Website Survey

ልጅን የማሳደግ (የመጠበቅ) መብት እና የጉብኝት ሁኔታ በዲ.ሲ።

Authored By: D.C. Bar Pro Bono Center

Information

Note: this text was produced using OCR technology, so it may contain errors. Please downloadable the document above to read the original.

ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት ስለ ልጅ እና ልጅ የት እንደሚኖር የመወሰን መብት ለመስጠት የተመሠረተ ህጋዊ ዝግጅት ነው፡፡ ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት የሚሰጠው እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች ብቻ ነው፡፡ በዳኛ የሚታዘዙት ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ ህጋዊ እና የመኖሪያ ሀላፊነት ናቸው፡፡

ህጋዊ ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት ማለት ምን ማለት ነው?

ህጋዊ ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት ማለት ለልጁ ህጋዊ ሀላፊነት መውሰድ ማለት ነው፡፡ ይኸውም የልጁን ጤንነት፣ የትምህርትና ጠቅላላ ደህንነት ያካትታል፡፡ የጋራ ህጋዊ ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት (ወላጆች ለልጃቸው ጉዳይ በጋራ መወሰን) ወይም የተናጠል ህጋዊ ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት (አንዱ ወላጅ ብቻ ስለ ልጅ መወሰን) መብት ሊኖርዎት ይቻላል፡፡

አካላዊ ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት ማለት ምን ማለት ነው?

አካላዊ ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት ማለት የልጅን የመኖሪያ ሁኔታ መወሰን ማለት ነው፡፡ ይኸውም የት እንደሚኖር፣ ምን እንደሚመገብ እና የት እንደሚተኛ ያካትታል፡፡ የልጁን የመኖሪያ ቦታ ወይም የመጎብኘት የጊዜ ሰሌዳን ያካትታል፡፡ የጋራ አካላዊ የማሳደግ ሀላፊነት (ልጅ ከእያንዳንዱ ወላጅ ጋር ለጥቂት ጊዜ አብሮ መኖር) ወይም የተናጠል አካላዊ የማሳደግ ሀላፊነት (ልጅ አብዛኛውን ጊዜ ከአንዱ ቤተሰብ ጋር መኖር) መብት ሊኖርዎት ይቻላል፡፡

ልጆቼን ለማየት ብቻ ብፈልግስ?

ጉብኝት (አንዳንድ ጊዜ መገናኘት ይባላል) ልጅዎ ከሌላው ወላጅ ጋር ሲኖር ልጅዎን የማየትና የመገናኘት መብትዎ ነው፡፡ እርስዎና ሌላው ወላጅ በሚመቻችሁ መንገድ የጉብኝቱን ጊዜ መወሰን ትችላላችሁ (ለምሳሌ በሳምንት አንድ ቀን ከቀትር በኋላ፣ ወይም በተፈራረቁ ቅዳሜ እና ዕሁድ አዳር፣ ወይም በበጋ ወራት ለብዙ ሳምንታት ማቆየት)፡፡ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካስፈለገ ማመልከት ይችላሉ፡፡

የማሳደግ እና የጉብኝቱን ሁኔታ ስለማመቻቸት የሚወስነው ማን ነው?

የፍ/ቤት ትዕዛዝ ከሌለ ሁለቱም ወላጆች ህጋዊ እና አካላዊ የሆነ የማሳደግ ሀላፊነት መብት አላቸው፡፡ ወላጆች በማንኛውም የማሳደግ እና የጉብኝት ጉዳይ መስማማት እና ያመኑበትን ማድረግ ይችላሉ፡፡

መስማማት ባንችል ምን ይሆናል?

የቤተሰብ ፍርድ ቤት በMulti-Door የአለመግባባት አስወጋጅ ክፍል (202-879-1549) በእርስዎና እና በሌላው ወላጅ ስምምነት እንዲፈጠር የሰለጠኑ የነጻ አማካሪዎች ያቀርባል፡፡ የፍርድ ቤት ጉዳይ ባይኖርዎትም በMulti-Door መጠቀም ይችላሉ፡፡

የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያስፈልገኛል?

የፍርድ ቤት የልጅ ማሳደግ ሀላፊነት ትዕዛዝ የሚያስፈልገው በእርስዎ እና በሌላው ወላጅ መካከል አለመስማማት ሲፈጠር፣ የእርስዎን የማሳደግ መብት ተቃዋሚ ካለ ወይም እነዚህን የመሳሰሉ አለመስማማቶችን ወይም ቅዋሜዎችን ለወደፊቱ ለማስወገድ ነው፡፡

በዲሲ ለልጅ ማሳደግ ሀላፊነት ማመልከቻ ማቅረብ እችላለሁ?

የዲሲ ፍርድ ቤት ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት ጉዳይ ላይ ለመወሰን በእርስዎ ጉዳይ ላይ የመወሰን ሥልጣን ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህም ሥልጣን ይባላል፡፡ ምንም እንኳን ዲሲ ሥልጣን ሊኖረው የሚችልበት ብዙ መንገዶች ቢኖሩትም በጣም የተለመደው ግን በአሁኑ ጊዜ ወይም በቅርብ ጊዜ የልጁ የመኖሪያ ግዛት ዲሲ ከሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት፡- ወይም ልጁ በዲሲ ነዋሪ የነበረና ከስድስት ወር ያነሰ ከዲሲ ውጭ ከኖረ እና ልጁ ዲሲ ውስጥ አሁን ነዋሪ ባይሆንም ወላጅ ወይም እንደወላጅ የሚጠብቀው ሰው ዲሲ ውስጥ ነዋሪ ከሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት፡-

 • ማመልከቻው ከመግባቱ ከስድስት ወር በፊት ልጁ በዲሲ ይኖር ከነበረ፣
 • ወይም ልጁ በዲሲ ነዋሪ የነበረና ከስድስት ወር ያነሰ ከዲሲ ውጭ ከኖረ እና ልጁ ዲሲ ውስጥ አሁን ነዋሪ ባይሆንም ወላጅ ወይም እንደወላጅ የሚጠብቀው ሰው ዲሲ ውስጥ ነዋሪ ከሆነ ነው፡፡

የልጅ ማሳደግ ሀላፊነት ወይም መጎብኘት ክርክር አንዴት መጀመር እችላለሁ?

ክሱን ለመጀመር የማሳደግ ሀላፊነት ወይም የመጎብኘት ማመልከቻ ለፍርድ ቤቱ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ክሱ ከተመሰረተ በኋላ የክሱን ማመልከቻ ግልባጭ ለተከሳሹ መስጠት አለበት። ትክክለኛውን አስፈላጊ የህግ ጥያቄዎችን ለማሟላት የዲሲ ፍርድ ቤት የፍቺ አና የማሳደግ ሀላፊነት ክርክር አምድ ሥር የተጻፈውን መግለጫ ይመልከቱ።

አንድ ግለሰብ አርስዎ ላይ ክስ መስርቶብዎት ከሆነ ተከሣሽ ነዎት፡፡ በህጉ መሠረት የማሳደግ ሀላፊነት እና የመጎብኘት ክስ ግልባጭ በደረሰዎ በ20 ቀናት ጊዜ ውስጥ መልስ የመስጠት ግዴታ አለብዎት። የክሱን መልስ ለፍርድ ቤቱ ከሰጡ በኋላ ለከሳሹ ግልባጭ የመስጠት ግዴታ አለብዎት። የመጀመሪያ ክስ ከተመሰረተ በኋላ በሂደት ላይ ያሉ የፍርድ ቤት መዝገቦች አምድ ሥር በፍቺ አና የማሳደግ ሀላፊነት ጉዳይ ያለውን መግለጫ አንደገና ይመልከቱ።

ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ አስፈላጊውን የፍርድ አቤቱታ በWWW.dcbar. org/pleadings ወይም ከዲሲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቤተሰብ ፍርድ ቤት መካከለኛ የመመዝገቢያ ማዕከል በ540 Indiana Avenue NW, የክፍል ቁጥር JM-540 ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት 8:30 am አስከ 5.00 pm ማግኘት ይቻላል።

እኔና ሌላው ወላጅ ባንስማማ ዳኛው ምን ያደርጋሉ?

ዳኛው ጉዳዩ በMulti-Door ፕሮግራም አማካይነት በአርቅ አንዲፈታ እንዲሞከሩ ያመቻቻሉ።

በአርቅ መስማማት ካልተቻለ የማሳደግ ሀላፊነት ችሎት ይካሄዳል። በዚህ ጊዜ አያንዳንዱ ወላጅ የልጁን ፍላጎት የተሻለ የሚያሟላውን ያቀርባሉ። የሁለቱም ሀሳብ ከተሰማ በኋላ ከቀረበው ሀሳብ በመነሳት ለልጁ ጠቀሜታ ያለውን ዳኛው ይወስናል።

ዳኛው የማሳደግ ሀላፊነትን እንዴት ይወስናሉ?

ዳኛው የልጁን ላጎት የበለጠ የሚያሟላ ውሳኔ መስጠት አለባቸው፡፡ ህጉ ሁለቱ ወላጆች በጋራ የተሳተፉበት የማሳደግ ሀላፊነት የልጁን ፍላጎት ያሟላል ብሎ ይገምታል፡፡ ይሁን እንጂ ዳኛው የጋራ የማሳደግ ሀላፊነት በልጁ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ካልሆነ፣ ልጁ በደል ተፈጽሞበት ከሆነ፣ ልጁን አፍኖ የመውሰድ ፍላጎት በወላጆች ከታየ ወይም የቤት ውስጥ ብጥብጥ ከተነሳ የተናጠል የማሳደግ ሀላፊነት ውሳኔ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡

ህጉ “የልጁን የተሻለ ፍላጎት ሲል ምን ማለት ነው”?

የልጁን የተሻለ ፍላጎት ለመወሰን ዳኛው ማንኛውንም ለልጁ የተሻለውን ምቹ ሁኔታ ግምት ውስጥ የማስገባት ግዴታ አለባቸው፡፡ በህጉ መሠረት ዳኛው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ |

 • የልጁን ፍላጎት፣
 • የወላጆችን ፍላጎት፣
 • ልጅ ከወላጆች፣ ከወንድሞች፣ ከእህቶች፣ ወይም ከሌሎችም ጋር ያለው/ያላት ግንኙነት፣
 • ልጅ ለቤቱ/ለቤቷ ለትምህርት ቤት እና ለማህበረሰቡ የምትሰጠው/የሚሰጠው ትኩረት ወይም ግምት፣
 • የተሳታፊዎችን የአእምሮአዊና የአካላዊ ጤንነት፣
 • የውስጥ ብጥብጥ ስለመኖሩ ማረጋገጫ፣
 • የወላጆች ግንኙነት እና በልጃቸው ጉዳይ ላይ የጋራ ውሳኔ የመወሰን ችሎታ፣
 • የማሳደግ ሀላፊነትን ለመጋራት የወላጆች ፈቃደኝነት፣
 • እያንዳንዱ ወላጅ በልጁ ህይወት ያሳየው ቅድሚያ ተሳትፎ፣
 • የልጁን ማህበራዊና የትምህርት ህይወት የማቃወስ ሁኔታ፣
 • በልጁ ወላጆች መኖሪያ ቤት መካከል ያለው ርቀት፣
 • የወላጆች የሥራ ጫና ሁኔታ፣
 • የልጆች ብዛት እና እድሜ፣
 • የእያንዳንዱ ወላጅ ጥያቄ ቅንነት ወይም ልባዊነት፣
 • የጋራ የማሳደግ ሀላፊነትን ለመውሰድ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የወላጆች ችሎታ ወይም አቅም፣
 • ጊዜያዊ እርዳታ በሚፈልጉ ቤተሰቦች ፕሮግራም፣ በሥራ መርሀግብር፣ በሥራ፣ በሀላፊነት ላይ እና በህክምና እርዳታ ላይ ያለ ተፅዕኖ፣
 • የወላጆች ጥቅማ ጥቅም።

እናት ወይም አባት ያልሆነ ሌላ ሰው (እንደ አያት፣ አጎት፣ እህት፣ ወይም ጓደኛ) የማሳደግ ሀላፊነት ማመልከቻ ማቅረብ ይችላል?

አንዳንድ ጊዜ በተወሰነ አጋጣሚ ከእናት ወይም ከአባት ሌላ ሶስተኛ ሰው ልጅን የማሳደግ ሀላፊነት ማመልከቻ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሊደርሱ የሚችሉት ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፡፡ (ሀ) ሶስተኛው ወገን ከወላጆች ጋር ልጁን የመጠበቅ ስምምነት ለተወሰኑ ጊዜያት ባለፉት ሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ ከነበረው፣ (ላ) ሶስተኛው ወገን ባለፉት 6 ወራት ጊዜ ውስጥ 4 ወር አብሮ በመኖር ልጁን እንደወላጅ ሲንከባከብ የቆየ ከሆነ፣ (ሐ) በአሁኑ ወቅት ልጁ ከሶስተኛ ወገን ጋር አብሮ የሚኖር ከሆነ እና ልጁን ከጉዳት ለመጠበቅ ሲባል የማሳደግ ሀላፊነት ለሦስተኛ ወገን መስጠት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ፣ ዳኛው፡ በቂ ነው ብለው ባመኑበት ምክንያት የማሳደግ ሀላፊነት እናት ወይም አባት ላልሆነ ለሶስተኛ ወገን መስጠትን ያካትታሉ፡፡

ልጅ የማሳደግ ሀላፊነት ወይም የመጠበቅ ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ መቀየር ይቻላል?

ፍርድ ቤቱ ልጅ የማሳደግ ወይም የመጎብኘት ሀላፊነት ዕዛዙን ሁል ጊዜ መለወጥ ይችላል፡፡ ይህም የሚደረገው የማሳደግ ወይም የመጎብኘት ሀላፊነት ማሻሻያ ጥያቄ በማመልከቻ ሲቀርብ ነው፡፡ ማመልከቻውን ያቀረበው ሰው አዲሱ ማሻሻያ በልጁ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ እና በመጀመሪያው ውሳኔ ላይ ጉልህ ለውጦች መከሰታቸውን ለዳኛው የማስረዳት እና

የማሳመን ግዴታ አለበት፡፡

ለበለጠ መረጃ:- የቤተሰብ እራስ አገዝ ማእከል በዲሲ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 500 Indiana Avenue, NW ክፍል ቁጥር JM-570 ያለቀጠሮ መጎብኘት ይቻላል፡፡ ማዕከሉ ስለጉዳዩ ያስረዳዎታል፡፡ አስፍላጊ ሰነዶችን አንዲሞሉና ወደ ሌላ የነፃ የህግ አገልግሎት ቦታዎች ይመራዎታል። ለበለጠ መረጃና ነፃ የህግ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ለማግኘት www.lawhelp.org/dc ይጎብኙ ወይም በDC Bar የህግ እርዳታ መስመር በ202-626-3499 የተቀዳ መልእክት አዳምጡ፡፡

የDO Bar Pro Bono ፕሮግራም የሚሰጠው አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው፡፡ የህግ አማካሪ አይደለም፡፡ ህግን በተመለከተ ምክር ከጠበቃ ያገኛሉ፡፡ ለተወሰነ ጉዳይ የህግ ምክር ከፈለጉ ወደ ጠበቃ ይሂዱ፡፡ የህግ መማሪያ ጽሁፎችን ወቅታዊ ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ህጎች በየጊዜው ይቀያየራሉ፡፡ ስለዚህ የDC Bar Pro Bono ፕሮግራም ለዚህ መረጃ ትክክለኛነት ዋስትና የለውም፡፡

This resource has been translated into Spanish, French, and Amharic thanks to the American Bar Endowment.
Last Review and Update: Oct 01, 2018
Back to top