፡፡ ያደረጉትን ጥረት በሙሉ በሚያስገቡት ወረቀት ውስጥ ይጥቀሱ፡፡ ደኛው ውሳኔውን በፍርድ ቤት ችሎት ወይም በፖስታ ቤት በኩል ያስታውቅዎታል፡፡ ዳኛው በቂ ጥረት አላደረጉም ብሎ ካመነ፣ ጥረትዎን ቀጥለው የጠፈውን ወገን ካለገኙት ሌላ ጥሪ ማስጋባት ይኖርብዎታል፡፡

  1. በታተመ ጽሁፍ፣ የታተመ ጽሁፍ ማለት በጋዜጣ ላይ ማሳተም ማለት ነው፡፡ ዳኛው ከፈቀደ ማስታወቂያውን ለማሳተም ወደ የቤተሰብ ፍርድ ቤት መካከለኛው ቅጽ መሙያ ማዕከል መሄድ ይኖርብዎታል፡፡ ማስታወቂያውን በሁለት ጋዜጦች በሳምንት አንድ ጊዜ ለሦስት ሳምንታት ማሳተም አለብዎት፡፡
  2. ማስታወቂያ በመለጠፍ፣ መለጠፍ ማለት በፍርድ ቤት ማስታወቂያ መለጠፍ ማለት ነው፡፡ ማስታወቂያውን ለማሳተም ገንዘብ ከሌለዎት ማስታወቂያው እንዲለጠፍልዎት መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የገንዘብ ክፍያው ተሰርዞልዎት ከሆነ በጥሪው ላይ መጥቀስ ይኖርብዎታል፡፡ዳኛው ማስታወቂያው በሀትመት ፋንታ እንዲለጠፍ መፈቀድ ወይም አለመፈቀዱን ውሳኔ ይሰጥዎታል፡፡ መለጠፉ ከተፈቀደልዎት የፍርድ ቤቱ ፀኃፊ ለ21 ቀናት ይለጥፍልዎታል፡፡

በማሳተም ወይም በመለጠፍ መግባቱን በምን አረጋግጣለሁ

  1. በታተመ ጽሁፍ፣ ጋዜጣው የመታተሙን ማረጋገጫ ለፍርድ ቤቱ ይልካል፡፡
  2. ማስታወቂያ በመለጠፍ፣ የፍርድ ቤቱ ፀኃፊ አስፈላጊውን ስለሚያደርግ እርስዎ የምስክርነት ሰነዱን ማሰገባት የለብዎትም፡፡

ከመጀመሪያው ከስ በኋላ የፍርድ ቤት ሰነዶች ማስገባት

ባጠቃላይ፣ በጉዳዩ ያስገቡዋቸው ሰነዶች እንደ መልስ ወይም ጥሪ ለሌላው ወገን መድረስ አለባቸው፡፡ እነኝህ ሰነዶች በአንደኛ ከፍል ፖስታ መሰደድ አለባቸው፡፡ ሌላው ወገን ጠበቃ ካለው ለጠበቃው በፖስታ ቤት በኩል ይላኩለት፡፡ ሌላው ወገን ጠበቃ ከሌለው ቀጥታ ለእራሱ ስደዱለት፡፡ ሰነዱን ለሌላው ወገን ወይም ለጠበቃው በእጅ መስጠት ይችላሉ፡፡

ሌሎች የፍርድ ቤት ሰነዶች ከመጀመሪያው ማመልከቻ በኋላ መስደዴን በምን አረጋግጣለሁ?

መጀመሪያው ክስ በኋላ የፍርድ ቤት ሰነዶች ሲያስገቡ ለማን እንዳስደዱ፣ በምን (በፖስታ ቤት ወይም በእጅ)፣ በየትኛው አድራሻ እና ቀኑን የሚገልጽ የአገልግሎት ሰርቲፊኬት መስገባት አለብዎት፡፡

የመጨረሻው ትዕዛዝ ከገባ በኋላ የሚሰደዱ የፍርድ ቤት ሰነዶች በአጠቃላይ፣

የመጨረሻው ትዕዛዝ ወይም ፍርድ በጉዳዮ ላይ ከተሰጠ ከ60 ቀናት በኋላ ማመልከቻ ወይም ሙግት ቢያሰገቡ ሰነዶቹ ልክ ጥሪ እና ከስ እንደሚያስገቡ መሆን አለበት፡፡

ለመረጃ፣

ነጻ አገልግሎት የሚሰጥበትን የቤተሰብ ፍርድ ቤት እራስ አገዝ ማዕከል፣በዲ.ሲ. ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውስጥ በሚከተለወ አደራሻ DC Superior Court, 500 Indiana Avenue, NW, Room JM-570 ይጎብኙ፡፡ ማዕከሉ ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል እሰከ ከምሽቱ አሰራ አንድ ሰዓት ድረስ ክፍት ነው፡፡ ማዕከሉ አስፈላጊዎቹን ሰነዶች ለመሙላት የሚያስፈልግዎትን ይረዳዎታል ወይም ወደ ሌላ ነፃ መረጃዎች ወደሚያገኙበት ይመራዎታል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና ሌሎች ነፃ የሕግ አገልግሎቶች እንዴት ለማግኘት እንደሚችሉ በድረ ገጽ www.lawhelp.org/dc ይመልከቱ ወይም የዲ.ስ. ባር የሕግ ዕርዳታ መስመር በስልክ ቁጥር 202-626-3499 ይደውሉ፡፡

የ D. C. Bar Pro Bono ፕሮግራም የሚሰጠው አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው፡፡ የሕግ አማካሪ አይደለም፡፡ ህግን በተመለከተ ምክር ከጠበቃ ያገኛሉ፡፡ ለተወሰነ ጉዳይ የህግ ምክር ከፈለጉ ወደ ጠበቃ ይሂዱ፡፡ የሕግ መማሪያ ጽሁፎችን ወቅታዊ ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ሕጎች በየጊዜው ይቀያየራሉ፡፡ ስለዚህ የ D. C. Bar Pro Bono ፕሮግራም ለዚህ መረጃ ትክክለኛነት ዋስትና የለውም፡፡

Last Review and Update: Oct 04, 2018
Volver arriba