Website Survey

እርስዎ በ ICE ከታሰሩ የእርስዎን ልጆች የማሳደግ መብት ላለመነጠቅ አሁን መወሰድ ያለባችው እርምጃዎች

Information

ይህ መመሪያ ጽሑፍ ሊጠቅማቸው ለሚችሉ ማናቸውም ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ለማሠራጨት እባክዎ ነጻነት ይሰማዎት።

አዘጋጆች ስቴፕቶ ኤንድ ጆንሰን የሕግ ባለሙያዎች [Steptoe & Johnson LLP]፣ ወሳኝ ለሆነው ትልቅ እገዛቸው ከፍተኛ ምስጋና ለአዩዳ [AYUDA]፣ የሕፃናት ሕግ ማእከል [Children's Law Center]፣ እና ለካፒታል አካባቢ የስደተኛ መብቶች ቅንጅት [Capital Area Immigrant Rights Coalition] ይድረሳቸው።

ሊንድሴይ ማርሻል [Lindsay Marshall]፣ ሎረን ዳሴ [Lauren Dasse]፣ ሎሪ ሜሩድ [Laurie Melrood] እና ሲንዲ ሽሎሰር [Cindy Schlosser] "በአሪዞና ውስጥ በ ICE ብታሰርስ” የሚለውን በማዘጋጀት ላይ ሁሉም በጣም አስፈላጊ ነበሩና ትልቅ ምስጋናችን ይድረሳቸው። የስፓኒሽኛ ቋንቋ ትርጉምን በማዘጋጀት ላይ ግሎባል ኮሙዩኒቲ ኢን አክሽን [Global Community in Action] ላደረጉት እገዛ እናመሰግናቸዋለን።

© 2017 - Steptoe & Johnson LLP

ይህ መመሪያ ጽሑፍ ሕጋዊ ምክር አገልግሎትን አይሰጥም እንዲሁም ይህን መመሪያ ጽሑፍ ስለተጠቀሙ ብቻ ከስቴፕቶ ኤንድ ጆንሰን የሕግ ባለሙያዎች [Steptoe & Johnson LLP]፣ ከአዩዳ [Ayuda]፣ ከየሕፃናት የሕግ ማእከል [Children’s Law Center]፣

ወይም ከካፒታል አካባቢ የስደተኛ መብቶች ቅንጅት [Capital Area Immigrant Rights Coalition] ጋር ምንም ዓይነት የጠበቃና ደንበኛ ግንኙነትን እንደተፈጠረ ተደርጎ አያስቆጥርም።

This is the first of a two-part guide. You can find the second part here and download the entire guide here.

የዚህ መመሪያ ጽሑፍ ዓላማ

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሚኖሩ ስደተኛ ወላጅ ከሆኑ፣ ይህ መመሪያ ጽሑፍ የተጻፈው ለእርስዎ ነው። ዓላማው የኢሚግሬሽን እና የሕፃን ደኅንነት ጥበቃ ሥርዓቶቹን በተመለከተ ለእርስዎ ግንዛቤ ለመስጠት እና በኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ ሕግ አስከባሪ አካል [Immigration and Customs Enforcement (ICE)] በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በልጆችዎ ላይ ያልዎትን መብት እንዳያጡ ዕቅድ ማዘጋጀት እንዲችሉ እርስዎን ለማገዝ የታለመ ነው። የእርስዎ ቤተሰብ አንድ ላይ መቆየት መቻሉን እርግጠኛ ለመሆን እንዲችሉ ማድረግ የሚችሉት ከሁሉም የተሻለ ነገር መረጃ እንዲኖርዎት ማድረግ እና ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ ነው!

ይህ መመሪያ ጽሑፍ ይህን እንዲያደርጉ እርስዎን ለማገዝ ተብሎ የተዘጋጀ ነው። በበጎ ፈቃደኛ ጠበቆች፣ የመብት ተከራካሪዎች፣ እና የቤተሰብ ሕግ እና የኢሚግሬሽን ኤክስፐርቶች አነስተኛ የቡድን ስብስብ አማካኝነት የተዘጋጀ ነው። በአጠቃላይ አነጋገር፣ በዚህ መመሪያ ጽሑፍ ላይ የተብራራውን ዕቅድ አወጣጥ ለመከተል ጠበቃ መቅጠር አያስፈልግዎትም። ሆኖም ግን በተለይ የሕፃን እና የቤተሰብ አገልግሎቶች ኤጀንሲ [Child and Family Services Agency (CFSA)] የተባለው የዲሲ የሕፃን ጥበቃ ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም በእርስዎ ቤተሰብ ጉዳይ ላይ እጁ ገብቶበት ከነበረ ወይም በሠሩት ጥፋት ምክንያት ታስረው፣ ተከሰው ወይም ተፈርዶብዎት የሚያውቁ ከሆነ እርስዎ በግልዎ ያልዎትን የተሻሉ አማራጮች ይበልጥ መረዳት እንዲችሉ በዚህ ረገድ ልምድ ያለው የኢሚግሬሽን ጠበቃ እና የቤተሰብ ሕግ ነገረ ፈጅ እንዲያማክሩ እንመክርዎታለን። የኢሚግሬሽን እገዛ የሚሰጡ እና የቤተሰብ ሕግ ላይ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶችን በዚህ መመሪያ ጽሑፍ ክፍል 3 ላይ በአካባቢዎ የሚገኙ የሕግ ምክር አገልግሎቶች ሰጪ ድርጅቶችን ዝርዝር ማግኘት ይችላሉ። በዚህ መመሪያ ጽሑፍ ላይ የቀረበው መረጃ ሥርዓቱን መረዳት እንዲችሉ እና ለእርስዎ ቤተሰብ ዕቅድ ማውጣት እንዲችሉ እርስዎን ለማገዝ ተብሎ የተዘጋጀ ነው ሆኖም ግን ምንም ዓይነት ሕጋዊ ምክርን አይሰጥም።

አሁኑኑ ዕቅድ ያውጡ!

በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ቋሚ የሆነ ሕጋዊ የመኖሪያ አቋም የሌልዎት ከሆነ፣ ወይም ሕጋዊ የመኖሪያ አቋም ኖርዎት ሆኖም ግን ተከሰው የሚያውቁ ወይም ተፈርዶብዎት የሚያውቅ ከሆነ፣ በ ICE የመያዝ አደጋ ላይ ያሉ ሊሆኑ ይችላሉ። አሁኑኑ ልጆችዎን ማን ሊንከባከብ እንደሚችል ዕቅድ ማውጣት ለእርስዎ በጣም አስፈላጊ ነው። ምንም ዓይነት ዕቅዶችን ካላደረጉ፣ እርስዎ በ ICE ከተያዙ ወይም እርስዎ ከታሰሩ ወይም በወንጀል ክስ ምክንያት በቁጥጥር ሥር ከዋሉ የእርስዎ ልጆች መጨረሻ በማደጎ አሳዳጊ እንክብካቤ ሥርዓት ውስጥ መግባት የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው። እርስዎ በ ICE በቁጥጥር ሥር ሲውሉ ወይም በሕግ አስከባሪ አካል ከታሰሩ ወዲያውኑ ለራስዎ እና ለቤተሰብዎ መብት ለመከራከር ዝግጁ መሆን አለብዎት እና ይህ መመሪያ ጽሑፍ ይህንን ዝግጅት ለመጀመር ምርጡ ቦታ ነው።

ይህ ክፍል እርስዎ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ወይም ከአገር ከተባረሩ የእርስዎን ልጆች የማሳደግና የመያዝ መብትዎትን በቋሚነት እንዳያጡ የድንገተኛ ጊዜ ዕቅዶችን ዛሬዉኑ ማድረግ ስላሉብዎት ነገሮች ትኩረትን ይሰጣል።

ለእርስዎ ልጆች እንክብካቤ ሊሰጥ የሚችለውን ሰው ለይተው ይወቁ

ክብካቤ ሰጪ (caretaker) ማለት በዩኤስ አሜሪካ ውስጥ ብዙውን ጊዜ እርስዎ ላይ የሆነ ነገር ቢፈጠር የእርስዎን ልጆች ኃላፊነት ወስዶ እንደ እርስዎ ሆኖ እንክብካቤ የሚሰጠን ሰው ለመግለጽ ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው። አብዛኛዎቹ ወላጆች እንዲህ የመሰለው ሰው ማን ሊሆን እንደሚችል በልባቸው ያስቡታል ሆኖም ግን ይህን ግለሰብ ለልጆቻቸው እንደ ኦፊሴላዊ፣ ወይም “ሹመት” የተሰጠው ክብካቤ ሰጪ አድርገው ለመሾም መደበኛ ዕቅዶችን አያዘጋጁም። ድንገት እርስዎ በ ICE ቢያዙ ለእርስዎ ልጆች እንክብካቤ አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ ከዚህ በታች የተሰጡትን ቅደም ተከተል እርምጃዎች ይከተሉ።

የተሾመው ክብካቤ ሰጪ ማንም የመረጡት ሰው ሊሆን ይችላል። ይህም የእርስዎን የትዳር ጓደኛ ወይም የልጆችዎ ሌላኛው ወላጅን የሚያካትት ቢሆንም የግድ ይህንን ሰው መሆን የለበትም። ክብካቤ ሰጪው በተጨማሪ የእርስዎ እናት ወይም አባት ወይም የእርስዎ አክስት ወይም አጎት፣ ወንድም ወይም እህት፣ ወይም ሌሎች ዘመዶች ሊሆኑ ይችላሉ። የክርስትና አባት ወይም እናት ወይም ቅርብ ጓደኛ ወይም ጎረቤት ሊሆኑ ይችላሉ። በርካታ ክብካቤ ሰጪዎችን ሊያስቡ ይችሉ ይሆናል። ከአንድ በላይ ልጅ ካልዎት ለተለያዩ ልጆች የተለያዩ ክብካቤ ሰጪ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ለመሾም ሊያስቡ ይችሉ ይሆናል።

እንደ ጥሩ አማራጭ በአጠቃላይ አነጋገር CFSA የእርስዎን ልጆች ተረክቦ ኃላፊነቱን እንዳይወስድ እና በቤተሰብ ፍርድ ቤት በእርሶ ላይ ክስ እንዳይመሠርት (የቸልተኝነት ክስ የፍርድ ክርክር ሂደት በመባል ይታወቃል) ለማድረግ እርስዎ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ የእርስዎ የተሾመው ክብካቤ ሰጪ ወዲያውኑ የእርስዎን ልጆች ይረከባቸዋል።

ከተመረጠው ሰው ጋር ስለ ጉዳዩ ይነጋገሩበት

የእርስዎ ልጆች ክብካቤ ሰጪ እንዲሆን እንዲጠየቅ አንድን ግለሰብ ለይተው ከመረጡ በኋላ ቀጣዩ እርምጃ ከእሳቸው ጋር ስለዚህ ጉዳይ መነጋገር ነው። በዕቅዶቹ ዙሪያ ሁለታችሁም አንድ ዓይነት ነገር እንደምታስቡና እንደምትስማሙ እርግጠኛ ለመሆን ከክብካቤ ሰጪው ጋር መወያየት የሚያስፈልጋቸው በርካታ አስፈላጊ ነገሮች አሉ። እርስዎ በ ICE ከተያዙ የእርስዎን ልጆች ለመንከባከብ እሳቸው ምን ዓይነት ግዴታዎችን መወጣት እንዳለባቸው መረዳታቸውን ያረጋግጡ። የእርስዎ ክብካቤ ሰጪ ላልተወሰነ ጊዜ የእርስዎን ልጆች ተቀብሎ ክብካቤ ለመስጠት ፍላጎት እና አቅሙ እንዳላቸው ያረጋግጡ። የኢሚግሬሽን ጉዳዮች እና የቤተሰብ ሕግ ጉዳዮች እልባት እስኪያገኙ ድረስ ወራት አንዳንድ ጊዜም ዓመታትን ሊወስዱ ይችሉ ይሆናል እና በዚህ ጊዜ ሁሉ የእርስዎ ልጆች በተረጋጋ መኖሪያ ቤት ውስጥ መቆየታቸውን እርግጠኛ መሆን ያስፈልግዎታል።

Hበደንብ ሊያስቡባቸው የሚገቡ እና እርስዎ በ ICE ድንገት በቁጥጥር ሥር ቢውሉ የእርስዎን ልጆች ተቀብለው ክብካቤ ለመስጠት ፍላጎት እና አቅሙ እንዳላቸው በምትወያዩበት ጊዜ፣ የእርስዎ ክብካቤ ሰጪ ሆኖ ሊሾም የሚችለውን ሰው መጠየቅ ያሉብዎት አንዳንድ ጥያቄዎች ከዚህ በመቀጠል ተሰጥተዋል።

ለምን ያክል ጊዜ የእርስዎን ልጆች መንከባከብ ይችላሉ?

ሁለታችሁም የሚያጋጥመው ችግር የሚቆየው ለጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት ብቻ ይሆናል ብላችሁ ልታስቡ ትችሉ ይሆናል፤ ሆኖም ግን መጥፎ ዕድል ሆኖ የኢሚግሬሽን እና የቤተሰብ ፍርድ ቤት የፍርድ ክርክር ሂደቶች ብዙውን ጊዜ ወራትን፣ ወይም በአንዳንድ ሁኔታዎች ዓመታትን ሊፈጁ ይችሉ ይሆናል። እርስዎ ከአገር እንዲወጡ ከተባረሩ፣ የእርስዎ ልጆች በክብካቤው ሰጪ ሥር ለረዥም ጊዜ መቆየት ሊያስፈልጋቸው ይችል ይሆናል። የእርስዎ ክብካቤ ሰጪ የእርስዎን ልጆች ለረዥም ጊዜ ሊይዛቸው ይችላል በሚችል እሳቤ ዕቅድን ማውጣት የተሻለ ነው። የሚያሳዝነው ነገር፣ ክብካቤ ሰጪዎች ልጆቹን እንዲይዙ የሚታሰበው እና ዕቅድ የሚወጣው ለጥቂት ሳምንታት ብቻ ስለሚሆን እና በዚህም ምክንያት ከዚህ ጊዜ በላይ ሊይዟቸው ስለማይችሉ አብዛኛዎቹ ሕፃናት መጨረሻቸው ለማደጎ ክብካቤ መሰጠት ይሆናል።

የእርስዎን ልጆች ለመንከባከብ ምን ያክል ወጪን ይጠይቃል?

በእያንዳንዱ ቀን የእርስዎ ልጆች ምግብ፣ መጠለያ፣ መጓጓዣ፣ የሕክምና እንክብካቤ፣ እና እንደ መጽሐፍት እና ልብስ የመሳሰሉ የግል ነገሮችን ማግኘት ያስፈልጋቸዋል። የሚሾሙት ክብካቤ ሰጪ የመንግሥት ድጋፍን ለማግኘት ይችሉ ይሆናል (እና እንዲሁም ልጆችዎ ከዚህ ቀደም የመድን ዋስትና ከሌላቸው የጤና መድንም ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል)። ካልሆነ ግን፣ እኚህ የሚሾሙት ክብካቤ ሰጪ ለእርስዎ ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ለማድረግ የገንዘብ አቅሙ አላቸው? እርስዎ በ ICE ድንገት ከተያዙ እኚህ የሚሾሙት ክብካቤ ሰጪ ለእርስዎ ልጆች ክብካቤ ሲያደርጉ ማገዝ እንዲቻል ገንዘብ እና ግብዓቶችን ከአሁኑ በጎን ለይተው ሊያስቀምጡላቸው እርስዎ ይችላሉን? ለእርስዎ ልጆች ፍላጎቶች የገንዘብ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ እንደ ዘመድ፣ ጓደኛ ወይም ፓስተር የመሳሰሉ ሌሎች ሰዎች አሉዎት?

በቤተሰቡ ውስጥ ሌላ ማን ሰው አለ?

በእርስዎ የሚሾሙት ክብካቤ ሰጪ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሁሉንም ሰዎች እርስዎ ያውቁዋቸዋልን? ከእርስዎ ልጆች ጋር በየቀኑ የሚገናኙ ሰዎች እነማን መሆናቸውን አውቀው ምቾት ሊሰማዎት ይገባል። በእርስዎ ጉዳይ ላይ የሕፃን እና ቤተሰብ አገልግሎቶች ኤጀንሲ [Child and Family Services Agency (CFSA)] እጁ ካለበት በቤተሰቡ ውስጥ ያለ ዐዋቂ ሰው የወንጀል ሪኮርድ ካለበት ወይም ከዚህ ቀደም በሕፃን ላይ ጥቃት በማድረስ ወይም በልጅ ቸልተኝነት ዙሪያ ክስ ካለበት የእርስዎ ልጆች በዚያ ቤተሰብ ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ላይፈቀድላቸው ይችላል።

በቂ የሆነ ክትትልና ቁጥጥር ይደረግባቸዋልን?

የሚሾሙት ክብካቤ ሰጪ ሥራ ይሠራሉ? እሳቸው ሥራ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ማን የእርስዎን ልጆች እንደሚይዝ ይወቁ። የእርስዎ ልጆች ትምህርት ቤት ወይም በሕፃናት መዋያ የሚውሉ ከሆነ፣ ጠዋት ላይ ማን ወደዚያ ያደርሳቸዋል እንዲሁም በቀኑ መጨረሻ ላይ ማን ይቀበላቸዋል? የእርስዎ ልጆች ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው ማረጋገጥ ይኖርብዎታል። የክብካቤ ሰጪው ቤት በእርስዎ ልጆች የዕድሜ ክልል ላሉ ልጆች ደኅንነት አስተማማኝ መሆኑን ያረጋግጡ።

የእርስዎ ክብካቤ ሰጪ ከእርስዎ ልጆች ማናቸውም ሊኖራቸው የሚችል ልዩ የሕክምና ነክ ፍላጎት ምን እንደሆነ ያውቃሉን?

ለሚሾሙት የክብካቤ ሰጪ የእርስዎን ልጆች ዶክተር ወይም የሕክምና አገልግሎት ሰጪ መገኛ አድራሻ እንዲሁም የልጆችዎን የእያንዳንዳቸውን የ Medicaid ወይም ሌላ የኢንሹራንስ ካርዶችን ፎቶኮፒ መስጠት ይኖርብዎታል። ከእርስዎ ልጆች መካከል ማናቸውም መድኃኒት የሚወስዱ ከሆነ፣ ክብካቤ ሰጪው መድኃኒቱ ለምን እንደሚወሰድ ምክንያቱን፣ የት መቀመጥ እንዳለበት፣ በምን ያክል ጊዜ ልዩነት እንደሚወሰድ ማወቅ የሚኖርባቸው ሲሆን በተጨማሪ መድኃኒቶቹ የት እንደሚገዙ መረጃ ሊሰጣቸው ይገባል።

የእርስዎ ክብካቤ ሰጪ የእርስዎ ልጆች የትኛው ትምህርት ቤት እንደሚማሩ ያውቃሉ?

የእርስዎን ልጆች በዚያው ትምህርት ቤት ለማቆየት ይችላሉ? በዲሲ ውስጥ ክብካቤው ሰጪው ቀስ በቀስ በስተመጨረሻ ልጆቹን እየተማሩ ካሉበት ትምህርት ቤት አስወጥተው ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ማስመዝገብ ከፈለጉ ወይም በክብካቤው ሰጪ ሥር እያሉ ከልጆችዎ መሃከል አንዱ ወይም አንዷ ወደ መካከለኛ ደረጃ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተሸጋገሩ የልጆቹ ተቀዳሚ ክብካቤ ሰጪ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ ያስፈልጋቸዋል።

የእርስዎ ክብካቤ ሰጪ የእርስዎ ልጆች የትኛው ትምህርት ቤት እንደሚማሩ ያውቃሉ?

የእርስዎን ልጆች በዚያው ትምህርት ቤት ለማቆየት ይችላሉ? በዲሲ ውስጥ ክብካቤው ሰጪው ቀስ በቀስ በስተመጨረሻ ልጆቹን እየተማሩ ካሉበት ትምህርት ቤት አስወጥተው ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ማስመዝገብ ከፈለጉ ወይም በክብካቤው ሰጪ ሥር እያሉ ከልጆችዎ መሃከል አንዱ ወይም አንዷ ወደ መካከለኛ ደረጃ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተሸጋገሩ የልጆቹ ተቀዳሚ ክብካቤ ሰጪ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ ያስፈልጋቸዋል። የእርስዎን ልጆች ከትምህርት ቤት ወይም ከሕፃናት መዋያው የእርስዎን ልጆች እንዲወስዱ ከሚፈቀድላቸው ሰዎች ዝርዝር ላይ የእርስዎን የሚሾመውን ክብካቤ ሰጪ ስም እና የድንገተኛ ጊዜ ተጠባባቂ ግለሰብን ስም እንደጠቀሱ ያረጋግጡ።

የእኔ ክብካቤ ሰጪ የኢሚግሬሽን ወረቀቶችን መያዝ አለባቸው?

የእርስዎ ክብካቤ ሰጪ ለእርስዎ ልጆች በዲሲ ውስጥ ክብካቤ ለመስጠት እንዲችሉ ሕጋዊ አቋም እንዲኖራቸው አይገደዱም። ሆኖም ግን ያስታውሱ፣ ግቡ የእርስዎ ልጆች መረጋጋት እና ደኅንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ማድረግ ነው እና ሁልጊዜ ሕጋዊ አቋም የሌላቸው ሰው ዩናይትድ ስቴትስን ለቀው እንዲወጡ ሊገደዱ የሚችሉባቸው አደጋዎች ይኖራሉ፤ በመሆኑም ክብካቤ ሰጪው ሕጋዊ አቋም እንዲኖራቸው ይመከራል።

የውክልና ሥልጣን አሰጣጥ ዝግጅቶች:

የልጅ ሞግዚትነት የውክልና ሥልጣን

ልጅን የማሳደግ የውክልና ሥልጣን [Custodial Power of Attorney (CPOA)] ሌላ ግለሰብን ለእርስዎ ልጆች ወሳኝነት ያላቸውን ውሳኔዎች እንዲሰጡ ጊዜያዊ ሥልጣን የሚሰጥ ሰነድ ነው። እርስዎ በ ICE ድንገት ከተያዙ የእርስዎ ልጆች በማደጎ ክብካቤ ሥር እንዳይወድቁ ለመከላከል በእርስዎ ለሚሾሙት የክብካቤ ሰጪ የልጅን ማሳደግ የውክልና ሥልጣን እንዲያዘጋጁላቸው ይመከራሉ። የልጅን ማሳደግ የውክልና ሥልጣን በእርስዎ እና በሌላ ግለሰብ መካከል የሚደረግ የግል ስምምነት ሲሆን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ግን አይደለም። የልጆቹ እናት እና አባት ሁለቱም ከልጆቹ ጋር ቅርብ የሆነ ግንኙነት ያላቸው ከሆኑ ሁለቱም ወላጆች CPOA ላይ መፈረም ይኖርባቸዋል።

እንደ ወላጅ፣ በማናቸውም ጊዜ ይህን CPOA መሰረዝ ወይም መሻር ይችላሉ። የ CPOA ሰነድ የእርስዎን ክብካቤ ሰጪ ለእርስዎ ልጆች በሁሉም የወላጅ ውሳኔን በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ አጠቃላይ ሥልጣንን ሊሰጣቸው ይችላል ወይም ለእሳቸው እንዲወስኑ ጊዜያዊ ሥልጣን ሊሰጡባቸው የሚፈልጉዋቸውን የተወሰኑ ነገሮች መርጠው ሊዘረዝሩ ይችላሉ። ከመቼ ጊዜ ጀምሮ በሥራ ላይ መዋል እንዲጀምር (ለምሳሌ እርስዎ ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ) እና መቼ እንዲቋረጥ (ለምሳሌ እርስዎ ከእስር ሲለቀቁ) እንደሚፈልጉ ሊያካትቱ ይችላሉ። ምንም እንኳን CPOA በውልና ማስረጃ ማረጋገጥ የሚያስፈልገው ባይሆንም በውልና ማስረጃ እንዲረጋገጥ ማድረጉ ጥሩ ሐሳብ ነው። ሁለት ኦርጂናል ሰነዶችን መሙላት አለብዎት፦ አንዱን ቅጂ ለእርስዎ ክብካቤ ሰጪ ይስጡ እና አንዱን ለራስዎ ያስቀሩት። እንግሊዝኛ ለማንበብ የሚቸገሩ ከሆኑ በተጨማሪ ሁለት ኦርጂናል ሰነዶችን በራስዎ አፍ መፍቻ ቋንቋ ሊይዙ ይገባል (ከሁለቱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከተዘጋጁት በተጨማሪ)። የሚቻል ከሆነ ለእርስዎ እና ለእርስዎ ተሿሚ ክብካቤ ሰጪ ኤሌክትሮኒካዊ ቅጂዎችንም በተጨማሪ ያዘጋጁ። ናሙና የልጅ ሞግዚትነት የውክልና ሥልጣን መስጫ እና ናሙና የልጅ ሞግዚትነት የውክልና ሥልጣን መሻሪያ ከተዛምጅነት ያላቸው መመሪያዎች በዚህ የጽሑፍ መመሪያ ክፍል 3 ላይ ተካተዋል።

የገንዘብ ነክ ጉዳዮች የውክልና ሥልጣን

የገንዘብ ነክ ጉዳዮች የውክልና ሥልጣን [Financial Power of Attorney (FPOA)] ሌላ ግለሰብን በእርስዎ ንብረት እና ሃብቶች ላይ ወሳኝነት ያላቸውን ውሳኔዎች እንዲሰጡ ጊዜያዊ ሥልጣን የሚሰጥ ሰነድ ነው። ሌላ የሚታመን ሰው ወደ የእርስዎ የባንክ ሒሳቦች እና ሌላ ንብረት መዳረሻ እንዳለው እንዲሁም የእርስዎ ልጆች የሚያስፈልጋቸውን የገንዘብ ድጋፍ ማግኘታቸውን፣ የቤት ኪራይ እና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያ መጠየቂያ ደረሰኞች መከፈላቸውን እና እርስዎ ከታሰሩ ሌሎች ገንዘብ ነክ ግዴታዎችዎት መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ሰው መኖሩን ለማረጋገጥ የገንዘብ ነክ ጉዳዮች የውክልና ሥልጣንን ማዘጋጀት ይኖርብዎታል።

የገንዘብ ነክ ጉዳዮች የውክልና ሥልጣን እንዲኖረው ሥልጣን የሚሰጡት ሰው ማናቸውም የታመነ ለአካለ መጠን የደረሰ ትልቅ ሰው ሊሆን ይችላል። ለእርስዎ ልጆች እንደ ክብካቤ ሰጪ ሆኖ እንዲያገለግል የሾሙት ሰው የገንዘብ ነክ ጉዳዮች የውክልና ሥልጣንንም እንዲሸፍን ሊመርጡት ይችላሉ ሆኖም ግን የግድ ይህ ሰው መሆን የለበትም። የሆነው ሆኖ፣ ከእርስዎ ሹም የክብካቤ ሰጪ ሌላ ሰውን ከመረጡ፣ የሚዘጋጀው FPOA ለልጆቹ እንክብካቤ የገንዘብ ነክ ኃላፊነትን መውሰድን የሚያካትቱ መመሪያዎችን መያዙን ያረጋግጡ።

የገንዘብ ነክ ጉዳዮች የውክልና ሥልጣን በእርስዎ እና በሌላ ግለሰብ መካከል የሚደረግ የግል ስምምነት ሲሆን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አይደለም። ግለሰቡ ምን የገንዘብ ሒሳቦችን እና ንብረቶችን ለጊዜው መድረስ እንዲችል እና በየትኞቹ ላይ ውሳኔ የመስጠት መብት እንዲኖረው መፍቀድ እንደሚፈልጉ በግልጽ ጠቅሰው ማስቀመጥ ይችላሉ። በተጨማሪ በማናቸውም ጊዜ FPOAን የመሰረዝ ወይም የመሻር ሥልጣን ያልዎት ሲሆን ልክ እንደ የልጅ ሞግዚትነት የውክልና ሥልጣን ሁሉ መቼ ውክልናው በሥራ ላይ እንደሚውል እና መቼ እንዲያቆም ማድረግ እንደሚፈልጉ መጥቀስ ይችላሉ። የእርስዎ ባንክ ወደ የእርስዎ ባንክ ሒሳብ ለሌላ ሰው መዳረሻን ለመስጠት መሙላት የሚያስፈልግዎት ተጨማሪ ቅጾች ሊኖሩት ይችሉ ይሆናል፤ በሚቀጥለው ጊዜ ወደ የእርስዎ ባንክ ሲሄዱ ይህንኑ መጠየቅ አለብዎት። ናሙና የገንዘብ ነክ ጉዳዮች የውክልና ሥልጣን መስጫ እና ናሙና የገንዘብነክ ጉዳዮች የውክልና ሥልጣን መሻሪያ በዚህ የጽሑፍ መመሪያ ክፍል 3 ላይ ተካተዋል።

FPOA በሕዝብ አዋዋይ ትክክለኛነቱ መረጋገጥ አለበት። ሁለት ኦርጂናል ሰነዶችን መሙላት አለብዎት፦ በእርስዎ ገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ ጊዜያዊ መዳረሻ እና የውሳኔ ሰጭነት ሥልጣን እንዲኖረው ለሾሙት ሰው አንዱን ቅጂ ይስጡት እና ቀሪውን አንዱን ደግሞ ለራስዎ ደኅንነቱ በሚያስተማምን ቦታ ላይ ያስቀምጡት። እንግሊዝኛ ለማንበብ የሚቸገሩ ከሆኑ በተጨማሪ ሁለት ኦርጂናል ሰነዶችን በራስዎ አፍ መፍቻ ቋንቋ ሊይዙ ይገባል (ከሁለቱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከተዘጋጁት በተጨማሪ)። የሚቻል ከሆነ ለራስዎ እና የእርስዎ የገንዘብ ነክ ጉዳዮች የውክልና ሥልጣን ላለው ግለሰብ የኤሌክትሮኒክ ስሪት ቅጂ ሊይዙ ይገባል።

የድንገተኛ አደጋ ተጠሪ ወረቀትን ማዘጋጀት

አብዛኛዎቹ ወላጆች ድንገት በ ICE ሳይታሰብ በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ስለሆኑ የእርስዎ ልጆች፣ የእርስዎ ሹም ክብካቤ ሰጪ፣ እና ሌላ ማናቸውም ለእርስዎ ልጆች ክብካቤ ሊሰጥ የሚችል የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ በኪስ ቦርሳቸው ውስጥ፣ በእጅ ቦርሳቸው ውስጥ ወይም በትምህርት ቤት ቦርሳቸው ውስጥ የሚይዙትን የድንገተኛ አደጋ ተጠሪ ወረቀትን አዘጋጅቶ መክተት ወይም መስጠት ጥሩ ሐሳብ ነው። ወረቀቱ የእርስዎን ልጆች ትምህርት ቤት ስም፣ አድራሻ እና ስልክ ቊጥር እንዲሁም የእርስዎ ልጆች በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት ወይም በሕፃናት መዋያ ውስጥ በሆነ ጊዜ ላይ ከሌሉ ሊኖሩ የሚችሉባቸውን ቦታዎች ስም፣ አድራሻ እና የስልክ ቊጥር ማካተት አለበት።

አስፈላጊ ከሆነ እርስ በርስ መልእክት መለዋወጥ እና ቅንጅትን መፍጠር እንዲችሉ ወረቀቱ በተጨማሪ እርስዎ የድንገተኛ ተጠሪ ወረቀትን ሊሰጧቸው ያሰቧቸውን ሌሎች ሁሉንም ግለሰቦች ስሞች እና ስልክ ቊጥሮች በላዩ ላይ የያዘ መሆን አለበት። በወረቀቱ ላይ የተዘረዘረ ሁሉም ሰው እርስዎ በ ICE ከተያዙ ለእርስዎ ልጆች እርስዎ ስላልዎት የክብካቤ ዕቅዶች ማወቅ ይኖርበታል። የድንገተኛ አደጋ ተጠሪ ወረቀት ናሙና በዚህ መመሪያ ጽሑፍ ክፍል 3 ላይ ተካቷል።

የእርስዎን ልጆች ከትምህርት ቤት ወይም ከሕፃናት መዋያው የእርስዎን ልጆች እንዲወስዱ ከሚፈቀድላቸው ሰዎች ዝርዝር ላይ የእርስዎን ተሿሚ ክብካቤ ሰጪ እና የድንገተኛ አደጋ ተጠሪ (እንዲሁም ከፈለጉ የሌሎች እንደ ተጨማሪ ተጠባባቂ ማካተት የሚፈልጉዋቸውን ሰዎች)መገኛ አድራሻ ከነስማቸው እንደጻፉ ያረጋግጡ።

ሕጋዊ የሆነ የኢሚግሬሽን አቋም ከሌላቸው ሰዎች የመገኛ አድራሻን በእጅዎ እንደያዙ እርስዎ በ ICE በቁጥጥር እንዳያዙ ስጋት ከገባዎት፣ ሕጋዊ አቋም ላለው ይህ መረጃን በደኅንነቱ አስተማማኝ ቦታ ሊያስቀምጥ የሚችል እና በድንገተኛ አደጋ ተጠሪ ወረቀቱ ላይ ያሉ ሰዎችን ማግኘት ለሚችል ለሌላ ግለሰብ የስልክ ጥሪ ለማድረግ ዕቅድ ሊያዘጋጁ ይችላሉ።

ሁሉንም አስፈላጊ ሰነዶች በአንድ ቦታ ሸክፎ ማስቀመጥ

ሁሉንም አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች በፋይል ወይም በፕላስቲክ ከረጢት ውስጥ አድርገው ደኅንነቱ በተጠበቀ ቦታ ላይ ማስቀመጥ ይኖርብዎታል። ምንም እንኳ አንዳንድ ወይም ሁሉም የእርስዎ ልጆች መረጃ ተመሳሳይ እንኳ ሊሆን ቢችልም የእያንዳንዱን አስፈላጊ ሰነድ ፎቶኮፒ ጨምሮ ለያንዳንዱ የእርስዎ ልጅ የተለያየ ራሱን የቻለ ፋይል ሊያዘጋጁ ይገባል። መሰባሰብ ያለባቸው አስፈላጊ ሰነዶች ዝርዝር በዚህ መመሪያ ጽሑፍ ክፍል 3 ላይ ማግኘት ይቻላል።

ምንም እንኳ የተወለዱት ከዩኤስ አሜሪካ ውጭ ቢሆንም ለያንዳንዱ የእርስዎ ልጆች የልደት ምስክር ወረቀቶች እንዳልዎት ያረጋግጡ። የእርስዎ ልጆች ፓስፖርት ከሌላቸው፣ ለእያንዳንዱ የእርስዎ ልጅ ፓስፖርት ሊያዘጋጁለት ይገባል። የእርስዎ ልጆች በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተወለዱ ከሆኑ እንዴት ፓስፖርት ማግኘት እንደሚችሉ www.travel.state.gov ላይ መረጃ ማግኘት ይችላሉ ወይም በአንዳንድ የአሜሪካ ፖስታ ቤቶች [US Post Offices] አዲስ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ። የእርስዎ ልጆች በሌላ አገር ውስጥ የተወለዱ ከሆኑ፣ ፓስፖርት ስለሚያገኙበት መንገድ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የእርስዎን ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ያነጋግሩ። የአንዳንድ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች የመገኛ አድራሻ መረጃ በዚህ መመሪያ ጽሑፍ ክፍል 3 ውስጥ ሊገኝ ይችላል። የእርስዎ ልጆች ፓስፖርት ከሌላቸው፣ በተቻለ ፍጥነት ፓስፖርት ያውጡላቸው።

የእርስዎ ተሿሚ ክብካቤ ሰጪ ወይም የእርስዎን ተሿሚ ክብካቤ ሰጪ አስፈላጊ የሆኑት ሰነዶችን ዝግጁ ሆነው በእጃቸው ያልያዙ ከሆኑ እና እርስዎ ድንገት በ ICE ቢያዙ ለእሳቸው መስጠት እንዲችሉ ሌሎች በእርስዎ ቤት ውስጥ ያሉ እንደ ትልቅ ልጅ የመሳሰሉ ሰዎች ሰነድ አቃፊው የት እንዳለ በትክክል ማወቅ አለባቸው።

Last Review and Update: Mar 16, 2017
Volver arriba