በተከራዮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
Information
1. የቤት ባለ ንብረቶች ሀላፊነቶች
የቤት አከራይ ከመሆኔ በፊት፤ ፈቃድ ሊኖረኝ ይገባል? ንብረቶቼን ለዲስትሪክቱ ማስመዝገብ ይጠበቅብኛል?
አዎን፤ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት፤ የመኖሪያ ቤቶን ካከራዩ አንድ ክፍልም ቢሆን፤ ማከራየት ከመጀመርዎ በፊት የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ ይጠበቅቦታል፡፡
- ያግኙ የይዞታ ማረጋገጫ ሰርትፊኬት የሚያከራዩት አፓርትመንት፣ የጋራ መኖሪያ ውስጥ ያለ ክፍል ወይም የይዞታ ማረጋገጫ ያለው ሙሉ ህንፃ ውስጥ ያለ ኮንዶሚኒየም ወይም የሚከራየው ቤት የአንድ ሙሉ ቤተሰብ ቤት ካልሆነ በቀር ፡፡
- የቤት ንግድ ፈቃድ ያግኙ
- ለመመዝገብ ወይም ከቤት ኪራይ ዋጋ ማረጋጊያ(የኪራይ ቁጥጥር) ነፃ ለመሆን ያመልክቱ፡፡
ቀድሞውኑ ቤት እያከራዩ ከነበረ እና እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልተው ካልነበረ ህግ እየጣሱ ነበር ማለት ነው፡፡ ለመመዝገብ ከማሰብዎ በፊት በምዝገባ ወቅት የሚጣልብዎትን ቅጣት ለማስወገድ ጠበቃ ማናገር ሊኖርቦት ይችላል፡፡ እነዚህን ሂደቶች ለማጠናቀቅ ከዚህ በታች የበለጠ መረጃ አለ፡፡ ስለ ፈቃድ እና ምዝገባ ቅድመ ሁኔታዎች ጠቅለል ያለ መረጃ ከፈለጉ ይጫኑ እዚህ ጋ.
ቤቱ በኪራይ ቁጥጥር ስር ያለ መሆኑን በምን አውቃለሁ?
ከቤት ኪራይ ዋጋ ማረጋጊያ ፕሮግራም(የቤት ኪራይ ቁጥጥር) በሁሉም የሚከራዩ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል ፕሮግራሙ ውጪ የሚያደርግ ፕሮግራም ውስጥ እስካልሆኑ ድረስ፡፡ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ካሟሉ ከኪራይ ቁጥጥር ውጪ ለመሆን ማመልከት ይችላሉ፡
- አራት ወይም ከዛ በታች የሚከራይ ኣፓርታማ በግሎ (በንግድ መልክ ያልሆነ)፣ ብቻዎን ወይም ከአራት ወይም ካነሱ ሰዎች ጋር(የንግድ ያልሆነ) ካሎት እና ከቁጥጥሩ ለመውጣት አመልክተው ከሆነ፤ ወይም
- የአካባቢ ወይም የፌደራል ኪራይ እያገኙ ከሆነ ድጎማ ወይም ሞርጌጅ ድጎማ ለ ክፍሎ፡ ወይም
- የሚከራየው ክፍል የግንባታ ፍቃድ ከታህሳስ 31/1975 በኋላ የወጣ ከሆነ ወይም የመጀመሪያው የይዞታ ማረጋገጫ ከ ጥር 1 1980 በኋላ የወጣ ከሆነ፤ የዚህ አዲስ ህንፃ ግንባታ በኪራይ ዋጋ ቁጥጥር ስር ያለ ተመሳሳይ ቁጥር ያለው ወይም ከዛ የሚበልጥ ህንፃን ማፍረስ የማይጠይቅ ከሆነ
- አጠቃላይ ህንፃው የተገነባበት መገኛ ቦታ ከጥር 1985 ጀምሮ በተደጋጋሚ ባዶ ከነበረ ፤ እንደገና በሚከራይበትም ወቅት ከዲ.ሲ. የቤቶች ህግ ጋር በተሳለጠ መልኩ ሲከራይ እንደነበር የሚያሳይ ነገር ከቀረበ፡፡
ከቁጥጥሩ ለመውጣት ብቁ ቢሆኑም እንኳ እንደ "አነስተኛ አከራይ" አራት እና ከዛ በታች የሆነ የሚከራይ ቤት እንዳለው ፤ የኪራይ ዋጋ ለመጨመር እና እንደ አከራይ ንግድ ውስጥ ለመግባት ከቁጥጥሩ ነፃ የመሆኛ ቁጥር ለማግኘት ማመልከት አለቦት፡፡ ለሌሎች ከቁጥጥር ነፃ መሆኛ ምክንያቶች ብቁ የሆኑ የቤት ባለንብረቶች የነፃ መሆኛ ቁጥር ለማግኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አንዳንድ ቤቶች ከኪራይ ቁጥጥር ሙሉ በሙሉ የወጡ ናቸው፡፡ እነዚህም፡ ሆስፒታሎች፣ የነርስ ቤቶች፣ ዶርሞች፣ በውጪ ሀገር መንግስት የሚተዳደሩ የሚከራዩ ክፍች እና ለትርፍ ባልተቋቋሙ እና የማህበራዊ አገልግት ለነዋሪው የሚሰጡ ድርጅቶች ክፍሎች ናቸው፡፡
ለመመዝገብ ወይም ከቤት ኪራይ ዋጋ ማረጋጊያ(የኪራይ ቁጥጥር) ነፃ ለመሆን ማመልከት ያለብኝ የት ነው?
ከሀውሲንግ እና ኮሚዩኒቲ ዴቨሎፕመንት ዲፓርትመንት የሬንታል አኮሞዴሽን ዲቪዥኑን ማግኘት ይኖርቦታል፡፡ በስልክ ቁጥር (202) 442-9505 እና ቢሮው በ 1800 Martin Luther King, Jr. Avenue, SE, Washington, D.C. 20020 ይገኛል፡፡
የይዞታ ማረጋገጫ ሰርትፍኬቱን እንዴት ማግኘት እችላለው?
የኮንሲዩመር እና ሬጉላቶሪ አፌርስ ክፍልን የዞን አስተዳደር ቢሮ ያግኙ፡፡ ስልክ ቁጥሩም (202) 442-4400. ማስገባት ይጠበቅቦታል ማመልከቻ፣ የ ቅድመ-ይዞታ መረጃ፣ እና $36.30 የማመልከቻ ክፍያ፡፡ የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬቱን በሚወስዱበት ወቅት ተጨማሪ ክፍያ ቢያንስ $42.00 ያስፈልጋል፡፡ በአብዛኛው የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬቱ ከመሰራቱ በፊት የንብረት ማጣራት ስራ ይካሄዳል፡፡ በኮንሲዩመር እና ሬጉላቶሪ አፌርስ ክፍል ላይ ተጨማሪ መረጃ አእዘዚ ይገኛል ድህረ ገፅ፡፡
የቤቶች ንግድ ፈቃድ ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?
የፈቃድ መስጠት ሂደቱ ሊያከራዩ በሚያስቡት የቤት አይነት ላይ ይወሰናል፡
- ለአንድ ቤተሰብ የሚከራዩ ቤቶች፡ የነጠላ-ቤተሰብ ቤቶች፣ የከተማ ቤቶች፣ ዱፕሌክሶች፣ የአንድ ሰው የኮንዶሚንየም ክፍሎች ወይም የግለሰብ ክፍሎች
- ለሁለት ቤተሰብ የሚከራዩ ቤቶች፡ ሁለት የተለያዩ መኖሪያዎች ያሉት ህንፃ ለምሳሌ ከታች የእንግሊዞች ቤዝመንት አፓርትመንት ያለው መኖሪያ ቤት
- የአፓርትመንት ቤቶች፡ ሶስት እና ከዛ በላይ የሆኑ መኖሪያዎችን የያዘ
የቤቶች ንግድ ፍቃድ የመስጠት ሀላፊነት ያለበት የኮንሲዩመር እና ሬጉላቶሪ አፌርስ ክፍል ነው፡፡ ይጫኑ እዚ ጋ ማመልከቻዎችን በቀጥታ ለማግኘት፡፡ ከተዘረዘሩት የንግድ አይነቶች፣ ምረጥ "የአንድ ቤተሰብ ኪራይ"፣ "የሁለት ቤተሰብ ኪራይ"፣ ወይም "የአፓርትመንት ቤቶች"፡፡
ለቤቶቹ ጥገና ማን ነው ሀላፊነት የሚወስደው?
የቤቱ ባለቤትመደበኘኛ ለሀሆነኑ በብለልሸሽተቶቸች ጥገና ሀላፊነቱን ይወስዳል፤ ነገር ግንተከራዩ ወይም የተከራዩ እንግዶች ብልሽቱን እስካልፈጠሩ ድረስ፡፡ ከበድ ያለ የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት በሚከራይ ቤት ላይ ቢፈፀም፤ ተከራዩ የቤቱን ኪራይ መክፈል ወይም ሙሉ ክፍያ መክፈል አይጠበቅበትም፤ እንዲሁም በሲቪል እና በወንጀል ተጠያቂ የመኖሪያ ቤት ህግ በመጣስ ያደርጋል፡፡
ይህ ተከራይ ቤቱን ንፁ አድርጎ የመያዝ እና የቤቱን ቁሶች እና መሳሪያዎች በአግባቡ የመጠቀም ሀላፊነት አለበት፡፡ ተከራዩ ቤቱን፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ማሽኖችን፣ ቁሳቁሶችን እና እቃዎችን በማወቅ ወይም በከፍተኛ ቸልተኝነት ከማጥፋት እና ከማበላሸት መቆጠብ አለበት፡፡
የመኖሪያ ቤት ህግን ካለማክበር ሊከተሉ የሚችሉ ነገሮች መካከል የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው፡
- ይህ ተከራይ የቤት አጣሪ ንብረቶቹ ላይ ጉብኝት እንዲካሄድ እና የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰቶችን በሙሉ ሪፖርት እንዲደረግ መጠየቅ ይችላል፡፡ አጣሪው የማጣራት ሂደቱን ሪፖርት ግልባጭ ለእርሶ በመላክ በተወሰነ ግዜ ውስጥ መደረግ ያለበት እድሳት ካለ እንዲካሄድ ሊጠይቆ ይችላል፡፡ እድሳቱ በተባለው ግዜ ካልተከናወነ ሊገኙ ይችላሉ፡፡
- ይህ ተከራይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት በሲቪል እርምጃ ቅርንጫፍ ፍርድ ቤቱ የእድሳት ትእዛዝ እንዲያወጣ በቤቱ ሁኔታ ካሌንደር ላይ ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ አንድ ተከራይ በዚህ ፍርድ ቤት የቤት ኪራይ ክፍያውን ማስመለስ አይችልም፤ ነገር ግን ይህ ተከራይየተለየ ጉዳይ በአነስተኛ ጥያቄዎች ፍርድ ቤት እስከ 10,000$ ያለ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል፡፡ ይጫኑ እዚ ጋር ለበለጠ መረጃ በቤቶች ሁኔታ ካሌንደር ላይ እንዴት ጉዳዮን እንደሚያመለክቱ ይመልከቱ፡፡
- አንድ ተከራይ በሲቪል እርምጃ ቅርንጫፍ እርሶ እድሳት እንዲያደርጉ የሚጠይቅ እና የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት በተፈጠረበት ወቅት h r ተከራዬ ለቤት ኪራይ ብዙ ወጪ በማውጣቱ ወጪው ተመላሽ እንዲሆንለት መደበኛ የሆነ ጉዳይ ማመልከት ይችላል፡፡ (የተመሰረተው ክስ የሚፈልገው ገንዘብ ብቻ ከሆነ እና የቤት እድሳት ጥያቄ ከሌለበት፤ ተከራዩከ10,000$ በላይ የግድ መጠየቅ አለበት ወይም ጥያቄውን በአነስተኛ ጥያቄዎች ፍርድ ቤት በኩል ማድረግ ይኞርበታል፡፡)
- የተጣሰው የመኖሪያ ቤት ህግ በጣም ከባድ ከሆነ (ለምሳሌ በክረምት ወቅት ምንም አይነት ሙቀት አለመኖር)ተከራዩበአፋጣኝ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የሲቪል እርምጃ ቅርንጫፍ ጊዜያዊ የእገዳ ትእዛዝሙቀቱ እንዲመለስለት እንደ ቤቶች ሁኔታ ካሌንደር ወይም እንደ መደበኛሲቪል እርምጃእንዲወጣ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
- የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰቱ ያን ያህል ከባድ ካልሆነ፤ተከራዩማስገባት ይችላልየተከራይጥያቄ ለሬንታል አኮሞዴሽን ዲቪዥን፡፡ ይህ ኤጀንሲ ተከራዮችን በአከራዮቻቸው ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ይፈቅዳል፡፡ ደንቦቹ እና ሂደቶቹ መደበኛ ያልሆኑ ናቸው እንዲሁም ለመቀጠል ተከራዮች በአብዛኛው ጠበቃ አያስፈልጋቸውም፡፡
- አንድተከራይበአነስተኛ ጥያቄዎች ፍርድ ቤት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ይችላል፡፡ አንድ ተከራይ ገንዘቡን አከራይ እንዲመለስለት ካሰበ በተከራየው ቤት ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ያወጣውን ወጪ ተከራይ ለሌላ ቦታ ኪራይ ያወጣውን ወጪ ወይም ተከራይ ለገጠመውየመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት ተከራይ እስከ 10,000$ ያለ ወጪውን ለመጠየቅ የአነስተኛ ጥያቄዎች ፍርድ ቤት በመሄድ ማስፈፀም ይችላል፡፡
- አንድ ተከራይ የቤት ኪራይ መክፈል ሊያቆም ይችላል፡፡ ወደ አከራይ ተከራይ ፍርድ ቤት ጉዳይን ማምጣት የሚችሉት አከራዮች ብቻ በመሆናቸው ለተከራይ ዳኛ ፊት ለመቅረብ ያለው ብቸኛ አማራጭ የቤት ኪራይ አለመክፈል እና በአከራይ እስኪከሰሱ መጠበቅ ብቻ ይሆናል፡፡ አንድ ግዜ በአከራይ ተከራይ ፍርድ ቤት ከደረሱ፤ ተከራዩ ዳኛውን እርሶ ቤቱ ላይ እድሳት እንዲያደርጉ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ አንድ ተከራይ መክፈል ካለበት ኪራይ ላይ ቅናሽ ሊያገኝ የሚችልበት አጋጣሚም አለ፡፡
የቤት ይዞታ ቁጥጥር እንዲደረግ እንዴት መጠየቅ እችላለሁ?
እድሳቱ እንደተደረገ እና እንደማያስፈልግ ማረጋገጫ ለማግኘት ወይም he ተከራዩ የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት ማድረጉን ለማረጋገጥ ንብረትዎ በቤት ይዞታ ተቆጣጣሪ እንዲፈተሸ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ቀጠሮ ለማስያዝ፤ በ(202) 442-4400 ይደውሉ፡፡ በቤቱ ውስጥ ስለተደረገው እድሳትም ሆነ ተከራይ ስላደረሰው የህግ ጥሰት ለተቆጣጣሪው ለማሳየት በፍተሸው ወቅት ቢገኙ በጣም ጥሩ ነው፡፡
2. የኪራይ ዋጋ መጨመር
የኪራይ ዋጋ መጨመር እችላለው?
እርሶ እና ተከራዮ በአብዛኛው በፅሁፍ በተቀመጠ ሊዝ፤ የተወሰነ የመጠን ስምምነት ካላችሁ ዋጋ መጨመር አይችሉም፤ በአብዛኛው እርሶ እና ተከራዮ በተወሰነ መጠን ለተወሰነ ግዜ ስምምነት ይኖራችኋል፡፡ ያ ግዜ አንድ ግዜ ካለቀ፤ በ30 ቀን የፅሁፍ ማሳወቂያ የቤቶን ኪራይ ዋጋ መጨመር ይችላሉ፡፡ እርሶ እና ተከራይዎ የተወሰነ የግዜ ገደብ ላይ ካልተስማማችሁ በአብዛኛው በ30 ቀን የፅሁፍ ማሳወቂያ ዋጋ መጨመር ይችላሉ፡፡
ዋጋ መጨመር የሚችሉ ከሆነ፤ ምን ያህል እና በምን ያህል ግዜ ዋጋ መጨመር እችላለው የሚለው የቤቱ የኪራይ ቁጥጥር ስር መሆን አለመሆኑ ላይ ይመሰረታል፡፡ ቤቱ ከኪራይ ቁጥጥር ነፃ የሆነ ቤት ከሆነ፤ ዋጋ የሚጨምሩት ህጋዊ ላልሆነ ነገር እስካልሆነ ድረስ ለምሳሌ ተከራዮ የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት ስላመለከተ ወይም እድሳት ስለጠየቀ እንደ ማጥቂያ እስካልሆነ ድረስ የቤቱን ዋጋ በየትኛውም መጠን እና በፈለጉት ግዜ መጨመር ይችላሉ፡፡ የዋጋ ጭማሬው ተግባራዊ ከማድረግዎ ድረስ ቢያንስ 30 ቀናት ቀደም ብለው ለተከራዮ የዋጋ መጨመሩን የሚገልፅ የፅሁፍ ማሳወቂያ ሊሰጡ ይገባል፡፡
መኖሪያ ቤቱ የኪራይ ቁጥጥር ውስጥ ካለበት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር የሚችሉት በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ነው፡
- ለመጨረሻ ግዜ ዋጋ የተጨመረው ቢያንስ ከ12 ወራት በፊት መሆን ይኖርበታል(ቤቱ ባዶ ካልሆነ በቀር)
- ቤቱ በአግባቡ በሬንታል አኮሞዴሽን ዲቪዥን ራድ የተመዘገበ ከሆነ
- የሚከራየው ቤት እና ሀውሲንግ አኮሞዴሽን የተለመደ መለያቸው የመኖሪያ ቤቶች ህግን ያከብራሉ፡፡
- ለማንኛውም የኪራይ ጭማሬ የ30-ቀን የፅሁፍ ማሳወቂያ ይሰጣሉ
በአጠቃላይ፤ የዋጋ ጭማሬ ሊያደርጉ የሚችሉት በዋጋ መቆጣጠሪያው ክፍል መሰረት በተወሰነ ፐርሰንት ብቻ ነው፡፡ ይሄም ከ10 በመቶ የበለጠ መሆን የለበትም እንዲሁም በየ አመቱ የሚኖረው የዋጋ ጭማሬ በሬንታል ሀውሲንግ ኮሚሽን የሸማች ዋጋ መረጃ ጠቋሚ ላይ ተመስርቶ ይሆናል፡፡ ሬንታል ሀውሲንግ ኮሚሽንን በ(202) 442-8949 በመደወል ምን ያህል ዋጋ መጨመር እንደሚችሉ ማወቅ ይችላሉ፡፡
የሚያከራዩት ቤት የትርፍ መጠኑ ቢያንስ 12 በመቶ ካልመለሰ፤ የሬንታል አኮሞዴሽን ዲቪዥን የሀውሲንግ እና ኮሚዩኒቲ ክፍሉን በመደበኛነት ከተፈቀደው አመታዊ ጭማሬ በላይ የዋጋ ጭማሬ ለማድረግ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ይሕንን ለማድረግም በንብረቱ ላይ ያሎትን እሴት፣ የስራ ማስኬጃ ወጪዎች፣ ምን ያህል የቤት ኪራይ እንደሚሰበስቡ እና ሌሎች የሂሳብ መረጃዎችን በማሳየት የ "ሀርድሺፕ ፔቲሽን" ወይም የይታይልኝ ጥያቄ የግድ ማቅረብ ይኖርቦታል፡፡ የይታይልኝ ጥያቄዎን እንዴት ማስገባት እንደሚችሉ የሬንታል አኮሞዴሽን ዲቪዥኑን በ(202) 442-9505 ቁጥር በማግኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በመጨረሻም፤ የተወሰነ የደረጃ ማሻሻል በህንፃው ላይ ካደረጉ፤ ያወጡትን ወጪ ለመክፈል የዋጋ ጭማሬ ለማድረግ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ፡፡ ከሬንታል አኮሞዴሽን ዲቪዥን የሀውሲንግ እና ኮሚዩኒቲ ዴቨሎፕመንት ቢሮ በዚህ ምክንያት ዋጋ መጨመር እንዲችሉ ፈቃድ ያስፈልጎታል፡፡ የሬንታል አኮሞዴሽን ዲቪዥንን በ(202) 442-9505 ደውለው ያግኙ፡፡
3. የደህንነት ማስያዣዎች
ለደህንነት ማስያዣ ምን ያህል ላስከፍል?
ከቤቱ የአንድ ወር ክፍያ በላይ ላያስከፍሉ ይችላሉ እንዲሁም ክፍያውም አንድ ግዜ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡
ይህንን ገንዘብ በልዪ ሁኔታ እንዳስቀምጥ ይጠበቅብኛል?
ገንዘቡን በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ወለድ በሚያስገኝ ሂሳብ በፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የግድ ማስቀመጥ አለብዎ፡፡ የባንክ ሂሳቡ ይህንን የደህንነት ማስያዣ ለማስቀመጥ ለብቻው የተከፈተ መሆን አለበት፡፡ ያንኑ ተመሳሳይ የባንክ ሂሳብ ከአንድ በላይ ለሆኑ ህንፃዎች መጠቀም ይቻላል፡፡ ተከራዩ ቤቱን ቢያንስ ለ12 ወራት ከተከራየ ከደህንነት ማስያዣ ወለዱ ላይ ህጋዊ የሆኑ ተቆራጮችን በመቀነስ እንዲከፍሉ ይጠበቅቦታል፡፡ የወለዱ መጠን በቁጠባው መጠን በተቀመጠበት ባንክ (በጃንዋሪ አንድ እና በጁላይ አንድ) በየ ስድስት ወር ይስተካከላል፡፡
ተከራዩ ቤቱን ከለቀቀ በኋላ ያስቀመጠውን ገንዘብ ለመመለስ ምን ያህል ግዜ ይኖረኛል?
የተቀመጠውን ገንዘብ ከነ ወለዱ ለመመለስ ወይም ደግሞ ተከራዩን ገንዘቡ የተያዘበትን ምክንያት እና ላጋጠመው ተገቢ የሆነ ወጪ ላይ ስለማዋል ለመንገር 45 ቀናት አሎት፡፡ ኢንተረስት የሚከፈለው አመት እና ከዛ በላይ ለቆዩ ተከራዮች ብቻ ነው፡፡
የተቀመጠውን ገንዘብ ለምን እጠቀመዋለው?
በአጠቃላይ ባለንብረቱ የደህንነት ማስያዣውን ተከራዩ በሊዙ ስምምነት መሰረት ሀላፊነቱን መወጣቱን እርግጠኛ ለመሆን ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ባለ ንብረቱ ማስያዣውን ለምን እንደሚጠቀመው ወይ በፅሁፍ ሊዝ ወይንም ደግሞ ለደህንነት ማስያዣው በተፃፈ ደረሰኝ በፅሁፍ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ ለምሳሌ በቤቱ ላይ ለደረሰ ብልሽት ለማስተካከል መከፈሉን ወይም ተከራዩ የቤት ኪራዩን መክፈል እያለበት ቤቱን ከለቀቀ ለቀረው ክፍያ መጠቀሞን የሚያሳይ፡፡
የቤቱ ጉዳት ወይም ችግር በተከራዩ ወይም በተከራዩ እንግዶች እስካልተፈፀመ ድረስ ለማንኛውም የቤቱ እድሳት ወጪ ተጠያቂ እርሶ ኖት፡፡ ተከራዩ ወይም የተከራዩ እንግዶች በአደጋ ወይም በቸልተኝነትም ቢሆን ቤቱን ካበላሹት ለእድሳቱ የሞከፍለው ተከራዩ ይሆናል፡ በተከራዩ ወይም በተከራዩ እንገግዶች ላልተፈጠሩ ብልሽቶች ለመደበኛ እድሳት እና የተጎዱ ነገሮች ማስተካከያ ሀላፊነት ያለብዎ እርሶ ኖት፡፡
የደህንነት ማስያዣውን ሙሉ በሙሉ ወይም የተወሰነ ለማስቀረት ቢያስቡ ምን ይፈጠራል ?
በተገቢ መንገድ ለተፈጠረ ወጪ መሸፈኛ የደህንነት ማስያዣውን ቢያስቀሩ ሁኔታውን ለተከራዩ በፅሁፍ በአካል በመስጠት ወይም በደብዳቤ በመላክ ማሳወቅ ይኖርቦታል፡፡ ይህንን ማሳወቂያ በሰጡ በ30 ቀናት ውስጥ ለተከራዩ የተቀየሩ ነገሮች ዝርዝር መግለጫ እና ሌሎች ገንዘቡ የዋለባቸው ቦታዎች ከእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ጋር ተዘርዝሮ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
የደህንነት ማስያዣው የተያዘበት አንድ ተከራይ ከእኔ በተቃራኒ ሆኖ ምን ሊያደርግ ይችላል?
ተከራዩ ህጋዊ ክስ በአብዛኛው የአነስተኛ ጥያቄዎች ፍርድ ቤት በማቅረብ ተገቢ የሆነው መጠን ተመላሽ እንዲሆንለት ሊጠይቆ ይችላል፡፡ በክርክሩ ከተሸነፉ በደህንነት ማስያዣው መጠን ላይ የተፈጠረ ብልሽት ካለ ተደምሮ የገንዘብ ውሳኔ በእርሶ ላይ ይፈረዳል፡፡
ማስያዣውን ባለመመለሴ እና ወይም ማሳወቂያ ባለመስጠቴ ልቀጣ እችላለሁ ?
ማስያዣውን ካልመለሱ ወይም ተገቢ ማሳወቂያ ካልሰጡ እና ተከራዩ ስላልተመለሰው የማስያዣ ገንዘብ ከከሰስዎት ተከራዩ ያስያዘው ገንዘብ እና ወለዱ ሙሉ በሙሉ እንዲመለስለት ብቁ ያልሆነበትን ምክንያት ማረጋገጫ መስጠት ይጠበቅቦታል፡፡ ፍርድ ቤቱ በመጥፎ እምነት ላይ ተመስርተው ያደረጉት ነገር እንደሆነ ከደረሰበት ተከራዩ "ትሪፕል ዳሜጅ" ለተሰኘው የህግ መብት ብቁ በመሆን የዋናውን ገንዘብ ሶስት እጥፍ እንዲጠይቅ ይደረጋል፡፡ "ባድ ፌዝ" ወይም በመጥፎ እምነት የሚለው አባባል ማለት ባልተገኘ ወይም ተዓማኒ ባልሆነ ምክንያት ገንዘቡን አለመመለስን ይመለከታል፡፡ ማስያዣውን መመለስን መርሳት፣ ጥሩ መጥፎ አመለካከት ወይም ታማኝ እምነት በትክክለኛ መንገድ ያደረጉት እንደ መጥፎ እምነት አይቆጠርም፡፡
ከተቀመጠው የደህንነት ማስያዣ በላይ የሆነ ጥፋት አፓርትመንቱ ላይ ቢደርስ ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እችላለሁ?
መክሰስ ይችላሉ በአብዛኛው በአነስተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄዎች እናም ከተቀመጠው የደህንነት ማስያዣ በላይ ለሆነው ጥፋት የፍርድ ውሳኔ ያገኛሉ፡፡
4. በአጠቃላይ ከቤት ስለ ማስወጣት
ተከራዬን ከቤት የማስወጣው እንዴት ነው?
በራስ ፈቃድ ከቤት ማስወጣት በዲ.ሲ ህገወጥ ነው፤ በተከራዮ ተቃራኒ ቆመው ክስ መመስረት እና ተከራዮን ለማስወጣት "ጀጅመንት ኦፍ ፖሴሽን" ማለትም በቤቱ የማዘዝ መብት ፍርድ የግድ ማግኘት ይኖርቦታል፡፡ በቤቶ ላይ የማዘዝ መብቶን ካገኙ በኋላ በዩኤስ ማርሻል ሰርቪስ አማካይነት የማስወጣት ሂደቱን ማካሄድ ይኖርቦታል፤ ከዩኤስ ማርሻል ሰርቪስ ጋር የሚወጣበትን ቀን ከመወሰን ባለፈ ተከራዩ ቤቱን እንዲለቅ ለማድረግ በሚል ሰበብ የተከራዩን ንብረት ማውጣት፣ የቤቱን ቁልፍ መቀየር፣ የቤቱን ሙቀት፣ ውሀ፣ ወይም ሌላ አይነት አገልግሎት ማጥፋት ህገወጥ ተግባር ነው፡፡
ያለ ፍርድ ቤት እውቅና ወይም የዩኤስ ማርሻል ሰርቪስን ሳይጠቀሙ ተከራዮን ከቤት ካስወጡ ህጉን በመጣስዎ ለሚፈጠረው የገንዘብ ጥፋት እና የተከራዩ ንብረት ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ሀላፊነት ይወስዳሉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ትክክለኛውን የፍርድ ቤት ሂደት ተከትለው እስከሚጨርሱ ድረስ ተከራዩ ተመልሶ ቤቱ ውሰጥ እንዲኖር ሊያዝ ይችላል፡፡
ተከራዬን አለወልድኩትም፡፡ ተከራዩን ለማስወጣት ህጋዊ ምክንያት ሊኖረኝ ይገባል?
አዎ፡፡ በዲ.ሲ. አንድን ተከራይ ስለማይወዱት ወይም ስለማይወዷት ብቻ ከቤቶ ማስለቀቅ አይችሉም፡፡ ቢያንስ አንድ ህግ ላይ የተመሰረተ ምክንያት ሊኖርዎ ይገባል፡፡ በጣም የተለመደው ህጋዊ ምክንያቶች የሚባሉት የቤት ኪራይ አለመክፈል እና የሊዙን ህግ መጣስ(ለምሳሌ፤ ሊሱ እየከለከለ ውሻ በቤትዎ አስገብቶ ማኖር)፡፡
ተከራዬን ለማስወጣት ልጠቀማቸው የምችላቸው ህጋዊ ምክንያቶች ምንድ ናቸው?
በህጋዊ መንገድ ተከራይን ለማስወጣት ከሚከተሉት ውስጥ ቢያንስ አንዱ እውነት እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ ማረጋገጫ ማቅረብ ይገባል፡
- ተከራዩ የቤት ኪራዩን ካልከፈለ፤
- ተከራዩ ወይም ነዋሪው የሊዙን የተወሰነ ክፍል ከጣሰ(ለምሳሌ ውሻ ማኖር በሚከለክል ቤት ውሰጥ ውሻ ማስገባት ወይም መኖር እያልተፈቀደላቸው ሰዎችን በቤቱ እንዲኖሩ ማድረግ) ወይም የመኖሪያ ቤት ህግ(ንብረት ማጥፋት ወይም አለማፅዳት)
- ተከራዩ ወይም ነዋሪው በቤቱ ውስጥ ህግ ከተላለፈ፤
- ተከራዩ ወይም ነዋሪው አደገኛ እፅ በቤቱ ውስጥ ካስቀመጠ፤
- ቤቱን ለአፋጣኝ እና የግል ጉዳይ ከፈለጉት፤
- ቤቱን እንደገና ለማደስ ከፈለጉ እና ነገር ግን ያንን ለማድረግ ተከራዩ የግድ መውጣት ካለበት፤
- ቤቱን ማፍረስ ከፈለጉ፤
- ቤቱ በአግባቡ መታደስ ወይም መስተካከል ካለበት፤ ወይም
- ቤቱ ከዚህ በኋላ ለኪራይ አገልግሎት የማይውል ከሆነ፡፡
የሊዙ ግዜ ሲያልቅ ተከራዬን እንዲወጣ ማድረግ እችላለው?
አይ፤ በዲ.ሲ. አንድ ግዜ የሊዙ ግዜ ካለቀ፤ ሊዙ በራሱ ወር ከወር ይቀጥላል፡፡ ሌላው የሊዝ አካል እንደዛው እንደነበረ ይቆያል(ለተከራዩ የፅሁፍ ማሳወቂያ እስካልሰጡት ድረስ የኪራዩን ዋጋ ጨምሮ)፡፡
በለምሳሌ፤ ለአንድ(1) አመት የሚቆይ ሊዝ ከጃኑዋሪ 1 2016 ጀምሮ እስከ ዴሴንበር 31/ 2016 ድረስ ተፈራርመው ከነበረ ሊሱን ከተከራይዎ ጋር ለማሳደስ ባይፈልጉ እንኳ ሊዙ ከጃንዋሪ 17 2017 ጀምሮ ወር ከወር ይቀጥላል፡፡ በሌላ ቋንቋ፤ ተከራይዎን ሌላ ህጋዊ የሆነ ምክንያት ከሌሎት በስተቀር የሊሱ ግዜ ስላለቀ ብቻ ከቤትዎ ማስወጣት አይችሉም፡፡
የፅሁፍ የሊዝ ስምምነት ከተከራዬ ጋር አልፈፀምኩም ወይም ደግሞ ሊዜ "ወር -ከ-ወር" የሚታደስ ነው፡፡ ተከራዬን ማስወጣት እችላለሁ?
ሌላ ህጋዊ የሆነ ምክንያት ከሌሎት በስተቀር ከቤትዎ ማስወጣት አይችሉም፡፡ ምንም አይነት የውል ስምምነት ባይኖሮ ወይም በወር -ከ- ወር ሊዝ ስምምነት ውስጥ ቢሆኑ ተከራዮን ማስወጣት የሚችሉት ህጋዊ የሆነ ምክንያት ካሎት ብቻ ነው፡፡
ተከራዬን ለማስወጣት ክስ መመስረት ፈልጋለሁ፡፡ ክስ ከመመስረቴ በፊት የ30-ቀን ማሳወቂያውን መስጠት አለብኝ?
በሕጉ ለውጦች ምክንያት ይህ ክፍል እየተሻሻለ ነው.
በዲ.ሲ. የቤት ባለ ንብረት ቤቱን ለማስለቀቅ ክስ ከመመስረቱ በፊት ለተከራይ መስጠት የሚጠበቅበት ማሳወቂያ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ይሆናል "ኖቲስ ቱ ቁዊት"፣ "ኖቲስ ቶ ቁዊት ኦር ቫኬት"፣ "ኖቲስ ቱ ኪዩር ኦር ቫኬት"፣ ወይም "ኖቲስ ቱ ኮሬክት" ይህ ማሳወቂያ ተከራዮን የቤት ኪራይ ካለመክፈል እና አደገኛ እፅ ቤት ውስጥ ከማስቀመጥ ውጪ በየትኛውም ምክንያት ከቤትዎ ከማስወጣትዎ በፊት ለተከራይዎ እንዲሰጡ የግድ ይጠበቅቦታል፡፡ በአብዛኛው፤ የ30-ቀን ማሳወቂያ ያስፈልጋል ነገር ግን ለአንዳንድ ጉዳዮች የቤት ባለ ንብረት እስከ 90፣ 120 ወይም 180-ቀናት እንዲሰጥ ሊጠበቅበት ይችላል፡፡
ተከራይዎ እንዲወጣ የፈለጉት ቤት ውስጥ አደገኛ እፅ በማስቀመጡ ምክንያት ከሆነ ይህን አይነት ቅድመ ማሳወቂያ ሊሰጡ አይጠበቅቦትም፡፡
ተከራይዎ እንዲወጣ የፈለጉት የቤት ኪራይ መክፈል ባለ መቻሉ ከሆነ ይህን አይነት ቅድመ ማሳወቂያ ሊሰጡ አይጠበቅቦትም፡፡ ተከራይዎ ቤቱን እንዲለቅ ከመጠየቁ በፊት ይሄን አይነት ማሳወቂያ የማግኘት መብቱን አሳልፎ ሰጥቶ ከነበረ የሊዝ ስምምነትዎን መልሰው ይመልከቱ፡፡ ሊዙ የተወሰነ ቋንቋ ሊኖረው ይችላል እንደ "ይህ ተከራይ ማቋረጥ ወይም መውጣት እንዳለበት ተከራይ ማሳሰቢያ ሲሆን ይህም ቤቱን ከመልቀቁ በፊት ለተከራዮች ተጨማሪ ማሳሰቢያ እንዲሰጥ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስፈርት ያስወግዳል"
- ሊዙ ላይ ይሄ ካለ፤ የተከራይዎ መልቀቂያ ምክንያት የቤት ኪራይ አለመክፈል ከሆነ የማቆም ማሳወቂያ ወይም ኖቲስ ቱ ኩዊት መስጠት አይጠበቅቦትም፡፡ ተከራይዎ ማሳወቂያ የማግኘት መብቱን ለመተው ሊስማማ የሚችለው ክፍያ መክፈል ሳይችል ለሚቀርበት ሁኔታ ብቻ ነው፡፡
- ሊዙ ተመሳሳይ ትርጓሜ ከሌለው፤ ተከራዩ ይህን ማሳወቂያ የማግኘት መብቱን አልተወም ማለት ነው ስለዚህ ለተከራይ የማቆም ማሳወቂያ ሊሰጡ ይገባል፡፡
- ተከራዩ ይህንን ማሳወቂያ የማግኘት መብቱን መተውን እና አለመተውን እርግጠኛ ካልሆኑ ከጠበቃ ጋር መነጋገር ይኖርቦታል፡፡
ያስታውሱ፤ ምንም እንኳ ማሳወቂያው ተከራዩን እንዲለቅ የሚያስገድድ ቢሆንም ከፍርድ ቤት የባለቤትነት ፈቃድ የተከራዩን ቤቱን እንዲለቅ ለማድረግ ማስገደድ አይችሉም፡፡
ለሊዝ ህግ ጥሰት ማሳወቂያዎች "ኖቲስ ቱ ኩዊት" ፣ "ኖቲስ ቱ ኩዊት ኦር ቫኬት" ወይም "ኖቲስ ቶ ኪዩር ኦር ቫኬት" የሆነ አይነት ቅድመ ሁኔታ ይኖር ይሆን?
አዎ፡፡ የእነዚህ ማሳወቂያዎች ቅድመ ሁኔታዎች በጣም ጥብቅ ናቸው፡፡ ወደ ማስለቀቅ ለማለፍ እና ሂደቱን ለማስቀጠል እርሶ ለተከራዩ ተገቢ የሆነ ቅድመ ማሳወቂያ ሊሰጡ ይገባል፡፡ አለበለዚያ፤ ክሱ በፍርድቤት ውድቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ቅድመ ሁኔታዎቹም፡
ለተከራዩ እንዴት የመኖሪያ ቤቱን ወይም የሊዙን ህግ እንደጣሱ በጣም ግልፅ የሆነ መረጃ መስጠት፤
ለተከራዬ የህግ ጥሰቱን እንዴት ማስተካከል እንደሚችል ግልፅ የሆነ መረጃ መስጠት፤
ለተከራዩ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ቢያንስ የ30 ቀን ግዜ መስጠት፤ እና
ማስታወቂያው በእንግሊዘኛ እና በስፓኒሽኛ መፃፍ ይኖርበታል፡፡
በባዶ ማሳወቂያ ከመመሪያ ጋር እዚይገኛል፡፡
በሆነ መንገድ "ኖቲስ ቱ ኩዊት" ፣ "ኖቲስ ቱ ኩዊት ኦር ቫኬት" ወይም "ኖቲስ ቶ ኪዩር ኦር ቫኬት"ን ለተከራዬ ማድረስ ይኖርብኝ ይሆን?
አዎ፡፡ ለተከራዮ እራሶ መስጠት ወይም መላክ ይችላሉ ወይም ደግሞ ሌላ ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው እንዲያደርግሎ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህንን በዚህ ማድረግ ይችላሉ፡
የግል አገልግሎት- የማሳወቂያ ወረቀቶችን በቀጥታ ለተከራዩ የሚሰጥ፤
ተቀያሪ አገልግሎት- በክፍሉ ውስጥ የሚኖር እድሜው ከ16 ዓመት በላይ ለሆነ ግለሰብ ግልባጩን መስጠት፤ ወይም
የተመዘገበ ፖስታ- የተከራዩን ግልባጭ በተመዘገበ ፖስታ በኩል መላክ፡፡ የተመዘገበ ፖስታን ከተጠቀሙ ፖስታውን ለመቀበል ተከራይ ራሱ ወይም ራሷ የግድ መፈረም አለባቸው እንዲሁምእርሶ የግድ ከፖስታ ቤቱ ተከራይ ፖስታውን ስለመቀበሉ/ሏ የፈረሙበትን ማረጋገጫ ማግኘት አለቦት፤ ወይም
መለጠፍ እና መላክ - ተከራዩን በአካል አጊኝቶ ለመስጠት ከሁለት(2) ግዜ ሙከራ በኋላ የማሳወቂያውን ግልባጭ በተከራዩ ቤት በር ላይ ማያያዝ ማጣበቅ ወይም መለጠፍ ይችላሉ፡፡ የማሳወቂያው ሌላ ግልባጭ በአንደኛ ደረጃ ፖስታ በሩ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉ በሶስት (3)ቀናት ውስጥ ለተከራዩ የግድ ሊላክለት ይገባል፡፡
በሂሳብ አለመክፈል ጋር የተያያዘ ካልሆነ በቀር፤ በ1800 Martin Luther King, Jr. Avenue, SE, Washington, D.C. 20020 በሚገኘው የሀውሲንግ ሬጉሌሽን አድሚኒስትሬሽን ማሳወቂያውን ለተከራይ ከሰጡበት ቀን አንስቶ ባሉ 5 የካሌንደር ቀናት ግልባጭ ለሬንት አድሚኒስትሬተር የግድ መስጠት ይኖርቦታል፡፡ ስልክ ቁጥሩም (202) 442-9505 ነው፡፡ ተከራዬ ከሴክሽን 8 ሀውሲንግ ቾይስ ቫውቸር ፕሮግራም የኪራይ ድጋፍ የሚያገኝ ከሆነ በ 1133 North Capitol Street, NE Washington, DC 20002 ለሚገኘው የዲ.ሲ. ሀውሲንግ አውቶሪቲ አንድ ግልባጭ የግድ መላክ ይኖርቦታል፡፡
ለተከራዬ "ኖቲስ ቱ ኩዊት" ፣ "ኖቲስ ቱ ኩዊት ኦር ቫኬት" ወይም "ኖቲስ ቱ ኪዩር ኦር ቫኬት" ሰጥቼዋለሁ/ሰጥቼያታለሁ ነገር ግን ከቤቴ አልለቀቁም፡፡ አሁን ምን ማድረግ እችላለሁ?
ለተከራይዎ "ኖቲስ ቱ ኩዊት" ፣ "ኖቲስ ቱ ኩዊት ኦር ቫኬት" ወይም "ኖቲስ ቱ ኪዩር ኦር ቫኬት" ከሰጡ በኋላ በማሳወቂያው ላይ ያለው ግዜ እስከሚያልቅ መጠበቅ ይኖርቦታል፡፡
ማሳወቂያው ስለ ኪራይ አመክፈል ከሆነ እና ተከራይዎ የክፍያ ሂሳቡን አጠናቆ ካልጨረሰ (ማሳወቂያው ሲደርሰው ወይም ከዚያም በኋላ) በአከራይ እና ተከራይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዲ.ሲ. ቅርንጫፍ በባለቤትነት ውሳኔ ለመስጠት ለመጠየቅ የንብረት ባለይዞታነት ቅሬታ ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ማሳወቂያዎ በፅሁፍ የተቀመጠ የሊዝ ስምምነት ወይም የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት ጋር የተገናኘ ከሆነ እ" ንዲሁም በማሳወቂያው ላይ በተገለፀው መሰረት ተከራዩ ማስተካከያ ካላደረገ፤ ከቀነ ገደቡ በኋላ ማስተካከል ቢችሉ እንኳ በአከራይ እና ተከራይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዲ.ሲ. ቅርንጫፍ በባለቤትነት ውሳኔ ለመስጠት ለመጠየቅ የንብረት ባለይዞታነት ቅሬታ ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ለ "ቅሬታው" የተወሰነ አይነት ቅድመ ሁኔታ አለ?
አዎ፡፡ ጉዳይዎ ወደ ቀጣዩ ሂደት እንዲያልፍ በአግባቡ የተሞላ የፍርድ ቤቱን መደበኛ ቅፅ መጠቀም ይኖርቦታል፡፡ የግድ ማድረግ ያለብዎ፡
- ይዘውት ለሚመጡት ጉዳይ ትክክለኛውን ቅፅ መጠቀም ለመኖሪያ ቤት ባለንብረቶች ሶስት አይነት ቅፆች አሉ፡፡
- Form 1A በኪራይ ክፍያ ወደኋላ የቀረ ተከራያቸውን እያስወጡ ላሉ አከራዮች የሚያገለግል ቅፅ ነው፡፡
- Form 1B ከባድ የሆነ እፅ ቤታቸው ውስጥ በማስገባታቸው እና በተወሰነ ሌላ አይነት ምክንያት ኖቲስ ቱ ኮሬክት/ቫኬት የማስተካከያ ማሳወቂያ ከደረሳቸው በኋላ ማስተካከያ ያላደረጉ ተከራዮችን እያስወጡ ላሉ አከራዮች የሚያገለግል ቅፅ ነው፡፡
- Form 1C በኪራይ ክፍያ ወደኋላ የቀሩ እና በተወሰነ ሌላ አይነት ምክንያት ተከራዮችን እያስወጡ ላሉ አከራዮች የሚያገለግል ቅፅ ነው፡፡
- ይህንን ቅፅ በመጠቀም መጥሪያውን ይሙሉ Form 1S .
- የተከራዮችዎን ስም እና አድራሻ በትክክል ይሙሉ(የአፓርትመንት ወይም የክፍል ቁጥርን ጨምሮ ካለ) እና የአድራሻቸውን ጎራ (NE፣ NW፣ SE፣ ወይም SW)፤
- በተለየ መልኩ ተከራይዎን ለምን ለማስወጣት እንደሚከሱ ምክንያትዎን(ኦቾን) እና
- ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን የቤት ባለመብትነቶን የማግኘት መብቶንም ይጠይቁ፡፡
- ፊርማዎን ያስፍሩ፡፡
- እንደ ኖቲስ ቱ ኮሬክት ኦር ቫኬት ማለትም አስተካክል ወይም ልቀቅ ማሳወቂያ መድረሱን የሚያሳይ ማስረጃ ያሉ ቅፁ የሚጠይቃቸውን ማናቸውንም አይነት ሰነዶች አብረው ያያይዙ፡፡
የቅሬታ ማቅረቢያው ክፍያ 15.00 $ ነው፡፡
ቅሬታዎን በዲ.ሲ. ጠቅላይ ፍርድ ቤት B, 510 4th Street, NW, Washington, D.C. 20001 ክፍል 110 በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአከራይ እና ተከራይ ቅርንጫፍ ፀሀፊ ቢሮ ማስገባት ይኖርቦታል፡፡
ሁሉም የሚሞሉ ቅጾች ከነመመሪያቸው እዚህ ይገኛሉ፡፡
ፍርድ ቤት መሄድ ያለብኝ መቼ ነው?
ቅሬታውን ለማስገባት ፍርድ ቤት ሲሄዱ፤ ፀሀፊው ቅሬታውን ካስገቡበት ቀን ቢያንስ በሶስት ሳምንት ግዜ ውስጥ የመጀመሪያ የችሎት መስሚያ ቀን ይመድብሎታል፡፡ ቅሬታ የሚያስገቡት ስለ ከባድ የእፅ ጉዳይ ከሆነ ቀደም ያለ ቀን ሊመደብልዎ ይችላል፡፡
በሆነ መንገድ "ቅሬታውዬን" ለተከራዬ እጅ ማድረስ ይኖርብኛል?
አዎ፡፡ የቅሬታ ማመልከቻዎን እርሶ በቀጥታ መስጠት ወይም ግልባጭ መላክ አይችሉም፡፡ ሌላ ሰው(የ "ሂደቱ አስፈፃሚ") ቢያንስ እድሜው 18 ዓመት የሆነ ለተከራዮ መልእክቱን ማድረስ አለበት፡፡ ለተከራይዎ በሚከተለው መልክ መልእክቱን ማድረስ ይችላሉ፡
- የግል አገልግሎት- የቅሬታ ወረቀቶችን በቀጥታ ለተከራዩ የሚሰጥ፤
- ተቀያሪ አገልግሎት- በቤቱ ውስጥ የሚኖር እድሜው ከ16 ዓመት በላይ ለሆነ ግለሰብ ግልባጩን መስጠት፤ ወይም
- መለጠፍ እና መላክ - የግል አገልግሎት ሰጪው ተከራዩን በአካል አጊኝቶ ለመስጠት ከሁለት(2) ግዜ ሙከራ በኋላ የማሳወቂያውን ግልባጭ በተከራዩ ቤት በር ላይ ማያያዝ ማጣበቅ ወይም መለጠፍ ይችላሉ፡፡ የማሳወቂያው ሌላ ግልባጭ በአንደኛ ደረጃ ፖስታ በሩ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉ በሶስት (3) ቀናት ግዜ ውስጥ ለተከራዩ የግድ ሊልኩለት ይገባል፡፡
ቅሬታዎን ስለማድረስ የፍርድ ቤት መመረሪየያ እዚ ይገኛል፡፡
ተከራዬ ከሴክሽን 8 ሀውሲንግ ቾይስ ቫውቸር ፕሮግራም የኪራይ ድጋፍ የሚያገኝ ከሆነ በ 1133 North Capitol Street, NE Washington, DC 20002 ለሚገኘው የዲ.ሲ. ሀውሲንግ አውቶሪቲ የቅሬታውን ግልባጭ የግድ መላክ ይኖርቦታል፡፡
የሂደቱ አስፈፃሚ ቅሬታዎን ካደረሰልዎ በኋላ እርሶ ወይም የሂደቱ አስፈፃሚ ለፀሀፊው በግልፅ የሂደቱ አስፈፃሚ እንዴት አድርጎ ለተከራዩ ወረቀቱን እንዳደረሰ የሚገልፅ የአገልግሎቱን ምስክርነት በፅሁፍ ማስገባት ይኖርቦታል፡፡ ምስክርነቱ ከመጀመሪያው የፍርድ ችሎት መስሚያ ቀን ቢያንስ ከአምስት ቀናት በፊት መግባት አለበት፡፡
5. ወደ ፍርድ ቤት መሄድ ለማስወጣት ጉዳይ
የርቀት ፍርድ ቤት ሥራዎች የጉዳይ መርሐግብር ጊዜን ሊለውጡ ይችላሉ። እባክዎን ስለጉዳይዎ ማንኛውንም ጥያቄ ወደ ጸሃፊው ቢሮ ይደውሉ
ቅሬታዬን አስገብቻለው ተከራዬን ለማስወጣት፡፡ ወደ ፍርድ ቤት ስሄድ ምን ይፈጠራል?
በጥዋት 9፡00 AM በፍርድቤቱ ክፍል ደርሰው እየጠበቁ መሆኖን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ዳኛው ሂደቱ ምን እንደሚመስል እና ምን አይነት እገዛ እንደሚኖር ያስረዳሉ፡፡ እንግሊዘኛ የማይናገሩ ከሆነ ወይም መስማት የማይችሉ ወይም የመስማት ችግር ያለብዎ ከሆነ የፍርድ ቤቱ ክፍል ፀሀፊን ማስተዋወቅ ከመጀመሩ በፊት መንገሮን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡
በመቀጠል፤ ፀሀፊው የሁሉንም በቀጠሮው ቀን እንዲቀርቡ የተጠየኩ አካላትን ስም ዝርዝር ያነባል፡፡ ስምዎ ሲጠራ "እዚህ ነኝ" ወይም "ተገኝቻለሁ" በማለት እና ስሞትን በመጥራት መመለስ ይጠበቅቦታል፡፡ ፀሀፊውን በደንብ እንደሚሰሙ ያረጋግጡ፡፡ የማይሰማዎ ከሆነ እጅዎን በማውጣት ለፀሀፊው ያሳውቁ፡፡ ስምዎ ሲጠራ ካለፍዎ እና ሳይመልሱ ከቀሩ ጉዳይዎ ሊሰረዝ ይችላል፡፡ አንድ ተሟጋች ጉዳዩ ሲጠራ ካልመለሰ፤ ፀሀፊውን ተከራዩ ላይ "ነባሪ" ለማስገባት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሁሉም ሰው ስም በሚጠራበት ወቅት ስምዎ ካልተሰማዎ ወይም ፍርድ ቤት አርፍደው ከደረሱ እና ስምዎ መጠራቱን እርግጠኛ ካልሆኑ የስም መጥራ ሂደቱ እንዳለቀ በፀሀፊው ቢሮ(ክፍል110) ወደ መስኮት 4 በመሄድ ፀሀፊው መኖርዎን እንዳወቀ ያረጋግጡ፡፡
አንድ ግዜ ፀሀፊው ሁሉንም ጠርቶ ከጨረሰ በኋላ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ወይም ከዛ በላይ የሆኑትን ነገሮች ለማድረግ መወሰን ይችላሉ፡
- ገጉደዳየዩነን መጨረሰስ ከ ተከራዮ ወይም ከ ተከራይዎጠበቃ ጋር፡፡
- በእርሶ ጉዳይ ላይ ዳኛው ውሳኔ እንዲሰጥ መጠየቅ እርሶ ህጋዊ ምክንያታዊነት ካሎት ተከራዮን ለማስወጣትእና ተከራዩ በእርሶ ጥያቄ ላይ መከላከያ ማቅረብ ካልቻለ፤ ዳኛው የባለቤትነት መብቶን የማስከበር ውሳኔ እና የሚገባዎት ከሆነም የቤት ኪራዮን በአፋጣኝ እንዲከፍሎ በመጀመሪያው ችሎት ሊወስንሎ ይችላል፡፡ ተከራይዎ መከላከያ ካለው ጉዳዩን ተጣርቶ በሌላ ቀን እንዲቀርብ ሊቀጠር ይችላል፡፡
- ጉዳዮን ፍርድ ቤቱ በመደበው አደራዳሪ በኩል "ይደራደሩ"፡፡ አደራዳሪው በሁለቱም ወገኖች በኩል ያለውን ሀሳብ ሰምቶ ጉዳዩን እልባት እንዲያገኝ ይረዳል፡፡ ነገር ግን መረዳት ካልቻሉ ወይም በአደራዳሪው የተነገርዎ ነገር ካልገባዎየመደራደሪያ ነጥቦቹን መቀበለል ወይም ጉዳዩን መጨረስ አይጠበቅቦትም ከጠበቃ ጋር መማከር ይኖርቦታል፡፡
- የመከላከያ ትዕዛዝ ይጠይቁ ወይም የመከላከያ ደንቦችዎን ያስቀምጡተከራዩጉዳዩ እንዲቀጥል ወይም በሌላ ቀን እንዲታይ ከጠየቀ፡፡ «መብትዎን ካስጠበቁ»፤ አንድ የመከላከያ ትዕዛዝ ሲገባ ቀደም ብለው በጠየቁት ቀን ወደ ኋላ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል፡፡
እርስዎ ወይም ተከራዩ (ወይም የተከራይ ጠበቃ) ተከራዮ የወደፊት የቤት ኪራይ ክፍያውን በፍርድ ቤት መዝገብ ቤት እንዲያስቀምጡ የሚጠይቅ "የመከላከያ ትዕዛዝ" መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ "የመከላከያ ትዕዛዝ" የሚል ርእስ ያለበትን ክፍል መመልከት ይችላሉ፡፡
በፍርድ ቤት የመጀመሪያ ቀን ቆይታ ምን ሊፈጠር እንደሚችል የበለጠ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጋርይጫኑ፡፡
በቀጠሮዬ ቀን ፍርድ ቤት መቅረብ ባልችል ምን ይፈጠራል?
በአፋጣኝ ለፍርድ ቤቱ ፀሀፊ በ(202) 879-4879 በመደወል ለምን መገኘት እንዳልቻሉ ያሳውቁ፡፡ ፀሀፊውን ስሙን ወይም ስሟን በመጠየቅ ይፃፉ፡፡ በተጨማሪም ለተከራይዎ ወይም ለተከራይዎ ጠበቃ በመደወል መገኘት እንደማይችሉ ማሳወቅ ይኖርቦታል፡፡ ከፍርዱ ቀን በፊት ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ግዜ ካገኙ በእለቱ በፍርድ ቤት መገኘት የማይችሉበትን ምክንያት ጠቅሰው ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ፀሀፊው ተለዋጭ ቀን መስጠት ካልቻለ ወደ ፍርድ ቤቱ በተቻለ ፍጥነት በመሄድ ምን እንደተፈጠረ ያጣሩ፡፡ ወደ ፍርድ ቤት ቢደውሉም እንኳ ዳኛው ክስዎን ሊያነሳብዎ ይችላል፡፡ በቦታው መገኘት ባለመቻልዎ ክሱ ከተነሳ "በፍርድ እጦት የተነሳ ክስ" ይባላል እና አብዛኛውን ጊዜ ጉዳዩን በድጋሚ ለማስከፈት ወይም አዲስ ጉዳይ ለመክፈት ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ::
ምን ይፈጠራል ተከራይዎ ፍርድ ቤት ካልቀረበ?
በመጀመሪያ የችሎት ቀን ተከራይዎ ፍርድ ቤት ካልቀረበ በጥዋቱ ጥሪ ወቅት ተከራዩ ላይ "ነባሪ" ለማስገባት መጠየቅ ይችላሉ፡፡ በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ነባሪ ማለትተከሳሹበውትድርናው ውስጥ አለመሆኑን የሚያረጋግጡ የፍርድ ቤት ሰነዶችን ካስገቡ በኋላ ለንብረት የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ ይደረጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ተከራዩ ወደ ፍርድ ቤት ለመምጣት ካልቻሉ ወይም ተከራዩ ወደ ፍርድ ቤት ቢመጡም ለቀሪው ወይም ለቀጣዩ ችሎት ወደ ፍርድ ቤት ተመልሶ ካልመጣ የጉዳይዎ ማረጋገጫ ከማግኘትዎ በፊት ለርስዎ ጉዳይ በፍርድ ቤት ( "ex parte" ማረጋገጫ የሚባለውን) ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልግዎታል ፡፡ ማረጋገጫ የሞያስፈልግ ከሆነ ዳኛው ለሌላ የችሎት ቀን ከሁለት ሳምንት በኋላ ለመመለስ ቀጠሮ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ተከራዩ ወደ ፍርድ ቤት ካልመጣ፤ ፀሀፊው በአብዛኛው ከጥዋት ጥሪ በኋላ ዳኛ ፊት መቅረብ እንደሚፈልጉ ለማወቅ ይጠይቆታል፡፡ እርግጠኛ ካልሆኑ የጥዋት ጥሪው እንደተጠናቀቀ ፀሀፊውን ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለብዎ እንዲያማክሮ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ምን ይፈጠራል ተከራዩ ሁሉንም ክፍያውን ፍርድ ቤት ከመሄዳችን በፊት ቢከፍል?
ተከራይዎን ቤቱን እንዲለቅ የከሰሱት የቤት ኪራይ ባለመክፈሉ ከሆነ እና ተከራዩ የቤት ኪራዩን በሙሉ ፍርድ ቤት ከመቆሙ በፊት በየትኛውም ሁኔታ ላይ ከከፈለ ክሱን እንዲያነሱ ይጠበቅቦታል፡፡ ተከራይዎ በድጋሚ መክፈል ካቆመ፤ የሚቀጥለውን ወርም ቢሆን የማስወጣት ሂደቱን ከእንደገና መጀመር ይችላ፡፡ የፍርድ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ክፍያውን ከፍሎ ካጠናቀቀ የሊሱ ህግ ቢያዘውም እንኳ ተከራዩ የክስ ሂደቱን ወጪ መክፈል አይጠበቅበትም፡፡ (ተከራዮች በዳኛ ትእዛዝ ካልተሰጣቸው በቀር የሊስ ስምምነታችሁ እንኳ ቢያዝ የፍርድ ሂደት ወጪዎችን መክፈል አይጠበቅባቸውም፡፡)
6. የተከራዮች ምላሾች እና ሌሎች አፀፋዎች
ተከራዩምላሹን አስገብቷል፡፡ "ምላሽ" ምንድ ነው?
ምላሽ ተከራዩ ራሱን ለመከላከል ተጨማሪ የችሎት ቀን ለማግኘት በፅሁፍ የሚያስቀምጠው ሃሳብ ነው፡፡ ተከራዩ ሊከስዎት ከፈለገ የእሱ ወይም የእሷ ምላሽ "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ""ማካካሻ"፣ እና/ወይም "መተኪያ"ን ሊያካትት ይችላል፡፡ ተከራዩ ፍርደ ሸንጎን ከፈለገ(ከ "ፍርደ ዳኛ"ከዳኛ ፊት ከመቆም)፤ ምላሹ "የሸንጎ ጥያቄ"ንም ሊያካትት ይችላል፡፡
ተከራዩ ምለሹን በፅሁፍ ማስገባት ይጠበቅበታል?
ተከራዩ "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ" ፣ "ማካካሻ"፣ እና/ወይም "መተኪያ"፤ ወይም ፍርደ ሸንጎን (ከ "ፍርደ ዳኛ" ከዳኛ ፊት ከመቆም) እስካልጠየቀ ድረስ የጽሁፍ ምላሽ በአከራይ ተከራይ ፍርድቤት ውስጥ አይጠበቅም፡፡
"የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ" ምንድ ነው?
ክፍያውን ባለመክፈሉ የተነሳ ተከራይዎን ከቤትዎ እንዲወጣ ከሰው ከነበረ፤ ተከራዮ እሱ ወይም እሷ የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት በመኖሩ የተነሳ በጣም ከፍተኛ የሆነ ወጪ በሌላ ቤት ኪራይ ሲያወጣ እንደነበር በመግለፅ "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ" በእርሶ ላይ ሊያነሳ ይችላል፤ እና ፍርድ ቤቱ ወጣውን ወጪ እንዲያስመልስለት እና መክፈል ይጠበቅበት የነበረውን እና የእርሶ የሆነውን ገንዘብ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ተከራዩ ገንዘቡ ተመላሽ እንዲሆንለት ወይ እስከዛ ድረስ በኪራይ ቤቱ ውስጥ የኖረበትን ወይም እየተቀነሰ በ 3 (ሶስት) ተከፋፍሎ እንዲከፈለው ሊጠይቅ ይችላል፡፡ በአብዛኛው ተከራዮች የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ የሚያቀርቡት የተከራዩት ቤት ሁኔታ በጣም የከፋ ሆኖ ለረዥም ግዜ የቆየ ከነበረ ብቻ ነው፡፡ ዳኛው ተከራዩን እንዳይከፍል ምህረት እስካላደረገለት ድረስ የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ ለማቅረብ $10 ያስከፍላል፡፡
ተከራዩ "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ"፣ "ማካካሻ"፣ ወይም "መተኪያ"ን ካመለከተ በስተቀር፤ ቅሬታዎን ለተከራዩ በግሎ ለማቅረብ ሞክረው ካልነበረ ከተከራዩ በተቃራኒ የገንዘብ ውሳኔ አያገኙም፡፡ ስለዚህ፤ የግል አገልግሎት ባይኖሮት እንኳ ተከራይዎ የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ፣ "ማካካሻ"፣ ወይም "መተኪያ"ን ካመለከተ የገንዘብ ውሳኔ ከተከራይዎ በተቃራኒ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
"ማካካሻ" ምንድ ነው?
ክፍያውን ባለመክፈሉ የተነሳ ተከራይዎን ከቤትዎ እንዲወጣ ከሰው ከነበረ፤ ተከራዮ እሱ ወይም እሷ የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት በመኖሩ የተነሳ በጣም ከፍተኛ የሆነ ወጪ በሌላ ቤት ኪራይ ሲያወጣ እንደነበር በመግለፅ "ማካካሻ" ሊጠይቅ ይችላል፤ እና ፍርድ ቤቱ ወጣውን ወጪ እንዲያስመልስለት ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ማካካሻም የዚህ "ከፍተኛ ክፍያ" መጠን ከተከራዩ መክፈል ካለበት መጠን ላይ እንዲቀነስ ይጠይቃል፡፡ ተከራዩ እስከዛሬ ድረስ በኪራይ ቤቱ ውስጥ የኖረበትን ግዜ ታስቦ ከሁሉም ላይ እንዲቀነስ በቤቱ ውስጥ የኖረው ከ 3 (ሶስት) በላይ ቢሆንም እንኳ ገንዘቡ ተቀናሽ እንዲሆንለት ሊጠይቅ ይችላል፡፡ በአብዛኛው ተከራዮች የማካካሻ ጥያቄ የሚያቀርቡት የተከራዩት ቤት ሁኔታ በጣም የከፋ ሆኖ ለረዥም ግዜ የቆየ ከነበረ ብቻ ነው፡፡ ለማካካሻ ጥያቄ ክፍያ የለውም፡፡
ተከራዩ "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ"፣ "ማካካሻ"፣ ወይም "መተኪያ"ን ካመለከተ በስተቀር፤ ቅሬታዎን ለተከራዩ በግሎ ለማቅረብ ሞክረው ካልነበረ ከተከራዩ በተቃራኒ የገንዘብ ውሳኔ አያገኙም፡፡ ስለዚህ፤ የግል አገልግሎት ባይኖሮት እንኳ ተከራይዎ የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ፣ "ማካካሻ"፣ ወይም "መተኪያ"ን ካመለከተ የገንዘብ ውሳኔ ከተከራይዎ በተቃራኒ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
"መተኪያ" ምንድ ነው?
ክፍያውን ባለመክፈሉ የተነሳ ተከራይዎን ከቤትዎ እንዲወጣ ከሰው ከነበረ፤ ተከራዮ ቤቱን በሚጠበቅበት ደረጃ ለማቆየት እሱ ወይም እሷ የመኖሪያ ቤቱ ላይ እድሳት በማድረግ ወይም እቃ ለመግዛቱ/ቷ "መተኪያ" ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ይህም በተደጋጋሚ እድሳት እንዲደረግ በተከራዩ ቢጠየቁም ባለማድረግዎ ተከራይ በራሱ አዲስ ስቶቭ መግዛትን ወይም የመፀዳጃ ቤት እቃ መቀየርን ያካትታል፡፡ መተኪያ ተከታዩ ለእድሳት እና ለግዢ በአጠቃላይ ያወጣው ወጪ ለእርሶ መክፈል ከሚገባው ገንዘብ ላይ ተቀንሶ እንዲከፈል ይጠይቃል፡፡ ተከራዩ እነዚህን ወጪዎች ወይ በኪራይ ቤቱ ውስጥ የኖረበትን ግዜ ላይ እየተቀነሰ ወይም በ 3 (ሶስት) ተከፋፍሎ እንዲከፈለው ሊጠይቅ ይችላል፡፡ መተኪያን ለመጠየቅ ምንም አይነት ክፍያ የለውም፡፡
ተከራዩ "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ"፣ "ማካካሻ"፣ ወይም "መተኪያ"ን ካመለከተ በስተቀር፤ ቅሬታዎን ለተከራዩ በግሎ ለማቅረብ ሞክረው ካልነበረ ከተከራዩ በተቃራኒ የገንዘብ ውሳኔ አያገኙም፡፡ ስለዚህ፤ የግል አገልግሎት ባይኖሮት እንኳ ተከራይዎ የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ፣ "ማካካሻ"፣ ወይም "መተኪያ"ን ካመለከተ የገንዘብ ውሳኔ ከተከራይዎ በተቃራኒ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ስለ ምላሾቹ "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ"፣ "ማካካሻ"፣ ወይም "መተኪያ"ን የበለጠ ለመረዳት እዚህ ይጫኑ፡፡
7. የተከራይ መከላከያዎች
አንዳንድ የቤት ኪራይ ላለመክፈል መከላከያዎችተከራዮችየሚያነሷቸው ምን ምን ናቸው?
አንዳንድ ግዜ ተከራዮች ስራ በመልቀቃቸው የተነሳ ወይም በህመም ምክንያት ያልታሰበ የህክምና ክፍያ መክፈል ኖሮባቸው የቤት ኪራይ መክፈል ያቅታቸዋል፡፡ ተከራዩ ለቤት ኪራይ መክፈል የሚችለው ገንዘብ የሌለው የመሆኑ እውነታ ለተከራዩ እንደ ህጋዊ መከለላከያ ነጥብ ሊሆን አይችልም፡፡
ነገር ግን፤ ክፍያውን ያልከፈለበት ዋነኛ ምክንያት ባይሆንም እንኳ ተከራዩ ቤቱን ከመልቀቅ የሚያድኑት ህጋዊ የሆኑ መከላከያዎችን ማቅረብ ይችላል፤ የተወሰኑት ህጋዊ መከላከያዎች የሚከተሉት ናቸው፡
- የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት - ከባድ የሆኑ ችግሮች በተከራዩቤት ውስጥ ነበሩ ተከራዩክፍያውን ያልከፈለ ወቅትየቤቱ አከራይየሚያውቀው ወይም እያወቀ ነገር ግን ማስተካከል ያልቻላቸው እንዲሁምበተከራዩወይምበተከራዩበቤተሰቦች ወይም በእንግዶች ምክንያት ያልተፈጠሩ ወይም ከባድ ችግሮችን ከሙቀቱ ጋር፣ ከሙቅ ውሀ ጋር፣ የወጥ ቤት እቃዎች፣ የመታጠቢያ ቤት ቁሳቁሶች፣ ፍሰቶች፣ ነፍሳት እና ፣ ወለሎች ግድግዳዎች እና የመሳሰሉት፡፡
- ልክ ያልሆነ መጠን -ተከራዩ የሚባለውን ያክል ገንዘብ የለበትም አከራዩ ያለውን ያክል ምክንያቱም አከራዩ እየከሰሰው ያለው ተከራዩን ከዚህ ቀደም ተከራይከፍሎ ስለነበረውም ጭምር ነው፡፡
- ህገ ወጥ የክፍያ ደረጃ - ተከራዩ የተባለውን ያክል ገንዘብ የለበትም አከራዩ ያለውን ያክል ምክንያቱም አከራዩ በየጊዜው የሚቀበለው ከተከራዩ ላይ ህገወጥ የሆነ የክፍያ መጠን ነው፡፡
- ኖቲስ ቱ ኩዊት አልደረሰውም ወይም ጥያቄው አልቀረበም-ተከራዩ መብቱን አሳልፎ አልሰጠም ነበር፤ ኖቲስ ቱ ኩዊት ለመቀበል እንዲሁም ተከራዩ አልደረሰውም ኖቲስ ቱ ኩዊት ከመከሰሱ በፊት ቤቱን እንዲለቅ የቅሬታ መግለጫ ማሳወቂያ ሲደርሰው፡፡
- ኖቲስ ቱ ኩዊት-አንድተከራይማግኘት አለበትኖቲስ ቱ ኩዊት ከመከሰሱ በፊት ቤቱን እንዲለቅ የቅሬታ ደብዳቤ እንዲደርሰው፤ ነገር ግን፡
- ተከራዩየተጠቀሰውን ያክል ገንዘብ የለበትምአከራዩእንዳለው፤ ወይም
- ኖቲስ ቱ ኩዊትማሳወቂያው አይገልፅምተከራዩስንት ብር እንዳለበት ወይም እንዳለባት ፤ ወይም
- ኖቲስ ቱ ኩዊት የሰጠውለተከራዩትንሽ ቀን ነበር የእሱ ወይም የእሷየሊዝስምምነት ወይም በህግ ከሚጠበቀው፡ ወይም
- አከራዩለተከራይበትክክል የኖቲስ ቱ ኩዊትግልባጩንአላቀረበም፡ ወይም
- ተከራዩሁሉንም የሚጠበቅበትን ገንዘቡን የከፈለውበኖቲስ ቱ ኩዊትማሳወቂያው ስር ነው፡፡
- ቅሬታ- አንድአከራይየቅሬታ መግለጫውን ግልባጭለተከራይበትክክል አላቀረበም፡፡
ምንድ ናቸው መከላከያዎቹ ለ"ኖቲስ ቱ ኩዊት" ጉዳይ የሊዝህግ ጥሰት(ኦች) ?
ተከራዩ ቤቱን እንዲለቅ የተከሰሰው ከቤት ኪራይ ክፍያ ጋር የተያያዘ ካልሆነ፤ "ኖቲስ ቱ ኩዊት" ፣ "ኖቲስ ቱ ኩዊት ኦር ቫኬት" የማግኘት መብት አለው፡፡ የሚከተሉት ተከራዩ ሊያነሳ የሚችላቸው ህጋዊ የሆኑ መከላከያዎች ናቸው፡
- ኖቲስ ቱ ኩዊትአልተሰጠም - ተከራዩአልደረሰውም የኖቲስ ቱ ኩዊትእሱን ወይም እሷንአከራዩለምን እንዲወጡእንደፈለገ የሚገልፅ ማሳወቂያ አልደረሳቸውም፡፡
- ኖቲስ ቱ ኩዊት - ተከራዩደርሷቸዋልየኖቲስ ቱ ኩዊትእሱን ወይም እሷን ለምንየቤት አከራዩተከራዩንtenantሊያስወጣ እንደፈለገ ነገር ግን፡
- የተጠቀሰው ምክንያት እውነት አይደለም፡ ወይም
- The ተከራዩችግሩን(ኦቹን) በማሳወቂያው ላይ ከተፃፈው የማስተካከያ ቀን ከማለቁ በፊት፤ ወይም
- አከራዩእያማረረያለበት ጉዳይየሊሱንህግ ወይም የመኖሪያ ቤት ህግን የጣሰ አይደለም፤ ወይም
- ምንም አይነት የተፃፈየሊስህግ የለም ወይም
- አከራዩለተከራዩበትክክል አልሰጠምማሳወቂያውን ፤ ወይም
- ማሳወቂያውተከራዩንእሱ ወይም እሷ ምን ስህተት እንደሰሩ እናአከራዩለምን ሊያስወጣቸው እንደፈለገለተከራዩአይገልፅም፤ ወይም
- ማሳወቂያውተከራዩችግሩን እንዴት መፍታት እንዳለበት አይገልፅም፤ ወይም
- ማሳወቂያው ለተከራዩችግሮቹን ለመፍታት ከ30 ቀናት በታች ነው የሰጠው፤ ወይም
- ማሳወቂያው በእንግሊዘኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋ አልተፃፈም፤ ወይም
- አከራዩክፍያውን የተቀበለውተከራዩማሳወቂያው ከደረሰው በኋላ ነው፡፡
- ቅሬታ-አከራዩለተከራይየቅሬታውንግልባጭ አላቀረበም፡፡
- በቀል-ትክክለኛ ምክንያትተከራይንለማስወጣት የፈለገበትምክንያት
- ተከራዪበመኖሪያ ቤቱ ላይ ቅሬታለአከራዩበማሰማቱ፤ ወይም
- ተከራዩበመኖሪያ ቤቱ ዙሪያ ቅሬታውን ለመንግስት ኤጀንሲ ወይም ለቤት ተቆጣጣሪ በመናገሩ፤ ወይም
- ተከራዩሌሎች ተከራዮችን የመኖሪያቸውን ወይም የህንፃውን አካባቢ ሁኔታ ለማስተካከል ስለረዳ ወይም ስላስተባበረ፡፡
- መድልዎ-አከራዩበኮሎምቢያ ዲስትሪክት እና/ወይም በፌደራል ህግ የተከለከለ መድሎ ውስጥ መግባት፡፡
- ትክክለኛውአከራዩተከራዩእንዲወጣየፈለገበት ምክንያትበተከራዩ:ዘር፣ ቀለም፣ ሀይማኖት፣ የትውልድ አገር፣ ፆታ፣ እድሜ፣ የጋቢቻ ሁኔታ፣ የሰውነት አቋም፣ ፆታዊ ግንዛቤ፣ ፆታዊ ማንነት ወይም አገላለፅ፣ የቤተሰብ ሁኔታ፣ የቤተሰብ ሀላፊነት፣ አካልጉዳት፣ የትምህርት ሁኔታ፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ የገቢ ምንጭ(በሴክሽን 8 የሀውሲንግ ቾይስ ቫውቸር ላይ የተመሰረተውንም ጨምሮ)፣ ወይም የመኖሪያ ወይም የንግድ ቦታ ወይም
- አከራዩበተለየ መልኩተከራዩንየሚያስተናግድበት ምክንያትተከራዩ፡ በተከራዩ፡ዘር፣ ቀለም፣ ሀይማኖት፣ የትውልድ አገር፣ ፆታ፣ እድሜ፣ የጋቢቻ ሁኔታ፣ የሰውነት አቋም፣ ፆታዊ ግንዛቤ፣ ፆታዊ ማንነት ወይም አገላለፅ፣ የቤተሰብ ሁኔታ፣ የቤተሰብ ሀላፊነት፣ አካልጉዳት፣ የትምህርት ሁኔታ፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ የገቢ ምንጭ(በሴክሽን 8 የሀውሲንግ ቾይስ ቫውቸር ላይ የተመሰረተውንም ጨምሮ)፣ ወይም የመኖሪያ ወይም የንግድ ቦታ፡፡
- ተከራዩአካል ጉዳተኛ ከሆነ እናአከራዩሊያስወጣው ከሞከረ ምንም እንኳተከራዩበራሱ ፍላጎት ምክንያታዊ ለሆነ ለውጥ(ወይም መኖሪያ ቦታ) በፖሊሲ፣ በአካሄድ፣በሊዙውል ወይም በህንፃው ምክንያትተከራዩየእሱን ወይም የእሷን መኖሪያ የመጠቀም እና የመደሰት እኩል እድል አለው፡፡ (ለምሳሌ በዚህ መከላከያ አንድ ሰው የሚያገለግል እንስሳ ለምሳሌ መስማት ለተሳነውተከራይየበር ደውል፣ የስልክ ጥሪ ወይም የጭስ ጠቋሚ መሳሪያ ድምፅ በመስማት የሚያስታውስ) በእንደዚህ አይነት ጉዳይ፤አከራይበ "የቤት እንስሳ-አይፈቀድም" በሚለው ህጉ ላይ በልዩ ሁኔታ ማየት መቻል አለበት እንዲሁምተከራዩውሻ ስላለው ከቤቱ ሊያስወጣው አይችልም፡፡)
- አከራዩሊያስወጣ ያሰበውተከራይ በቤቱ ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ብዛት ከሆነ፤ተከራዩቢያንስ አንድ ልጅ ከእሱ ወይም ከእሷ ጋር የሚኖር ከሆነ እና በቤቱ ውስጥ በአጠቃላይ የሚኖሩት ሰዎች ብዛት ከሚከተሉት ካልበለጠ (ሀ) በቂ በሆነ አፓርትመንት ውስጥ 2 ሰው ወይም (ለ) አንድ ወይም ሁለት መኝታ ባለው አፓርትመንት ውስጥ በመኝታ ቤቶቹ ብዛት ሁለት እጥፍ የሆኑ ሰዎች ከሆኑ፡፡
8. የጥበቃ ትዕዛዞች እና የፍርድ ቤት ክፍያዎች
"የጥበቃ ትእዛዝ" ማለት ምንድ ነው?
እርሶ ወይም ተከራይዎ(የተከራይዎ ጠበቃ) ተከራይ ሁሉንም የወደፊት ክፍያውን በፍርድ ቤቱ መዝገብ እንዲሰፍር "የጥበቃ ትእዛዝ" እንዲወጣ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፡፡
ተከራዩመክፈል የሚጠበቅበት ስንት ነው?
ጉዳዩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተከራዩ ሙሉውን የቤት ኪራይ በየ ወሩ እንዲከፍል ይጠበቅበታል፡፡ ወደ ጥበቃ ትእዛዙ የተገባው ወሩ ከተጀመረ በኋላ ከሆነ ዳኛው ተከራዩን ከወሩ የቀሩትን ቀናት ብቻ እንዲከፍል ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
ከበድ ያለ የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት በአፓርትመንቱ ውስጥ ከተፈፀመ፤ ተከራይ ዳኛውንአፓርትመንቱ ሙሉ ክፍያሊከፈልበት የሚገባ ስላልሆነ አነስ ባለ ዋጋ የጥበቃ ትእዛዝ እንዲገባ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ በፍርድ ሂደቱ ወቅት ተከራዩ ምን ያህል የቤት ኪራይ መክፈል እንዳለበት ለመወሰን ዳኛው የተለየ "ቤል" የመስማት ችሎት ሊቀጥሩ ይችላሉ የእርስዎ ጉዳይ ለቤል ችሎት ከተዘጋጀ፤ በአፓርታማ ውስጥ ችግር እንደሌለ፣ ዳኛው ለአፓርታማው ሁኔታ መናገር ወይም ምስሎችን ወይም ምስክሮችን ወደ ፍርድ ቤት በማቅረብ lዳኛው ለችሎቱ ለማሳየት መዘጋጀት ይኖርብዎታል፡፡ በአፓርትመንቱ ውስጥ ችግር ከነበረ እና ነገር ግን ተከራዩ ነግሮዎት የማያውቅ ከነበረ ወይም እርሶ በተገቢው ሰዓት ችግሩን ቀርፈው ከነበረ፤ ይህንኑ ለዳኛው ማስረዳት ይችላሉ፡፡
ተከራዩ ከሙሉ ክፍያው ዝቅ ያለ የክፍያ መጠን በወር እንዲከፍሉ ቢፈቀድለትም እንኳ፤ በጉዳዩ መጨረሻ ዳኛው ወይም ፍርደ ሸንጎው ተከራዩ ጉዳዩ እየታየ ባለበት ወቅት ምን ያህል መክፈል እንደነበረበት ይወስናሉ፡፡ ዳኛው ወይም ፍርደ ሸንጎው የጥበቃ ትእዛዙ በጣም ዝቅተኛ ነው ብለው ካመኑ ተከራዩ ከቤቱ ላለመውጣት ልዩነቱን መክፈል እንዳለበት ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ ዳኛው ወይም ፍርደ ሸንጎው የጥበቃ ትእዛዙ በጣም ከፍተኛ ነው ብለው ካመኑ ገንዘቡ በተከራዩ የቤት ኪራይ ሂሳብ ላይ እንዲደመር ወይም ለተከራዩ እንዲመለስ ሊደረግ ይችላል፡፡
ተከራዬየ "ጥበቃ ትእዛዙን" ባይከፍልስ?
ተከራዩ የጥበቃ ትእዛዝ ክፍያውን ካልፈፀመ ወይም በወቅቱ ካልከፈለ፤ ከተከራዩ በተቃራኒ በመቆም ለፍርድ ቤቱ የይዞታ ባለቤትነት መብት ውሳኔ እንዲሰጥዎ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ ፡፡
ነገር ግን በአብዛኛው፤ ተከራዩ አቤቱታዎን ከማስገባትዎ በፊት የጥበቃ ትእዛዙን ለመክፈል የተወሰነ ተጨማሪ ግዜ ከጠየቀ ወይም በአቤቱታዎ ችሎት ቀን ገንዘቡን ይሶ ከመጣ እና ለመክፈል ዝግጁ ከሆነ ዳኛው ዘግየት ብሎ እንዲከፍል ሊፈቅዱለት ይችላል፡፡
ስለ ጥበቃ ትእዛዝ የበለጠ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ጋር ይጫኑ፡፡
የፍርድ ቤት ክፍያዎችን መክፈል ባልችል ምን ይፈጠራል?
ከአከራይ ተከራይ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ያሉ ወጪዎችን ወይም ክፍያዎችን መክፈል ካልቻሉ "ካለ ቅድመ ወጪ፣ ክፍያ ወይም ጥበቃ የማመልከት ሂደቱን ማስቀጠል" በተለምዶ "IFP" ወይም "In Forma Pauperis" ማመልከት ይችላሉ፡፡ የፍርድ ቤቱን ቅፅ መሙላት እና ስለ ገንዘብ አቅሞ የተናገሩት በሙሉ እውነት ስለመሆኑ ቃለ መሀላ እንዲገቡ ይጠበቃል፡፡ ማመልከቻውን እና ምስክርነቱንአንድ ግዜ ከጨረሱ፤ ጥያቄዎን ሊፈቅድልዎ ወይም ሊከለክልዎ ከሚችል ዳኛ ፊት ይቀርባሉ፡፡
9. ስምምነቶች
ጉዳዬን ለመጨረስ ከተከራዬጋር ምን ማወቅ አለብኝ?
ተከራይዎን ለማስወጣት ክስ ከጀመሩ በኋላ ያሎት አንደኛው አማራጭ ከተከራይዎ እና ከጠበቃው ጋር ነገሩን ለመፍታት መሞከር ነው፡፡ ጉዳዩን መፍታት አይጠበቅቦትም እንዲሁም እንዲህ ለማድረግ መገፋፋት የለቦትም፡፡ ማድረግ በማይችሉት ነገር ላይም ለመስማማት አይፈልጉም ይሆን ይሆናል፡፡
ጉዳዩን ለመፍታት ተስማምቻለሁከተከራዬ ጋር፡፡ የስምነቱን ሁኔታ እንዴት በፅሁፍ ማስቀመጥ እችላለሁ?
በስምምነት ላይ የተመሰረተ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ Form 4A
አብዛኞቹ የቤት አከራዮች በ "ይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ" ስምምነት ወይም "Form 4A" ስምምነቱን የሚጨርስ ተከራይ ይወዳሉ፡፡ የቅፁን ግልባጭ እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህ ቅፅ አንድ ግዜ ከተፈረመበት እና በሁለቱም ወገን ይሁንታን ካገኘ በአፋጣኝ ወደ "ይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ" በመተላለፍ በ "ቃለመጠይቅ እና ውሳኔ ፀሀፊው" ያፀድቀዋል፡፡ አሁንም፤ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ ማለት እርሶ ተከራዩን የማስወጣት መብት አሎት ማለት ነው፤ ነገር ግን፤ ተከራዩ ህጉን አክብሮ እስከኖረ ድረስ ላለማስወጣት ከተስማሙ ውሳኔው ይዘዋወራል ወይም "በይደር" ይታለፋል፡፡
በአብዛኛው፤ እነኚህ ስምምነቶች ተከራይ ያለበትን ውዝፍ እዳ በተወሰነ ግዜ ልዩነት እንዲከፍል የክፍያ እቅድን ያወጣሉ፡፡ ነገር ግን፤ ተከራዩ በስምነቱ ላይ የተዘረዘረውን መጠን ሁሉንም በወቅቱ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ተከራዩ ሙሉ ክፍያውን ካልከፈለ ወይም ቢያንስ ለአንድ ቀን እንኳ ካዘገየ፤ ተከራዩን ማስወጣት ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ አከራዮች የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰቶችን በተወሰነ የግዜ ገደብ ውስጥ በማደስ ለማስተካከል ይስማማሉ፡፡ ከ Form 4A በተጨማሪ ተስማሚዎቹ አካላት የእድሳቱን ቀን የሚያወጡበት ቅፅ እዚህ ይገኛል፡፡ ነገር ግን፤ ይህንን የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት ለማስተካከል በተስማሙበት ወቅት ሳይችሉ ቢቀሩ ተከራዩ አሁንም ቢሆን ሙሉ ክፍያውን በስምምነቱ መሰረት መበሰዓቱ መክፈል ወይም ቤቱን መልቀቅ ይኖርበታል፡፡
በ Form 4A ላይ የተስማበትን እድሳት ባያደርጉ፤ ተከራዩ የ "ኖቲስ ቱ ሾው ኮዝ" ያስገባል እንዲሁም ዳኛውን እድሳቶን እንዲያጠናቅቁ ወይም እንዲያርሞ ወይም የወደፊቱን የቤት ኪራይ ዋጋ እንዲቀንስ እንዲያደርጉ እንዲያዝዎ ይጠይቃል፡፡
የስምምነት ውል/ Form 4B
እርሶ እና ተከራይዎ የ "ስምምነት ውል" ውስጥ መግባት ወይም የክፍያ እቅድ የሚያወጣውን "Form 4B" ይችላሉ፤ ነገር ግን በራሱ ወደ "የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ" አይገቡም፡፡ የForm 4B ግልባጭእዚህይገኛል፡፡ ተከራዩ ስምምነቱን መከተል ሳይችል ቢቀር፤ "የውሳኔ ይግባኝ" መጠየቅ እና የሆነውን ለማስራዳታ ሁለታችሁም ከዳኛ ፊት እንድትቀርቡ ይሆናል፡፡
እንደ Form 4B አካል የተወሰነ እርማት ለማድረግ እርሶ እና ተከራይዎ ልትስማሙ ትችላላችሁ፡፡ በተጨማሪም ለወደፊቱ በእቅድ ላይ የተመሰረተ እድሳት ለመዘርዘር እዚህ ቅፅ ይገኛል እዚህ፡፡
ሌሎች ስምምነቶች
እርሶ እና ተከራይዎ ወይ በራሳችሁ በመወያየት ወይም ደግሞ በፍርድ ቤቱ -በተቀጠረ አደራዳሪ አጋዥነት የሆነ አይነት ስምምነት ላይ ልትደርሱ ትችላላችሁ፡፡ ፍርድ ቤቱ "ፕሮሱህፔስ" የተባለ ማንኛውንም አይነት ሌላ ስምምነት ከተከራይ ጋር ለመፈፀም የሚፅፉበት ባዶ ቅፅ ያቀርባል፡፡ ማንኛውም አይነት ስምምነት ለፍርድ ቤቱ ማስገባቶን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ አንዳንድ አይነት ስምምነቶች ከዳኛ ፊት ቀርበው መፅደቅ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ፍርድ፣ ፅሁፍ እናየማስወጣትሂደት
የባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ አለኝ፡፡ ቤቱን ለቆ እስኪሄድተከራዬምን ያህል ግዜ ይኖረዋል?
የባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ ካገኙ በኋላ፤ ንብረትዎ እንዲመለስልዎ የመጠየቂያፅኁፍለማስገባት የግድ ሁለት ሙሉ የስራ ቀናትን መቆየት ይኖርቦታል፡፡ የንብረት ማስመለስ መጠየቂያ ማለት የሰነድ አይነት ሲሆን የዩ.ኤስ ማርሻልስ አገልግሎት ተከራይ የማስወጣት ስልጣን ነው፡፡
የንብረት ማስመለሽያ መጠየቂያፅሁፍከገባ በኋላ የፀሀፊው ቢሮ ለዩ.ኤስ ማርሻልስ አገልግሎት ይልካል፡፡ ለዩ.ኤስ ማርሻልስ አገልግሎት የስልጣኑን መግለጫ ሰነድ ግልባጭ ለተከራይ ይልካል፡፡ ለዩ.ኤስ ማርሻልስ አገልግሎት የማስወጫ ቀኑን ለመወሰን ይደውላሉ፡፡ በጣም የቅርብ የሚባለው የማስወጣት ሂደት ሰነዱ በገባ በ4ኛው የስራ ቀን ላይ ይሆናል፡፡ ይህ ሰነድ ህጋዊ የሚሆነው ለ75 ቀናት ብቻ ነው፡፡ ተከራዩ በ75ኛው ቀን መልቀቅ ካልቻለ፤ አዲስ ሰነድ ለማውጣት ፍርድቤቱን መጠየቅ ይኞርቦታል፡፡
ያስታውሱ፤ ተከራዩን በራስዎ ለማስወጣት መሞከር በዩ.ኤስ ማርሻልስ አገልግሎት በኩል ካልሆነ በስተቀር ህገወጥ ነው፡፡ በቤት መልቀቅ ሂደቱ ውስጥ ለዩ.ኤስ ማርሻልስ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
ውሳኔ ከተሰጠኝ በኋላተከራዬያለበትን እዳ በሙሉ ሊከፍለኝ ቢሞክርከመውጣቱ በፊትምን ይፈጠራል?
ተከራዩን ቤቱን እንዲለቅ የከሰሱት ክፍያ ካለመክፈሉ ጋር ተያይዞ ከሆነ፤ ተከራዩ ሃሳብ "የማስቀየር" መብት አለው ወይም ያለበትን እዳ በሙሉ አጠናቆ ክፍያውን በመፈፀም ክፍያ ከከፈለበት ቀን ጀምሮ በቤቱ ውስጥ የመቆየት መብቱን ያስከብራል፡፡ ዳኛው ተከራዩ ያለበትን የገንዘብ መጠን "ትራንሰ-ለክስ" እያሉ ሲጠሩ ሰምተው ይሆናል፤ ይህም ሂሳቡን እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ ተከራዩ ለእርሶ መክፈል ያለበት ክፍያ ማለት ነው፡፡
ተከራዩ ሂሳቡን የኪራይ ሂሳቡን እና የፍርድ ቤት ክፍያዎችን ጨመሮ ሙሉ በሙሉ አዲስ ካደረገ ከከፈለበት እለት አንስቶ እርሶ የቤቱ የማስወጣት መብት የሎትም፡፡ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ እና የንብረት ማስመለስፅሁፍስለሚኖር እንዲሁም መክፈያው ግዜ ስለደረሰ ተከራይዎን የቤት ኪራይ እንዲከፍል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ተከራዩ የእሱን ወይም የሷን ተከራይና አከራይ ውል የማደስመብት ይኖረዋልበጉዳዩ ላይ ክፍያ እንዲፈፀም ባይጠይቁም እንዲሁም ጉዳዩን የጀመሩት የ30-ቀን ማሳወቂያ በመስጠት ቢሆንም እንኳ ፤
ብቸኛ የሚያሳስበው ነገር የተከራዩ የመውጣት ምክንያት የቤት ኪራዩን መክፈል አለመቻሉ ነው፡፡
ተከራዩ ኪራዩን መክፈል ካቆመ፤ በሚቀጥለው ወር ላይ ቢሆንም እንኳ፤ የማስወጣት ሂደቱን መጀመር ይችላሉ፡፡ በሙሉ ጥሬ ገንዘብ ክፍያ፣ መኒ ኦርደር ወይም ሰርቲፋይድ ፈንድ የሚመጡ ክፍያዎችን ያለመቀበል መብት የሎትም፡፡ ከተከራዩ የተወሰነ ክፍያን ከተቀበሉ ተከራዩ ይህን በመክፈሉ ቤቱን ከመልቅ ሂደት ነፃ የሚያወጣው እንዳይመስለው ለተከራዩ መጠኑን የሚገልፅ ደረሰኝ መስጠትዎን እርግጠኛ መሆን ይኖርቦታል፡፡
የቤት ባለንብረትነት ውሳኔ ተወስኖልኛል፤ ነገር ግን ከዚህ ቀደምተከራዬያልከፈላቸውን ክፍያዎች ማግኘት እችላለሁ?
ዳኛውን "የገንዘብ ውሳኔ" ተከራዩ መክፈል ባለበት መጠን ላይ ተመስርቶ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የገንዘብ ውሳኔ ማለት ተከራዩ በህግ የሚጠበቅበትን ክፍያ ከነ ወለዱ እንዲከፍል የሚያስገድድ ትእዛዝ ነው፡፡ ተከራዩ የማይከፍል ከሆነ ከተከራይዎ ደሞዝ ወይም የባንክ ሂሳብ ከታገደ ገንዘብ ላይ እንዲከፈልዎ ይደረጋል፡፡ ይህም የተከራዩን ደሞዝ ወይም የባንክ ሂሳብ "ጋርኒሺንግ" ወይም ማስገደድ ይባላል፡፡
የገንዘብ ውሳኔ እንዲሰጥዎ ከፈለጉ፤ ቅሬታዎን ለፈፍርድ ቤቱ በሚያስገቡበት ወቅት አብረው መጠየቅ ይኖርቦታል፤ እንዲሁም ቅሬታውን ካስገቡበት ቀን ጀመር መከፈል አለበት ብለው የሚያስቡትን የገንዘብ መጠንም ጭምር አብረው ማካተት ይኖርቦታል፡፡ ዳኛው ይህንን የገንዘብ ውሳኔ ሊቀበሉ የሚችሉበት ብቸኛ ምክንያት ቅሬታ እና ትእዛዙ በቀጥታለተከራዩ ደርሶ ከነበረ ወይም ተከራዩ የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ፣ የማካካሻ ወይም መተኪያ እርሶ ላይ አንስቶ ከነበረ ነው፡፡
በአከራይ ተከራይ ፍርድ ቤት የገንዘብ ውሳኔ ካላገኙ ወይም ተከራዩ ሊከፍሎት የሚገባው ገንዘብ የአከራይ ተከራይ ፍርድ ቤቱ መሰብሰብ ከሚችለው በላይ ከሆነ በአብዛኛው የተለየ ጉዳይ በአነስተኛ ጉዳዮች ፍርድ ቤት(መጠኑ 10,000.00 $ እና ከዛ በታች ከሆነ) ወይም ከዛ በላይ ከሆነ ደግሞ በሲቪል አክሽን ብራንች መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ጉዳዩ ስለ ቤት ኪራይ ከሆነ፤ ጉዳዩ ላልተከፈለ ክፍያ የመጨረሻ ቀን በሆነው በሶስት (3) አመት ግዜ ውስጥ መጠየቅ አለበት፡፡
የገንዘብ ውሳኔን ተፈፃሚ የማደርገው እናተከራዬንእንዲከፍለኝ የማደርገው እንዴት ነው?
ተከላካዩተከራይዎ በፈቃደኝነት የማይከፍሎ ከሆነ፤ ከውሳኔው ወደ ማስገደድ ሂደት እና የተከራዩን ደሞዝ ወይም የባንክ ሂሳብ ለማሳገድ ቢያንስ አስር(10) ቀናትን መጠበቅ ይኖርቦታል፡፡ ክፍያው ከአስር ቀናት በኋላም ካልተፈፀመ የገንዘብ ውሳኔውን ቀጣይ ሂደት መከተል ይኞርቦታል፡፡ የተከራዩን ደሞዝ ማሳገድ ከፈለጉ "የውሳኔ አባሪ ፅሁፍ" ማስገባት ይኖርቦታል፡፡ የተከራዩን የባንክ ሂሳብ ማሳገድ ከፈለጉ፤ "አባሪ ፅሁፍ በደሞዝ፣ የቀን ገቢ እና ኮሚሽን" ላይ ጥያቄ ማስገባ ይኖርቦታል፡፡ የ10 ዶላር የማመልከቻ ክፍያ ይኖራል እንዲሁም የፍርድ ቤት ትእዛዙንበጉዳይ አስፈፃሚለተከራዩ ቀጣሪ ወይም ባንክ ማድረስ ይኖርቦታል፡፡
ተከራዬየት እንደሚሰራ አላውቅም ወይምተከራዬባንክ ሂሳቡ የት እንደሆነ አላውቅም፡፡ የተወሰነልኝን ገንዘብ እንዴት መሰብሰብ እችላለሁ?
መረጃ ከፀሀፊው በመጠየቅ እና 10 ዶላር በመክፈልየፍርድ እገዳየቃል ምርመራ ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ፡፡ በቃል ምርመራው ላይ፤ተከራይዎንበቃለ መሀላስር የት እንደሚሰራ እና የባንክ ሂሳቡ የት እንደሆነ እንዲሁም ስለሌሎች ስላሉት ንብረቶች ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ተከራዩ ገቢውን የት እንደሚያስቀምጥ የሚያሳይ መረጃ (የታክስ ሪተርን፣የክፍያ ስቴትመንቶች ወዘተ)፡፡ የፍርድ እገዳ ጥያቄ የማቅረብ ጥያቄዎን የሚያደርስ የሂደት አስፈፃሚ ሊኖሮት ይገባል፡፡ ይህ የእገዳ ጥያቄ ሰነድ ምን አይነት ሰነዶችን ተከራዩ ይዞ መምጣት እንዳለበት መግለፅ ይኖርበታል፡፡
ከመሰብሰብ የተጠበቁ የገቢ አይነቶች ይኖራሉ?
በአንዳንድ ጉዳዮች፤ የገንዘብ ውሳኔ በተከራዩ ላይ ቢኖሮትም እንኳ ከተወሰኑ ምንጮች የመጣ ከሆነ በህግ የተከራዩን ገንዘብ መውሰድ ሊከለከሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ የተጠበቁ የገቢ ምንጮች የሚከተሉት ናቸው፡
- የማህበራዊ ደህንነት
- ተጨማሪ የደህንነት ገቢ (SSI)
- የማህበራዊ ደህንነት የአካል ጉዳት ዋስትና (SSDI)
- የቀድሞ ወታደር ጥቅማ ጥቅም
- የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ የጡረታ ጥቅሞች
- የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ የአገልግሎት ክፍያ
- የአካል ጉዳት ጥቅማ ጥቅሞች
- የማህበራዊ ድጋፍ/ TANF ጥቅማ ጥቅሞች
- የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች
- በጡረታ እና በድጎማ ፕላኖች ውስጥ የሚደረጉ ክፍያዎች*
- አልሞኒ፣ ድጋፍ ወይም የተለየ እገዛ*
- የሰራተኞች የካሳ ክፍያ
- በሲቪል ወይም በወንጀለኛ ጉዳዮች ላይ በፍርድ ቤት የታዘዙ ክፍያዎች*
- ከባቡር መንገድ የተረፉ የጡረታ ጥቅማ ጥቅሞች
- የፌዴራል ዳኞች የካሳ ክፍያ
- የሎንግሾር እና ሀርበር ሰራተኞች የካሳ ጥቅማጥቅሞች
- የሲማንስ ወይም የማስተርስ ወይም የአሳ አጥማጆች ደመወዝ
- የብላክ ለንግ ጥቅማ ጥቅሞች
*ገደብ ተፈጻሚ ሊሆን ይችላል፡፡