የአገልግሎት ክፍያን ማስወገጃዎች በዲ.ሲ.
Contents
Information
በዲሲ የቤተሰብ ፍርድ ቤት የፍች፣ የልጅ ጥበቃ፣ ጉብኝት እና እገዛ ጉዳይ ለማስገባት $80 ያስከፍላል፡፡ ጉዳዩ ከተጀመረ በኋላ መልስ ወይም ቅራኔ ለማቅረብ $20 ይከፈላል፡፡ ለምስክሮች እና ለማስታወቂያዎች ሌላ ተጨማሪ ክፍያ ሊኖር ይችላል፡፡
የፍርድ ቤት ክፍያውን መክፈል አቅም ባይኖረኝስ?
ከመክፈል በፊት ጉዳይን ማስገባት የሚለውን ቅጽ በመሙላት ፍርድ ቤቱ ክፍያውን እንዲያስቀርልዎት መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ይህም in forma pauperis ወይም IFP ይባላል፡፡ አስፈላጊዎቹን የፍርድ ቤት ሰነዶች በድህረ ገጽ www.dcbar.org/pleadings ወይም በዲ.ሲ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቤተሰብ ፍርድ ቤት መካከለኛው መመዝገቢያ ማዕከል በ (500 Indiana Avenue NW, room JM-540) ከሰኞ እሰከ ዓርበ ከ8:30 a.m. to 5:00 p.m. ባለው ጊዜ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከመክፈል በፊት ጉዳይን ማስገባት የሚለውን ቅጽ መቼ መሙላት㗹እችላለሁ?
መጀመሪያ ጉዳይዎን ሲያስገቡ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ይሁን እንጂ መጀመሪያ ጊዜ ቢከፍሉም ተጨማሪውን ክፍያ ወይም ዋጋውን መክፈል ካልቻሉ በኋላ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ፍርድ ቤቱ ፈቃዱን የሚወስነው እንዴት ነው?
ቤተሰብዎንና እራስዎን ለመርዳት የሚከፈል ብዙ ወጭ እንዳለብዎት፣ ጥሩ ገቢ እንደሌለዎት ወይም ሥራ እንደማይሠሩ ለፍርድ ቤቱ ማሳየት አለብዎት፡፡
የመንግሥት እርዳታ እንደ ለችግረኛ ቤተሰቦች ጊዜያዊ እርዳታ (TANF) ወይም or Supplemental Security Income (SSI), የሚያገኙ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ክፍያውን ያስቀርልዎት ይሆናል፡፡ የመንግሥት እርዳታ ባያገኙም ገቢዎ የተወሰነ ከሆነ ክፍያ ሊቀርልዎት ይችል ይሆናል፡፡
ክፍያ እንዲቀርልኝ እንዴት አድርጌ ነው የምጠይቀው?
ክፍያ ከማድረግ በፊት ጉዳይን ማስገባት የሚለውን ቅጽ ለዳኛው ማሳየት ስለሚኖርብዎት ፍርድ ቤት የሚያስገቧቸውን ሰነዶች (ለምሳሌ ክስዎን) አስቀድመው ማዘጋጀት አለብዎት፡፡ ሰነዶቹን ከማስገባትዎ በፊት ክፍያው እንዲቀር የተፈቀደበትን ሰነድ ማግኘት አለብዎት፡፡ የክርክር ሰነዶችዎን ካስገቡ በኋላ ከሆነ ያገኙት ፍርድ ቤቱ የከፈሉትን ገንዘብ አይመልስልዎትም፡፡ የጠየቁበትን እና የክርክሩን ሰነዶች በፍርድ ቤቱ ውስጥ ላለው ዳኛ (ዲ.ሲ. ከፍተኛው ፍርድ ቤት የክፍል ቁጥር 4220) ውሰዱ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ዳኛው ወዲያውኑ ሊወስን ይችላል፡፡ ይሁን እንጅ ዳኛው በጣም ሥራ ከበዛበት ለሁለት ሰዓት ያህ መቆየት ይኖርብዎት ይሆናል፡፡
የገንዘቤን ሁኔታ በሰነድ ማሳየት ይኖርብኛል?
አብዛኛውን ጊዜ አይኖርብዎትም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ጥያቄውን ሲያስገቡ የሰጡት መረጃ በቂ ነው፡፡ አልፎ አልፎ ዳኛው ተጨማሪ መረጃ ወይም የጽሁፍ ሰነድ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡.
ቅጹን ለመሙላት ወይም ለበለጠ መረጃ የቤተሰብ ፍርድ ቤት እራስ አገዝ ማዕከል በ ዲ.ሲ. ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፦
አድራሻው 500 Indiana Avenue, NW, Room JM-570 መሄድ ይችላሉ፡፡. ማዕከሉ ከሰኞ እሰከ ዓርብ ከ8:00 a.m. እሰከ 5:30 p.m. ባለው ጊዜ ውስጥ ክፍት ነው፡፡ ማዕከሉ ምን ማድረግ እንዳለብዎት፣ ትክክለኛ ሰነዶችን የመሙላት እርዳታ እና ወደ የነጻ የሕግ አገልግሎቶች ይመራዎታል፡፡
ጥያቄዬ ከተፈቀደ በኋላ ምን ማድረግ አለብኝ?
ዳኛው ከፈቀደልዎት ክፍያ እንዲቀርልዎት የታዘዘበትን ከመክሰሻ ሰነዶችዎ ጋር ወደ የቤተሰብ ፍርድ ቤት መመዝገቢያ ማዕከል ይውሰዱት፡፡ የመመዝገቢያ ማዕከሉ ቀኑ የታተመበት ክፍያ እንዲቀርልዎት ያስገቡበትን ሰነድ እና የክስ ሰነዱን ግልባጭ እንዲሰጥዎት ይጠይቁ፡፡
ለፍርድ ቤት ማመልከቻ ባስገባሁ ቁጥር ክፍያ እንዲቀርልኝ መጠየቅ እችላለሁ?
አይችሉም፡፡ ፍርድ ቤቱ ክፍያ እንዲቀርልዎት አንዴ ከፈቀደልዎት በኋላ በእዛው ጉዳይ ላይ የፍርድ ቤት ሰነዶች ባስገቡ ቁጥር አዲሰ ፈቃድ መጠየቅ የለብዎትም፡፡ ለመካከለኛው መመዝገቢያ ማዕከል ክፍያው እንደተወገደልዎት ይንገሩ፡፡ የፍርድ ቤት መዝገቦችን አመሳክረው ያረጋግጣሉ፡፡ በሌላ በተለየ ጉዳይ አዲስ መዝገብ ቁጥር ካስወጡ አዲስ ፈቃድ መጠየቅ ይኖርብዎታል፡፡
ሌሎች ምን ዓይነት ክፍያዎች ሊወገዱ ይችላሉ?
ፍርድ ቤቱ ክፍያ ማስቀረቱን ከፈቀደልዎት ምስክር ሰጭዎችዎንም አለክፍያ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ለማሳተም ወይም በእርሰዎ ጉዳይ ማስታወቂያ ማውጣት ካስፈለገዎት ፍርድ ቤቱ በጋዜጣ ከማውጣት ይቅር ነጻ ማስታወቂያ እንዲሰጥዎት ያደርጋል፡፡
ክፍያ ማስቀረት የጠበቃዬን ወጭ ይከፍላል?
አይከፈልም፡፡ ይሁን እንጅ በጉዳይዎ በነጻ ሊወከሉልዎት የሚችሉ ጠበቆች እንዲያገኙ የሚረዱ ነጻ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች አሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ በድህረ ገጽ www.lawhelp.org/dc ይመልከቱ ወይም በዲ.ሲ. ባር የሕግ መረጃ መስመር በ202-626-3499 ስለዚህ ጉዳይ የተቀዳ መረጃ ያዳምጡ፡፡
የ D. C. Bar Pro Bono ፕሮግራም የሚሰጠው አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው፡፡ የሕግ አማካሪ አይደለም፡፡ ሕግን በተመለከተ ምክር ከጠበቃ ያገኛሉ፡፡ ለተወሰነ ጉዳይ የሕግ ምክር ከፈለጉ ወደ ጠበቃ ይሂዱ፡፡ የሕግ መማሪያ ጽሁፎችን ወቅታዊ ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ሕጎች በየጊዜው ይቀያየራሉ፡፡ ስለዚህ የ D. C. Bar Pro Bono ፕሮግራም ለዚህ መረጃ ትክክለኛነት ዋስትና የለው ም፡፡
This resource has been translated into Spanish, French, and Amharic thanks to the American Bar Endowment.