የውክልና ስልጣን ምንድ ነው?
FAQ
የውክልና ስልጣን ምንድ ነው?
ሌላ ሰው እርሶን ወክሎ እንደርሶ ማድረግ ሲችል - ብዙ ግዜ ምቹ ነው - እንደውም በጣም ወሳኝ ነው ፡፡ የውክልና ስልጣን በሚባል ሰነድ አማካኝነት ሌላ ሰው እንደ እርሶ ሆኖ እንዲወስን ህጋዊ ስልጣን መስጠት ይችላሉ፡፡ የውክልና ስልጣን ከሰጡ እርሶ ዋና ሲሆኑ እንዲሁም እርሶ የመረጡት ግለሰብ ደግሞ ወኪል ወይም ተጠሪ ይሆናል፡፡
የውክልና ስልጣን የሚሰጥ ሰነድ ግልፅ እና ለመረዳት የማይከብድ መሆን አለበት፡፡ መስጠት የሚፈልጉትን ስልጣን ብቻ የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡ የሚሰጠው ስልጣን በጣም ውስን ወይም ደግሞ በጣም ሰፊ ሊሆን ይችላል፡፡
ለወኪሌ ምን አይነት ነገሮች ላይ ስልጣን መስጠት እችላለው?
አብዛኛው ሰዎች የሚያደርጓቸው ነገሮች በወኪል አማካይነት ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ ወኪሎን የሚከተሉትን ነገሮች እንዲያደርግ ሊወክሉ ይችላሉ፡
- ለእርሶ እቃ እንዲገዛ ወይም እንዲሸጥ
- የህዝብ ጥቅማ ጥቅሞችን (እንደ ሜዲኬድ፣ ሜዲኬር ወይም ሶሻል ሴክዩሪቲ) ለእርሶ ማመልከት፡፡
- ንግዶን ማስተዳደር
- ክፍያዎችን መቀበል
- ገንዘቦን ስራ ላይ ማዋል
- በቼክ ያሉ ገንዘቦችን ወደጥሬ ገንዘብ መቀየር
- በአጠቃላይ ገንዘብ ነክ የሆኑ ነገሮችዎን ማስተዳደር፤ ወይም
- እርሶን ተክቶ መክሰስ
በውክልና ስልጣን ሰነዱ ላይ ለወኪሎ የቶቹን ስልጣኖች እንደሰጡ እና መቼ ተፈፃሚነት እንደሚኖራቸው የግድ መጥቀስ ይኖርቦታል፡፡
እያንዳንዱ የተሰጠ ስልጣን ሰነዱ ላይ የግድ መስፈር ይኖርበታል?
ሰፋ ባለ ቋንቋ ገንዘብ ነክ ነገሮችን ማስተዳደር ወይም የህክምና አገልግሎት ውሳኔዎችን መስጠት የሚለው ለብዙ ነገር በቂ ሲሆን ወኪሎ “ሁሉንም ስልጣን” እንዲያገኝ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ስልጣኖች የሚሰጡት የግድ በሰነዱ ላይ ከተጠቀሱ ብቻ ይሆናል፡፡ እነዚህ የግድ መጠቀስ ያለባቸው ነገሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡
- ገንዘብዎን ወይም ሌሎች ንብረቶችዎን በስጦታ መልክ ለሌላ ሰው አሳልፎ የመስጠት ስልጣን
- የማህበረሰብ ንብረት ስምምነትዎን የመቀየር ስልጣን እና
- ከኢንሹራንስ ፖሊሲዎ ላይ ተጠቃሚ የሚሆኑ ሰዎችን የመመደብ ስልጣን ናቸው፡፡
አንዳንድ ስልጣኖች ለወኪል መሰጠት የሚችሉ አይደሉም፡፡ ከነዚህም መካከል፡
- በህዝባዊ ምርጫ ላይ የመምረጥ ስልጣን፡ እና
- ኑዛዜ የመስጠት ወይም የማሻሻል ስልጣን ናቸው፡፡
በዝርዝር የተጠቀሱ ስልጣኖች በተለየ መልኩ በትዳር ውስጥ ላሉ አንዳቸው ቢታመሙ እና ነርሶች ቤት መግባት ወይም ሌላ የረዥም ግዜ ህክምና ቢያስፈልጋቸው እና ምን ይፈጠራል ብለው ስጋት ላለባቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ከጉዳተኛው የትዳር አጋር ወደ ጤነኛው ማሻገር ስልጣን ለሜዲኬድ ብቁ እንዲሆኑ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ፤ ለወኪሎ ሰፊ ንብረትን በስጦታ መልክ አሳልፎ ለሌላ ሰው እስከመስጠት ያለ ስልጣን መስጠት ወኪሉ ታማኝ ወይም ብልህ ካልሆነ ከባድ የሆነ ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ጥያዎች ካሎት ከጠበቃዎ ጋር መነጋገር ይኖርቦታል፡፡
የውክልና ስልጣን ተግባራዊ የሚሆነው እና የሚያበቃው መቼ ነው?
- የውክልና ስልጣን እንደተፈረመ ስራ ላይ እንዲውል ወይም ደግሞ ወደፊት በሆነ ግዜ ላይ እንዲተገበር ተብሎ ሊፃፍ ይችላል፡፡
- የወደፊቱ ግዜ ምናልባት የተወሰነ ቀን ወይም የተወሰነ የሁኔታዎች መከሰትን የሚገልፅ ሊሆን ይችላል-- ለምሳሌ፤ በዶክተርዎ በራስዎ ውሳኔ የመስጠት አቅም እንደሌሎት ውሳኔ በሚሰጥበት ወቅት፡፡
- የውክልና ስልጣን እስከመጨረሻው የሚዘልቅ ወይም ለተወሰነ ግዜ ብቻ የሚቆይ ተደርጎ ሊፃፍ ይችላል፡፡
- የውክልና ስልጣንዎ ሲሞቱ ያበቃል፡፡ የኑዛዜ ምትክ ሆኖ ማገልገል አይችልም፡፡
ዘላቂ የውክልና ስልጣን ምንድን ነው?
የእርሶየውክልና ስልጣን ሰነድ ላይ በግልፅ እስካልተገለፀ በቀር እርሶ በአምሮ ብቁ ሆነው መቆየት ካልቻሉ የወኪሎ ስልጣን ይነሳል፡፡ ነገር ግን ፤ የውክልና ስልጣኑ እርሶ በአካል የማይችሉበበት ደረጃ ላይ ቢሆኑም በስራ ላይ እንደዋለ እንዲቆይ እንዲጠቅስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህንን የሚገልፅ የውክልና ስልጣን ዘላቂነት ያለው የውክልና ስልጣን ይባላል፡፡
ዘላቂ የውክልና ስልጣን ሁለት ነገሮችን እንዲሸፍን ተደርጎ ሊፃፍ ይችላል፡፡
- ወኪልዎ ስልጣን እሚኖረው የሚፈልጉት እርሶ በራሶ መወሰን የማይችሉበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ ብቻ ከሆነ፤ ወይም
- የውክልና ስልጣኑ ወዲያውኑ ተግባራዊ እንዲሆን ከፈለጉ እና እርሶ በራሶ መወሰን የማይችሉበት ደረጃ ላይ ቢደርሱም እንዲቀጥል የሚፈልጉ ከሆነ ነው፡፡
ይህ ዘላቂ የሆነ የውክልና ስልጣን ወኪሎን የህክምና አገልግሎት ውሳኔዎችን እንዲወስን ለመፍቀድ መጠቀም ይቻላል?
አዎ፡፡ ዘላቂነት ያለው የውክልና ስልጣንን ለወደፊት የጤና አገልግሎት እቅዶ ላይ ስለመጠቀም ለበለጠ መረጃ "ለጤና አገልግሎት ዘላቂነት ባለው የህግ ውክልና ዙሪያ ተዘውትረው የሚነሱ ጥያቄዎች" የሚለውን ፅሁፍ ይመልከቱ፡፡ . ብዙውን ግዜ ሁለት የተለያየ የውክልና ስልጣን ሰነድ ቢኖር ምቼ ነው -- አንድ ለገንዘብ ነክ ሀላፊነቶች እና አንድ ደግሞ የህክምና አገልግሎት ውሳኔዎችን በተመለከተ፡፡
ዘላቂ የውክልና ስልጣን የሞግዚትነት ምትክ ሆኖ ማገልገል ይችላል?
A Durable Power of Attorney is an alternative to guardianship only if it is given beforeyou become mentally incapacitated. የውክልና ስልጣን ለመስጠት፤ የሚያደርጉትን ነገር የሚያውቁበት አይነት የአእምሮ ብቃት ደረጃ ላይ መሆን ይኖርቦታል፡፡ አንድ ግዜ ይህንን አቅም ካጡ ፤ ለእርሶ የውክልና ስልጣን ለመስጠት በጣም ዘግይተዋል ማለት ነው፡፡ በዛ ደረጃ ላይ እንደ አስፈላጊነቱ ፍርድ ቤት ለእርሶ ሞግዚት ወይም ጠባቂ ሊመድብሎ ይችላል፡፡
ለሰው የውክልና ስልጣን በምንሰጥበት ወቅት የሚያሰጉ ነገሮች ይኖሩ ይሆን?
አዎ፡፡ በውክልና ስልጣን ወኪሎ ብዙ ግዜ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን እንዲወስን እምነት ይጣልበታል እንዲሁም የተወሰኑ ወይም ሙሉ ንብረቶን የማንቀሳቀስ አጋጣሚ ያገኛል፡፡ ወኪሎ ታማኝ ካልሆነ፤ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፤ ወኪሎ እምነቱን ካልጠበቀ እና ገንዘብዎን ይዞ ከጠፋ ገንዘብዎን ለማስመለስ በጣም አስቸጋሪ ወይም የማይቻል ይሆናል፡፡
እንዲሁም፤ በመደበኝነት በወኪሎ እርምጃ(የሞኝ እርምጃም ቢሆን) ውስጥ ይታሰራል እንዲሁም እንደ እርሶ ሆኖ በሚያደርጋቸው ነገሮች ላይ ለወኪሎ ቸልተኝነት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ለምሳሌ፤ ወኪሎ ገንዘብ ነክ ነገሮችዎን እንዲያስተዳድር ስልጣን ከተሰጠው እና እርሶን ወክሎ የሆነ ነገር ለመግዛት ውል ከፈረመ እርሶ ወደዱም ጠሉም ለመክፈል ይገደዳሉ፡፡
የሚታመን ወኪል መምረጥ በርግጥም በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ የትኞቹን ሀላፊነቶች ለወኪሎ መስጠት እንዳለብዎ በጥንቃቄ ሊያስቡ ይገባል፡፡
ለእርሶ ውሳኔ ለመወሰን የወኪሎ አመለካከት በምን ሊመራ ይገባል?
እርሶ ውሳኔዎችን በራሶ የመወሰን አቅሞን እስካላጡ ድረስ ወኪሎ በእርሶ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ሊንቀሳቀስ ይገባል፡፡
እርሶ ውሳኔ የመስጠት አቅሞን ካጡ፤ ወኪሎ እርሶ የማድረግ አቅም ባሎት ግዜ ሊያደርጉ የሚችሉትን ነገር ከግምት ውስጥ በማስገባት ማድረግ አለበት፡፡
ለምሳሌ ወኪሎ እርሶ ብቁ ሆነው በነበረበት ወቅት ከሆነ ድርጅት ጋር መስራትን እንደሚቃወሙ እያወቀ እርሶ በራሶ መወሰን የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ከሆኑ እርሶን ወክሎ ከዚህ ድርጅት ጋር መስራት የለበትም፡፡
እርሶ የሚፈልጉትን ነገር መለየት ወኪሎ መለየት ካልቻለ/ች እሱ ወይም እሷ የእርሶ የተሻለ ፍላጎት ሊሆን ይችላል ብለው ያሰቡትን እንዲያደርጉ ይጠበቃል፡፡
የውክልና ስልጣን ከሰጠሁ በኋላ በነፃነት እንቅስቃሴዬን መቀጠል እችላለው?
አዎ፡፡ ለሰው የውክልና ስልጣን መስጠት ውሳኔ ከመወሰን ወይም ለግሎ የግሎን ንግድ ከማንቀሳቀስ አያግድም፡፡ እርሶ እና ወኪሎ ካልተስማማችሁ፤ የእርሶ ውሳኔ ይመራል፡፡ (ይህም በተመሳሳይ ሰዓት የሚሰጥ ውሳኔ ላይ ከሆነ ነው፡፡ ወኪሎ የሆነ ንብረት መሸጥ እንዳለበት ከወሰነ እና ከሸጠ በኋላ የሚወስኑት ውሳኔ ንብረቱ እንዳይሸጥ የሚል ቢሆን የተሸጠውን ንብረት ማስመለስ አይችሉም፡፡) ወኪሎ ፍላጎቶን የማያከብር ከሆነ፤ የውክልና ስልጣኑን ማንሳት ይኖርቦታል፡፡
ዘላቂ የሆነ የውክልና ስልጣን ካለው ወኪሎ ጋር በሀሳብ ካልተስማሙ እርሶ ብቻዎን ውሳኔ ለመስጠት የማይፈቅድ ሁኔታ ላይ ከሆኑ በኋላ የውክልና ስልጣኑን ማንሳት ስለማይችሉ ችግር ሊፈጠር ይችላል፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ወቅት፤ ወኪሎ በሞግዚትነት ለመቀጠል ጥያቄ ሊያቀርብ እና ፍርድ ቤቱን የእርሶን የአእምሮ ብቃት እንዲያጣራ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
የውክልና ስልጣን በአንድ ግዜ ከአንድ በላይ ለሆኑ ሰዎች መስጠት ይቻላል?
አዎ፡፡ የውክና ስልጣን ለሁለት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ሰዎች በአንድ ግዜ መስጠት ይችላሉ ወይም ሁለተኛ ወኪሎን ውስን በሆኑ ሁኔታዎች ላይ ብቻ ሀላፊነት እንዲወስድ አድርገው ሊወክሉ ይችላሉ(ለምሳሌ የመጀመሪያው ወኪል ህይወት ካለፈ)፡፡
ነገር ግን ከአንድ በላይ ለሆኑ ግለሰቦች የውክልና ስልጣን ከመስጠትዎ በፊት ግራ መጋባት ወይም ግጭት የሚያስከትል ነገር መኖር አለመኖሩን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡ የውክልና ስልጣን ከአንድ በላይ ለሆኑ ወኪሎች ከመስጠት በፊት ሊያስገኝ ስለሚችለው እና ሊያሳጣ ስለሚችለው ነገር (እንዲሁም ሊያሳጣ የሚችለውን ነገር ስለመፍታት) ከጠበቃ ጋር ቀደም ብሎ መወያየት ብልህነት ነው፡፡
የውክልና ስልጣን የግድ መፃፍ ወይም ተቀድቶ መቀመጥ ይኖርበታል?
አንዳንድ ግዜ፡፡ ወኪሎን መሬት የመሸጥ ስልጣን ለመስጠት ከፈለጉ፤ ወይም በሌላ መንገድ ለማስተላለፍ ወይም ሀላፊነት ለመስጠት ካሰቡ በሰነዱ ላይ ለተጠቀሰው አላማ እርሶ በፈቃደኝነት መፈረምዎን የውክልና ስልጣን ሰነዱን በጠበቃዎ ፊት በመፈረም ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ የውክልና ስልጣን ሰነዱ የሚከተሉትን ነገሮች በመጀመሪያው ገፅ አናት ላይ በደማቁ ተፅፎ ሊይዝ ይገባል፡፡
ይህ የውክልና ስልጣን ከዚህ በታች ስሙ የተገለፀው ግለሰብ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ነገሮችን እንዲያከናውን ወኪሌ ሆኖ እንዲያከናውን የሚከተለው ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ እዚህ የውክልና ስልጣን ሰነድ ላይ ለተወሰኑ ንብረቶች ብቻ ተብሎ ተዘርዝሮ እስካልተቀመጠ ድረስ እኔን ወክሎ እንዲሸጥ፣ እንዲያከራይ፣ እንዲሰጥ፣ ስም እንዲያዞር፣ ከንብረቴ ውስጥ እንዲያስወጣ ወይም ሌላ ፍላጎቱን በግል ንብረቶቼ ላይ እንዲገልፅ እንዲሁም ሂደቱን ለማስፈፀም ሌሎች ነገሮችን እንዲተገብር፡፡
የውክልና ስልጣኑን መጠነ ሰፊ ለሆነ የቤት ግንባታ ግብይት የሚጠቀሙበት ከሆነ ንብረቱ በሚገዛበት ወይም በሚሸጥበት ቀን ወይም ቀደም ተብሎ በሰነዶች መመዝገቢያ ቢሮ በመሄድ መመዝገብ ይኞርበታል፡፡ የውክልና ስልጣን ሰነዱ ለህዝብ መዝገብ ግልባጭ ተደርጎ ዋናው ለሚያስገባው ሰው ተመላሽ ይሆናል፡፡
ምንም አይነት መሬት በወቅቱ ከሌለ በሰነዶች መመዝገቢያ ሄዶ ውል መፈራረሙ ከህግ አንፃር ያን ያክል አስፈላጊ አይደለም፤ ነገር ግን ምንም ቢሆን በሰነዶች መመዝገቢያ ሄዶ መፈራረም ብልህነት ነው፡፡ አንዳንድ ተቋሞች ወይም ግለሰቦች በሰነዶች መመዝገቢያ ያልተረጋገጠ የውክልና ስልጣንን በመጠራጠር ህጋዊነቱን ከማመን ይቆጠባሉ፡፡
የውክልና ስልጣን ሊሰረዝ ይችላል?
አዎ፡፡ ይህም የውክልና ስልጣን ማንሳት ይባላል፡፡ የውክልና ስልጣንን ለማንሳት ለወኪሉ እንዲሁም ከተቻለ በውክልና ስልጣኑ ጋር ለተገናኘ ማንኛውም ሰው በሙሉ የፅሁፍ መግለጫ መስጠት ይጠበቅቦታል፡፡
የውክልና ስልጣን ሰነዱ ወኪሎን መጠነ ሰፊ የሆነ የቤት ግንባታ ግብይት እንዲያደርግ እንዲያስችለው የተሰጠ ከነበረ የውክልና ስልጣኑን መነሳት የሚገልፀውን የፅሁፍ መግለጫ ለሰነዶች ማረጋጫ ቢሮው በመስጠት ማስመዝገብ ይኖርቦታል፡፡ማሳወቂያው ሰነድ የዋናውን የውክልና ስልጣን የሰነድ ቁጥር እና ቀን ሊይዝ ይገባል፡፡
የውክልና ስልጣን ላይ የፍርድ ቤት ክትትል ሊኖር ይችላል?
በተለምዶ፤ የውክልና ስልጣን ያለው ወኪል ያለምንም የፍርድ ቤት ክትትል መንቀሳቀስ ይችላል፡፡ ነገር ግን፤ የተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ የውክልና ስልጣን የፍርድ ቤትን እይታ የሚጠይቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ጥያቄዉ በእርሶ ወይም በተወሰኑ ጉዳዩ በሳባባቸው ግለሰቦች ሊቀርብ ይችላል፡፡ ፍርድ ቤት ለምሳሌ ሶስተኛ ወገን የውክልና ስልጣኑን ማክበር እንዳለበት እና እንደሌለበት ሊወስን ይችላል፣ አንድ ተወካይ ለእርስዎም ሆነ ለሶስተኛ ወገን ማብራሪያ እንዲሰጥዎ ሊያዝዝ ይችላል ወይም የውክልና ሥልጣኑን ሊተረጉመው ወይም ሊያሻሽለው ወይም ወኪሉን ሊያስወግድ ይችላል፡፡
የውክልና ስልጣን ሰነድ ለማዘጋጀት ጠበቃ ያስፈልገኛል?
የውክልና ስልጣን ሰነድ በጠበቃ መዘጋጀት ወይም ደግሞ ጠበቃ ሊያየው ይገባል የሚል የህግ ቅድመ ሁኔታ የለም፡፡ ነገር ግን፤ ለወኪሎ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ስልጣኖችን የሚሰጡ ከሆነ የተወሳሰበ ሰነድ ከመፈረም የግል የህግ አማካሪ ማግኘቱ ብልህነት ነው፡፡ የውክልና ስልጣን ሙሉ በሙሉ ምን እንደሚል ሳይዱ እና ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ እንዲሁም አማራጮችን ሳያዩ መፈረም ችግርን እንደመጥራት ይቆጠራል፡፡
ስለ ግል የውክልና ስልጣን ሰነድ የህግ አማካሪ የት ማግኘት እችላለው?
እዚጋ ጠቅ ያድርጉ የህግ አገልግሎት ኤጀንሲዎች ዝርዝር መረጃ በመስጠት ይረዳዎታል፡፡ ለነፃ የህግ ድጋፍ ብቁ ካልሆኑ፤ በፈቃድ እና እግድ ላይ የሚሰሩ ወይም በውክልና ስልጣን ሰነድ ላይ ልምድ ወዳላቸው እና ብቁ የሆኑበትን የሙያ ዘርፍ እንደ “የጥንት ህግ” ወደሚቆጥሩ ጠበቃዎች መሄድ ይኖርቦታል፡፡
የውክልና ስልጣን ለመስጠት መጠቀም የምችለው ቅፅ ይኖር ይሆን?
ማሳሰቢያ፡ የዚህን ቅፅ ባዶ ቦታ በመሙላት መጠቀም ቢቻልም፤ ለእያንዳንዱ ጉዳዩ ተገቢ ላይሆኑ ግን ይችላሉ፡፡ በእርሶ ግላዊ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የውክልና ስልጣን ሰነድ ቢኖሮ በጣም የተሻለ ነው፡፡ መስጠት የሚፈልጉትን ስልጣን ብቻ መስጠት የሚችሉ መሆን አለባቸው እንዲሁም እርሶ በሚፈልጉት መንገድ ብቻ ተፈፃሚ የሚሆኑ መሆን አለባቸው፡፡ በዚህ ቅፅ ውስጥ ያልተረዱት ምንም አይነት ነገር ቢኖር፤ ከመፈረምዎ በፊት ጠበቃዎን ማናገር ይርቦታል፡፡