Website Survey

የልጅ ድጋፍ በዲ.ሲ። ጉዳይን መጀመር

Authored By: D.C. Bar Pro Bono Center

Contenido

Information

የልጅ ድጋፍን የፍርድ ክርክር ለማስጀመር የሚችሉባቸው አራት የተለያዩ መንገዶች አሉ።

1. የፍርድ ክርክር ፋይልን ለማስገባት የዲሲን የሕፃን ድጋፍ

አገልግሎቶች ዲቪዚዮንን ይጠይቁ። የሕፃን ድጋፍ አገልግሎቶች ድቪዚዮን [Child Support Services Division (CSSD)] ጠበቆቹ የወላጅነት መብትን እና የሕፃን ድጋፍ የፍርድ ቤት ትዕዛዞችን ለማስከበር የሚሠሩ የዲሲ ኤጀንሲ ነው። ለችግረኛ ቤተሰቦች ጊዜያዊ እርዳታ [Temporary Assistance for Needy Families (TANF)] ወይም Medicaid የሚቀበሉ ከሆኑ CSSD አገልግሎቶችን በነጻ ያቀርባል። እርስዎ TANF ወይም Medicaid ላይ ከሌሉበት CSSD $5 አገልግሎት ክፍያን ሊጠይቅዎት ይችል ይሆናል (የገንዘብ ትዕዛዝ መስጫ ወይም ቼክ ብቻ ተቀባይነት ይኖረዋል፣ ገንዘቡ ለ D.C. Treasurer ተከፋይ ይሆናል)። ለአንዳንድ አገልግሎቶች ተጨማሪ ክፍያዎች ሊጠየቁ ወይም ከማናቸውም ከተሰበሰቡ የልጅ ድጋፍ ገንዘቦች ላይ ተቀናሽ ሊደረጉ ይችሉ ይሆናል። CSSD የኮሎምቢያ ዲስትሪክትን የወላጅነት መብት እና የልጅ ድጋፍ ጉዳዮችን ጥቅሞች የሚያስከብር መሆኑን እባክዎ ልብ ይበሉ። CSSD በተናጥል ግለሰብ ወላጆችን ወይም ሕጋዊ ሞግዚቶችን አይወክልም።

እንዴት ማመልከት እችላለሁ?

ቀጠሮ ለማስያዝ ወይም ማመልከቻን ለመጠየቅ ወደ 202-442-9900 ይደውሉ። ወይም ማመልከቻን ለማውረድ ወደ የድር ጣቢያው http://www.cssd.dc.gov ላይ ይሂዱ። ማመልከቻውን ይሙሉት እና ይፈርሙበት። የሚከተሉትን ቅጂዎች (ኦርጂናሎቹን ሳይሆን) ዓባሪ ያያይዙ፦

  • የእያንዳንዱ ልጅ የልደት የምስክር ወረቀት።
  • ማናቸውም የመለያየት ስምምነቶችን፣ የፍቺ ውሳኔዎችን፣ የአሳዳጊነት ትዕዛዞችን፣ ወይም የወላጅነት ማረጋገጫ ሰነዶችን።
  • ማናቸውም አሁን በሥራ ላይ ያሉ የልጅ ድጋፍ ትዕዛዞችን (የተረጋገጡ)፤
  • የእርስዎ ገቢ ማረጋገጫ፤
  • የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ፤
  • የማንነት መለያ ማረጋገጫ (በመንግሥት የተሰጠ ፎቶ ያለበት መታወቂያ)።

የማመልከቻ እሽጉን ወደየሚከተለው በአካል ይውሰዱ ወይም በፖስታ ቤት ይላኩ፦

Child Support Services Division
Office of the Attorney General
441 4th Street NW, Suite 550 North
Washington DC 20001

ከዚህ ሌላ CSSD እንዴት ሊያግዘኝ ይችላል?

ተጨማሪ ለማወቅ፣ ቢሮውን በስልክ ማነጋገር ወይም በአካል ተገኝተው መጠየቅ ይችላሉ። የሥራ ሰዓታት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 8:15 a.m. እስከ ቀኑ 4:45 p.m. ድረስ ነው።

2. ጠበቃ በነጻ ለማግኘት።

ማመልከቻ ያስገቡ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች በልጅ ድጋፍ የፍርድ ቤት ጉዳዮች ላይ በዲሲ ውስጥ የሚያግዙ በርካታ ነጻ የሕግ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች አሉ። የልጅ ድጋፍ ጉዳዮችን በመያዝ ላይ የሚሠሩ ፕሮግራሞችን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት www.lawhelp.org/dc ወይም Family Court Self-Help Center (የዚህን ወረቀት መጨረሻ ይመልከቱ) ይጎብኙ።

3. የራስዎት ጠበቃ ይሁኑ።

የራስዎት ጠበቃ ይሁኑ። የልጅ ድጋፍ የፍርድ ቤት ጉዳይን ለመጀመር ጠበቃ አያስፈልግዎትም። የሚያስፈልግዎትን ሕጋዊ ወረቀቶች (አቤቱታ ማቅረቢያ ሰነዶች) www.dcbar.org/pleadings ላይ ወይም D.C. Superior Court Family Court Central Intake Center (500 Indiana Avenue NW፣ ክፍል ቊጥር JM-540) ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ቢሮው ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 8:30 a.m. እስከ 5:00 p.m. ድረስ ክፍት ነው።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ የልጅ ድጋፍ ውሳኔ እንዴት እንደሚሰጥ የሚያብራራውን “የልጅ ድጋፍ በዲሲ ውስጥ” የሚለውን መረጃ ሰጪ ወረቀት ይመልከቱ።

በመጀመሪያ፣

አቤቱታዎችን ፋይል ያስገቡ። ወላጅነትን ለመመሥረት እና/ወይም ድጋፍን ለማረጋገጥ አቤቱታ ማቅረቢያ ሰነድን ያስገቡ። የእርስዎን ወረቀቶች ወደ D.C. Family Court Central Intake Center ይውሰዱዋቸው። የፋይል ማስከፈቻ ክፍያ $80 መክፈል ይኖርብዎታል (ዋና ክሬዲት ካርዶች፣ ጥሬ ገንዘብ ወይም በገንዘብ ማዘዣ ሰነድ አማካይነት ይከፍላሉ)። ክፍያውን መክፈል የማይችሉ ከሆነ እንዴት የፍርድ ቤት የመዝገብ ክፍያ እና ወጪዎችን ሳይከፍሉ ፍርድ ቤቱ እንዴት ፋይል እንዲያስገቡ ሊፈቅድልዎት እንደሚችል ማብራሪያ የሚሰጠውን “በዲሲ ውስጥ የክፍያ ይለፈኝ መጠየቂያዎች” የሚለውን መረጃ ሰጪ ወረቀት ያንብቡት። የእርስዎን ፋይል ባስገቡበት ተመሳሳይ ቀን ላይ የችሎት የሚሰየምበት ቀን ይሰጥዎታል፣ ይህም በ45 ቀናት ውስጥ የሚደረግ ይሆናል። የ Central Intake Center ለእርስዎ የችሎቱን ቀን የሚያሳየውን የችሎት ማስታወቂያ እና የፍርድ ቤት መቅረቢያ ትዕዛዝን [Notice of Hearing and Order Directing Appearance (NOHODA)] ይሰጥዎታል።

በመቀጠል፣

Yአቤቱታ ሰነዶቹን ለሌላኛው ወገን ይስጡ ወይም ያሰጡ። ሌላኛው ወላጅ የአቤቱታውን እና የ NOHODA ቅጂዎችን እንዲያገኝ ማድረግ ይኖርብዎታል። ይህን ለማድረግ የሚችሉባቸው አራት የተለያዩ መንገዶች አሉ፦

  1. የግል አገልግሎት፦ በጉዳዩ ላይ እጁ ያለበት ዐዋቂ ሰው የአቤቱታ እና የ NOHODA ሰነዶችን በግሉ ለሌላኛው ወላጅ እንዲሰጥልዎት መጠየቅ። ይህንን እርስዎ ራስዎ ማድረግ አይችሉም። ጓደኛ፣ ዘመድ ወይም ሕጋዊ ባለሙያ የዚህ ዓይነት ሂደትን አገልግሎት ሰጪ ሰነዶቹን እንዲሰጥልዎት መጠየቅ ይችላሉ።
  2. ተተኪ አገልግሎት በቤት ውስጥ፦ በቤቱ ውስጥ የሚኖር በጉዳዩ ላይ እጁ ያለበት ዐዋቂ ሰው የአቤቱታ እና የ NOHODA ሰነዶችን በግሉ ለሌላኛው ወላጅ ወደ ቤቱ እንዲሄድ እና ሰነዶቹን እንዲሰጥልዎት መጠየቅ። ይህንን እርስዎ ራስዎ ማድረግ አይችሉም። ጓደኛ፣ ዘመድ ወይም ሕጋዊ ባለሙያ የዚህ ዓይነት ሂደትን አገልግሎት ሰጪ ሰነዶቹን እንዲሰጥልዎት መጠየቅ ይችላሉ።
  3. ተተኪ አገልግሎት በመሥሪያ ቤት ውስጥ፦ በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ የሚሠራ በጉዳዩ ላይ እጁ ያለበት ዐዋቂ ሰው የአቤቱታ እና የ NOHODA ሰነዶችን በግሉ ለሌላኛው ወላጅ ወደ መሥሪያ ቤቱ እንዲሄድ እና ሰነዶቹን እንዲሰጥልዎት መጠየቅ። ይህንን እርስዎ ራስዎ ማድረግ አይችሉም። ጓደኛ፣ ዘመድ ወይም ሕጋዊ ባለሙያ የዚህ ዓይነት ሂደትን አገልግሎት ሰጪ ሰነዶቹን እንዲሰጥልዎት መጠየቅ ይችላሉ።
  4. የተረጋገጠ ፖስታ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፖስታ አገልግሎት፦ አቤቱታ ሰነዱን እና NOHODA በተረጋገጠ ፖስታ፣ ለመቀበል ማረጋገጫ ደረሰኝ የሚያስቆርጥ ፖስታ አገልግሎትን በመጠቀም ለሌላኛው ወላጅ ፖስታ ይላኩለት። ይህንን እርስዎ ራስዎ በፖስታ ቤት በመገኘት ማድረግ ይችላሉ። ፖስታ ቤቱ ደብዳቤውን እንዳደረሰ የመቀበል ማረጋገጫ ደረሰኝ (“አረንጓዴ ካርድ”) ለእርስዎ በፖስታ ቤት በኩል ይልክልዎታል። እርስዎ በፖስታ ቤት በኩል አቤቱታ ሰነዶችን እና NOHODA በተረጋገጠ ደብዳቤ በላኩበት ተመሳሳይ ቀን ላይ ለሌላኛው ወላጅ የ NOHODA ሁለተኛ ቅጂን በአንደኛ ደረጃ ፖስታ አገልግሎት በኩል ይላኩለት። ፍርድ ቤቱ (1) ሌላኛው ወገን በተመላሽ ደረሰኝ ላይ ከፈረመ፤ ወይም (2) በተመሳሳይ ቤት ውስጥ የሚኖር ወይም መሥሪያ ቤት ሥራ የሚሠራ ሌላ ዐዋቂ ሰው ተመላሽ ደረሰኙ ላይ ስለመቀበሉ በማረጋገጥ ከፈረመ አገልግሎቱን እንደ “ጥሩ” አገልግሎት ይቆጥረዋል። ተመላሽ ደረሰኙ ላይ ማንም ሰው ካልፈረመበት ሆኖም ግን በመጀመሪያ ደረጃ ፖስታ አገልግሎት የተላከው ደብዳቤ ቅጂ ለእርስዎ ተመላሽ ካልሆነ፣ የልጅ ድጋፍን በሚመለከተ ባለ የፍርድ ክርክር ላይ አገልግሎቱ እንደ “ጥሩ” ይቆጠራል ሆኖም ግን ወላጅነት መብትን በሚመለከት ግን ተቀባይነት አይኖረውም።

በመቀጠል የአገልግሎት የእምነት ቃል ማረጋገጫ ፋይል ያስገቡ።

የአገልግሎት የእምነት ቃል ማረጋገጫ እንዴት ሌላኛው ወላጅ ሰነዶቹን እንዳገኘ በማረጋገጥ በቃለ መሐላ የሚሰጥ ሰነድ ነው። የእርስዎን ቃለ መሐላ በ Family Court Central Intake Center ማስገባት ይኖርብዎታል። ሌላኛው ወላጅ በግል ወይም በተተኪ አገልግሎት በኩል ሰነዶቹ እንዲደርሱት ከተደረገ፣ ሰነዶቹን የሰጠው ዐዋቂ ሰው ቃለ መሐላውን መሙላት ይኖርበታል። ለሌላኛው ወገን በተረጋገጠ እና በመጀመሪያ ደረጃ የፖስታ አገልግሎት ሰነዶቹን እንዲያገኝ ካደረጉ፣ ቃለ መሐላውን እርስዎ ራስዎ መሙላት አለብዎት።

የእርስዎን ችሎት በአካል ተገኝተው ያዳምጡ።

የእርስዎን የገቢ ማረጋገጫ፣ ለልጁ የሚያወጡትን የጤና ኢንሹራንስ ወጪዎች፣ የልጅ እንክብካቤ ወጪዎች፣ ለልጁ የሚደረጉ ማናቸውም ተጨማሪ ወጪዎች፣ እና ስለ ሌላኛው ወላጅ ገቢ እርስዎ ያልዎት ማናቸውም መረጃን ማረጋገጫ ይዘው ይቅረቡ።

4. የግል ጠበቃ ይቅጠሩ።

የግል ጠበቃ ይቅጠሩ። የልጅ ድጋፍ የፍርድ ቤት ክርክር ጉዳዮችን የሚያስተናግዱ የግል ጠበቃዎችን ዝርዝር ለማግኘት የ Bar Association of the District of Columbia’s Lawyer Referral Service የዳሰሳ ጥናትን https://badc.barlrs.com ላይ ይሙሉ። መላኪያው አገልግሎት ክፍያው $39.95 ነው። ሪፌራሎችን በተጨማሪ ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ማግኘት ወይም መሥመር ላይ (ኦንላይን) መፈለግና ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፣

ያለ ቀጠሮ ነጻ የምክር አገልግሎት የሚሰጠውን የቤተሰብ ፍርድ ቤት ራስ-አገዝ ማእከል [Family Court Self- Help Center] የሚባለውን በ D.C. Superior Court, 500 Indiana Avenue, NW ውስጥ በክፍል ቊጥር JM-570 ላይ ሊጎበኙት ይችላሉ። ማእከሉ ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 8:00 am – 5:30 pm ድረስ ክፍት ነው። ማእከሉ የፍርድ ሂደቱን ለእርስዎ ሊያብራራልዎት፣ ተገቢነት ያላቸውን ሕጋዊ ወረቀቶች በመሙላት ላይ እርስዎን ሊያግዝዎት፣ እና ወደ ሌላ ነጻ የሕግ አገልግሎት ሰጪዎች ሊመራዎት ይችላል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወይም እንዴት ነጻ የሕግ አገልግሎት ሰጪዎችን ማነጋገር እንደሚቻል ለማወቅ www.lawhelp.org/dc ይጎብኙ ወይም ስለነዚህ ነገሮች የተቀረጹ መልእክቶችን ለማዳመጥ ወደ D.C. Bar Legal Information Helpline በስልክ ቊጥር 202-626-3499 ይደውሉ።

የ D. C. Bar Pro Bono ፕሮግራም የሚሰጠው አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው፡፡ የሕግ አማካሪ አይደለም፡፡ ሕግን በተመለከተ ምክር ከጠበቃ ያገኛሉ፡፡ ለተወሰነ ጉዳይ የሕግ ምክር ከፈለጉ ወደ ጠበቃ ይሂዱ፡፡ የሕግ መማሪያ ጽሁፎችን ወቅታዊ ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ሕጎች በየጊዜው ይቀያየራሉ፡፡ ስለዚህ የ D. C. Bar Pro Bono ፕሮግራም ለዚህ መረጃ ትክክለኛነት ዋስትና የለውም፡፡

This resource has been translated into Spanish, French, and Amharic thanks to the American Bar Endowment.
Last Review and Update: Mar 29, 2024
Volver arriba