Website Survey

በተከራዮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች

Authored By: DC Bar Pro Bono Center

Information

1. አጠቃላይ መረጃ ከቤት ስለ መውጣት

አከራዬበመጀመሪያ እኔን ወደ ፍርድ ቤት ሳይጠራኝሊያስወጣኝ ቢሞክር ህጋዊ ነው?

በዲ.ሲ፤አከራይዎወደ ፍርድ ቤት ሳይወስድዎ እና "የቤት ባለቤትነት መብት ውሳኔ" ሳያገኝ ከቤት ሊያስወጣዎ አይችልም፡፡ የቤትዎ አከራይ ያለ ቤት ባለቤትነት ውሳኔ እሱ/እሷ ከቤት ሊያስወጣዎ ቢሞክሩ ንብረትዎ ላይ ለሚደርስ ማንኛውም አይነት ጉዳት ከፋይ እና በተጨማሪም ህግ በመጣስ ጥፋት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

አከራይዎፍርድ ቤት ሳያቀርብዎ እንደሚያስወጣዎ ከዛተ እዚህ ጋር በመጫን አከራይዎንየማስወጣት ሀሳቡህገወጥ እንደሆነ የሚነግር ደብዳቤ በማውጣት ሊልኩለት ይችላሉ፡፡

ከነዚህ መካከል አንዱ ኤጀንሲ ጋር በመሄድ እና በማነጋገር ህገወጥ ለሆነውየማስወጣትሂደት እገዛ ማግኘት ይችላሉ፡

ቢሮየተከራይጠበቃ (Office of the Tenant Advocate)

2000 14th Street, NW
Suite 300N
Washington, DC 20009
(202) 719-6560

ደዲ.ሰሲ. የህግ ተማሪዎች በፍርድ ቤት (D.C. Law Students In Court)

4340 Connecticut Ave, N.W., Suite 100 
Washington, DC 20008 
Call for hours:(202) 638-4798

የከራይ ተከራይመረጃ ማእከል (Landlord Tenant Resource Center)

አከራይ ተከራይፍርድ ቤት ህንፃ (ህንፃ B)
510 4th Street, N.W., Room #208
9:15 AM - 12:00 ምሳ ሰዓት

 እባክዎ ልብ ይበሉ፤ ለአገልግሎቱ ከፍተኛ ፍላጎት ስላለ፤ የመረጃ ማእከሉ በያንዳንዱ ቀን የሚስተናገዱ ተጠቃሚዎችን ቁጥር ውስን ማድረግ አዲስ የሚመጡ ሰዎችን ከጥዋቱ 12 p.m በኋላ አይቀበልም፡፡ ምንም እንኳ በግዜ የሚዘጋ ቢሆንም ሁሉም በእለቱ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ያላቸው ወይም የጉዳያቸው አስቸኳይነት ከግምት ውስጥ ይገባል፤ (ለምሳሌ፤ የቀጥታየፍርድ ቤት እግድ፣ ከስራ መታገድ ወይም የቤት ውስጥ ሙቀት መቋረጥ) ከ12 ሰዓት በፊት ይታያሉ፡፡

ለዝርዝሩ ወደ "ህጋዊ ድጋፍ ጠይቅ" ከላይ ያለውን ትር ይመልከቱ፡፡

ዩኤስ ማርሻልስበምወጣበትወቅት መገኘት አለባቸው?

አዎ፡፡ ቤትበሚለቁበትወቅት የዩኤስ ማርሻሎች የግድ መገኘት አለባቸው፡፡ አለበለዚያ፤ ህገወጥ ይሆናል እንዲሁም አከራይዎ ለሚበላሽ ንብረትዎ ተጠያቂ እና ህግ ላለማክበር የገንዘብ ተቀጪ ይሆናል፡፡

የቤትአከራዬአይወደኝም፡፡ እኔን ለማስወጣት ህጋዊ ምክንያት ያስፈልገዋል?

አዎ፡፡ በዲ.ሲ. አከራይዎ ስላልፈለገ ወይም ስላልወደድዎት ብቻ ከቤት ሊያስወጣዎ አይችልም፡፡ በህጋዊ መንገድ ከቤቱ ለማስወጣት አከራይዎ ቢያንስ አንድ ህጋዊ ምክንያት ሊኖረው ይገባል፡፡ በጣም የተለመደው ህጋዊ ምክንያት የቤት ኪራይ አለመክፈል እና የሊዝ ህግ ጥሰት ማድረስ (ለምሳሌ፤ ሊሱ እያልፈቀደ ውሻ ቤት ውስጥ ማኖር)፡፡

የቤትአከራዬሊጠቀማቸው የሚችላቸው ህጋዊ የሆኑ ምክንያቶች ምንድናቸው?

ለአከራይዎ በህጋዊ መንገድ ለማስወጣት፤ እሱ ወይም እሷ ለፍርድ ቤቱ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መካከል ቢያንስ አንዱ(1) እውነት መሆን ይኖርበታል፡

 • የቤት ኪራዮን አልከፈሉም፤
 • እርሶ ወይም ሌላነዋሪህግ ጥሰው ከተገኙየሊሱን(ለምሳሌ፡ሊሱእየከለከለ ውሻ ቤት ውስጥ ማስቀመጥ ወይም በቤቱ ውስጥ ያልተፈቀድላቸው ሰዎች መኖር) ወይም የመኖሪያ ቤት ህግ (ለምሳሌ፤ የቤቱን ንብረት በማጥፋት ወይም ፅዳቱን ባለመጠበቅ)፤
 • እርሶ ወይም ሌላተከራይበንብረቶች ላይ ህግ ጥሰት፤
 • እርሶ ወይም ሌላተከራይአደገኛ እፅ በቤቶ ውስጥ ከተጠቀሙ፤
 • አከራዩ ቤቱን ለአስቸኳለይ እና ለግሉ ጉዳይ ሊጠቀመው ከፈለገ፤
 • አከራዩ ቤቱን ማሳደስ ከፈለገ እና እርሶ እያሉ ያንን ማድረግ የማይቻል አይነት ከሆ፤
 • አከራይዎ ቤቱን ሊያፈርሰው ከፈለገ፤
 • ቤቱ በአግባቡ መታደስ ወይም መስተካከል ካለበት፤ ወይም
 • ቤቱ ከዚህ በኋላ ለኪራይ አገልግሎት የማይውል ከሆነ፡፡

የቤትአከራዬየሊዝስምምነታችን ሲያበቃ ከቤቱ ሊያስወጣኝ ይችላል?

በዲ.ሲ በጭራሽ፤ አንድ ግዜየሊዙወቅት ካበቃ፤ ሊዙ በራሱ በየወሩ መታደስ ይጀምራል፡፡ ሁሉም የሊሱ ቀሪ አካላት እንደነበሩ ይቀጥላሉ(የቤት ኪራይ ዋጋውን ጨምሮ የፅሁፍ ማሳወቂያ እስካልደረስዎት ድረስ)፡፡

ለምሳሌ ለአንድ(1) አመት የሚቆይየሊዝ ስምምነትከጃንዋሪ 1 2016 ጀምሮ ከተፈራረሙ እና የሊዙ ግዜ በ ዲሴንምበር 30 2016 ከተጠናቀቀ፤ የቤቱ አከራይ እንዲታደስ ባይስማማ እንኳ - የሊሱ ውል ከጃኑዋሪ 1 2017 ጀምሮ ከወር ወር እየታደሰ ይሄዳል፡፡ በሌላ ቋንቋ፤ የቤቶ አከራይ የሊዝ ስምምነቶ ቢያበቃም እንኳ ሌላ ምክንያት ከሌለው በስተቀር ከቤቱ ሊያስወጣዎ አይችልም፡፡

የቤትአከራዬዋጋ መጨመር ይችላል?

በአብዛኛው በፅሁፍ ሊዝ ላይ በተወሰነ መጠን ለመጨመር ከተስማማችሁት በቀር የቤት አከራይዎ ዋጋ መጨመር አይችልም፡፡ በአብዛኛው እርሶ እና አከራይዎ በተወሰነ መጠን ለተወሰነ ግዜ ዋጋ ለመጨመር ትስማማላችሁ፡፡ አንድ ግዜ ያ ግዜ ካለቀ አከራይዎ የሰላሳ (30) ቀን የፅሁፍ ማሳወቂያ በመስጠት የቤት ኪራይ ዋጋን ለመጨመር ይችላል፡፡ እርሶ እና አከራይዎ በተወሰነ የግዜ ገደብ ላይ ስምምነት ከሌላችሁ፤ አከራይዎ በማንኛውም ሰዓት የሰላሳ (30) ቀን የፅሁፍ ማሳወቂያ በመስጠት ዋጋ መጨመር ይችላል፡፡

አከራይዎ ዋጋ መጨመር ከተፈቀደለት፤ ምን ያህል እና በምን ያህል ግዜ መጨመር እንዳለበት የሚወስነው የቤቱ በኪራይ ቁጥጥር ስር መሆን አና አለመሆን ላይ ተመስርቶ ነው፡፡ ቤቱ ከኪራይ ቁጥጥር ነፃ ከሆነ፤ አከራዩ በየትኛውም የዋጋ መጠን እና በየትኛውም ግዜ ዋጋ መጨመር ይችላል፤ አከራዩ ዋጋ የሚጨምረው ህገወጥ ለሆነ ምክንያት እስካሆነ ድረስ፤ ለምሳሌ፤ ተከራዩ ለወሰደው እንዳንድ ህጋዊ እርምጃ እንደ በቀል እርምጃ አስቦ ዋጋ መጨመር፣ አከራዩ ለወሰደው ህጋዊ እርምጃ እንደ መኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት ማመልከት ወይም እድሳት መጠየቅ ላሉ፡፡ አከራዩ ለተከራዩ አዲሱን የዋጋ ጭማሬ ተግባራዊ ከማድረጉ በፊት ቢያንስ የ30 ቀን የፅሁፍ ማሳወቂያ ሊሰጥ ይገባል፡፡

ቤቱ በቤቶች ቁጥጥር ስር ያለ ከሆነ አከራዩ የቤቱን ዋጋ የሚጨምረው በሚከተሉት መስፈርቶች ላይ ተመስርቶ ነው፡

 • ለመጨረሻ ግዜ ዋጋ የተጨመረው ቢያንስ ከ12 ወራት በፊት መሆን ይኖርበታል(ቤቱ ባዶ ካልሆነ በቀር)
 • ቤቱ በአግባቡ በሬንታል አኮሞዴሽን ዲቪዥን ራድ የተመዘገበ ከሆነ
 • የሚከራየው ቤት እና ሀውሲንግ አኮሞዴሽን የተለመደ መለያቸው የመኖሪያ ቤቶች ህግን ያከብራሉ፡፡
 • የቤትአከራዩዋጋ ለመጨመር አከራዩ የ30-ቀን የጽሁፍ ማሳወቂያ ሰጥቶ ከሆነ

በአጠቃላይ አንድ አከራይ በኪራይ ቁጥጥር ስር ያለ ቤት ካለው ኪራዩን መጨመር የሚችለው በየአመቱ በተወሰነ መጠን ብቻ ነው፡፡ ይህም መጠን ከ10 በመቶ መብለጥ የለበትም እንዲሁም ትክክለኛው በየአመቱ መጨመር የሚችለው መጠን የሚሰላው በሬንታል ሀውሲንግ ኮሚሽን እና በተጠቃሚ ዋጋ መረጃ ጠቋሚ ላይ ተመስርቶ ነው፡፡ የሬንታል ሀውሲንግ ኮሚሽንን በ(202) 442-8949 በመደወል አከራዩ ምን ያህል መጨመር እንዳለበት ማወቅ ይችላሉ፡፡

ሬንታል ፕሮፐርቲ ቢያንስ 12% ተመላሽ የማይመለስ ከሆነ ባለንብረቱ የቤት ኪራይ ባለሥልጣን ብዙውን ጊዜ ከሚፈቅደው ከፍ ያለ የኪራይ ጭማሪ እንዲከፍል መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህንን ለማድረግ አከራዩ "የሀርድሺፕ ፔቲሽን" ማመልከቻ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ የቤቶ አከራይ የሀርሺፕ ፔቲሽን ካስገባ፤ ማመልከቻው ትክክለኛ መሆኑን ለማየት ጠበቃ ማናገር ሊኖርቦት ይችላል፡፡

በመጨረሻም ባለቤቱ በህንፃው ላይ የተወሰነ ማሻሻያ ካደረገ በኋላ አከራዩ ያወጣውን ወጪ ለመመለስ የቤት ኪራይ ዋጋ ለመጨመር ፈቃድ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ አከራዩ ከኪራይ አስተረዳደር ወይም ሬንት አድሚኒስትሬተር ላቀረበው ምክንያት ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ የቤት አከራይዎ በህንፃው ላይ ባደረገው ማሻሻል የተነሳ የቤት ኪራይ ዋጋ ለመጨመር ማሰቡን የሚገልፅ ማሳወቂያ ካደረስዎ የነገሩን ትክክለኛነት ለማወቅ ጠበቃ ማነጋገር ሊኖርቦ ይችላል፡፡

ወደ ላይ ተመለስ

2. የፍርድ ቤት ውሳኔዎች ማስታወቂያ

በሕጉ ለውጦች ምክንያት ይህ ክፍል እየተሻሻለ ነው.

 የቤቴአከራዬ እኔን ከማስወጣቱ በፊት ማሳወቂያ ማግኘት ይኖርብኛል?

አዎ፡፡ አከረይዎ ከቤት ሳያስወጣዎ በፊት ቢያንስ ሁለት በአመዛኙ 4 ማሳወቂያ ሊደርሶት ይገባል፡፡

1. ኖቲስ ቱ ኩዊት

የመጀመሪያው ማሳወቂያ ወይ "ኖቲስ ቱ ኩዊት፣" "ኖቲስ ቱ ኩዊት ኦር ቫኬት"፡፡ የቤት ኪራይ ክፍያ ባለመክፈልዎ ወይም አደገኛ እፅ ቤቶ ውስጥ በመጠቀም ካልሆነ በቀር አከራይዎ በሌላ ምክንያት በህጋዊ መንገድ እርሶን ከማስወጣቱ በፊት የግድ ይህንን ማሳወቂያ ሊሰጥዎ ይገባል፡፡

ከቤቱ የሚያስወጣዎ ምክንያት አደገኛ እፅ ቤት ውስጥ በማስቀመጥዎ ከሆነ አከራይዎ ይህንን ማሳወቂያ መላክ አይጠበቅበትም፡፡

ከቤቱ የሚያስወጣዎ ምክንያት የቤት ኪራይ ክፍያ ባለመክፈልዎ ከሆነም አከራይዎ ይህንን ማሳወቂያ መላክ አይጠበቅበትም፡፡ ቤቱን እንዲለቁ ከመከሰስዎ በፊት ይህ የማሳወቂያ ደብዳቤ እንዲደርሶ ወይም እንዲቀር ምን እንደተስማሙ የሊዝ ስምምነትዎን ይመልከቱ፡፡ ሊዙ የተወሰነ ቋንቋ ሊኖረው ይችላል እንደ "ይህ ሊዝ ማቋረጥ እንደ ተከራይመቋረጥ ማሳወቂያ ይተዳደራል ወይም መውጣት እንዳለበት ተከራይ ማሳሰቢያ ሲሆን ይህም ቤቱን ከመልቀቁ በፊት ለተከራዮች ተጨማሪ ማሳሰቢያ እንዲሰጥ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስፈርት ያስወግዳል"

ሊዙ ይህ ቋንቋ ካለበት አከራይዎየኖቲስ ቱ ኩዊትማሳወቂያ መላክ አይጠበቅበትም፡፡

ይህ ሊዝ ተመሳሳይ ትርጓሜ ከሌለው፤ ማሳወቂያ የማግኘት መብቶን አልተውም ማለት ነው፤ ስለዚህ አከራይዎ ማሳወቂያውን የግድ ሊልክልዎ ይገባል፡፡ ይህንን ማሳወቂያ የማግኘት መብቱን ለመተው ሊስማሙ የሚችሉት ክፍያ መክፈል ሳይችሉ ለሚቀሩበት ሁኔታ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ለሆኑ የማስወጣት ምክንያቶች አከራይዎ የግድ ማሳወቂያ ሊልክሎ ይገባል፡፡

*አስታውሱ፤ ምንም እንኳ ይህ ማሳወቂያ ቤቱን እንዲለቁ ቢገልፅም፤ ከፍርድ ቤት የቤት ባለመብትነት ውሳኔ አግኝቶ በቤቱ ማዘዝ እስኪችል አከራይዎ ልቀቁ በሎ ማስገደድ አይችልም፤

2. ቅሬታ

ሁለተኛው ማሳወቂያ ቅሬታ ይባላል፡፡ አከራይዎ ህጋዊውን የፍርድ ቤት ጉዳይ ለምን እንደተከሰሱ እና የመጀመሪያውን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ቀን እና ሰዓት የሚገልፅ የቅሬታ ማሳወቂያ የግድ ሊልክሎት ይገባል፡፡

3. ማሳወቂያለተከራይ ለማስቀረትቤት መልቀቅን ክፍያ አስፈላጊ እንደሆነ የሚገልፅ

ቤቱን የሚለቁት የቤቱን ኪራይ ባለመክፈልዎ ከሆነ እና በእርሶ ተቃራኒ የሆነ ውሳኔ ሲወሰን በፍርድ ቤ ካልተገኙ፤ አከራይዎ ምን ያህል ክፍያ እናሌሎች ወጪዎች እንዳለብዎ ለፍርድ ቤቱ በፅሁፍ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ የዚህን ቅፅ ግልባጭ ለእርሶ መላክ ይኖርበታል፡፡

4. የፍርድ ቤትማዘዣ

የመጨረሻው ማሳወቂያ"የፍርድ ቤትማዘዣ" ይባላል፡፡ ይሄ አከራይዎ በፍርድ ቤት የተሰጠውን የቤት ባለቤትነት መብት ውሳኔውን ካገኘ እና በቤቱ ማዘዝ ከጀመረ በኋላ ሊደርሶ የሚገባ ህጋዊ የሆነ የልቀቅ ማሳወቂያ ነው፤ ይሄ ማሳወቂያ ሲደርሶት ለመጀመሪያ ግዜ ከሆነ፤ ከጠበቃ ጋር በአፋጣኝ መነጋገር ይኖርቦታል፡፡

የኔአከራይየግድ"ኖቲስ ቱ ኩዊት፣" "ኖቲስ ቱ ኩዊትወይም ቫኬት" "ኖቲስ ቶ ኪዩር ኦር ቫኬት"በሆነ መንገድ ሊሰጠኝ ይገባል?

አዎ፡፡ አከራይዎ ማሳወቂያውን ራሱ ወይም ራሷ መጥተው ሊሰጡዎ ይችላሉ፡፡ ወይም ደግሞ ከሚከተሉት በአንዱ ሊደርሶ ይችላል፡

 • የግል አገልግሎት- የማሳወቂያ ወረቀቶችን በቀጥታ ለእርሶ ይሰጣሉ፤
 • ተቀያሪ አገልግሎት- በቤትዎ ውስጥ የሚኖር እድሜው ከ16 ዓመት በላይ የሆነ ግለሰብ ግልባጩን ይቀበላል፤ ወይም
 • የተመዘገበ ፖስታ- ለደብዳቤዎቹ እርሶ በግሎ እስከፈረሙ ድረስ ግልባጩን በተመዘገበ ፖስታ በኩል ለእርሶ መላክ፡፡
 • መለጠፍ እና መላክ - እርሶን በአካል አጊኝቶ ለመስጠት ሁለት(2) ግዜ ከሙከሩ በኋላአከራዩየማሳወቂያውን ግልባጭ በቤትዎ በር ላይ ማያያዝ ማጣበቅ ወይም መለጠፍ ይችላሉ፡፡ የማሳወቂያው ሌላ ግልባጭ በአንደኛ ደረጃ ፖስታ በሩ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉ በሶስት (3)ቀናት ውስጥ ለእርሶ የግድ ሊላክሎት ይገባል፡፡

የማሳወቂያው ሌላ ግልባጭ በአንደኛ ደረጃ ፖስታ በሮ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉ በሶስት (3)ቀናት ውስጥ ለእርሶ የግድ ሊላክሎት ይገባል፡፡

የህግ ጥሰት ማሳወቂያዎች "ኖቲስ ቱ ኩዊት፣" "ኖቲስ ቱ ኩዊትወይም ቫኬት፣"ለሊዝወይም "ኖቲስ ቶ ኪዩር ኦር ቫኬት" የሆነ አይነት ቅድመ ሁኔታ ይኖር ይሆን?

አዎ፡፡ የእነዚህ ማሳወቂያዎች ቅድመ ሁኔታዎች በጣም ጥብቅ ናቸው፡፡ ወደ ማስለቀቅ ለማለፍ እና ሂደቱን ለማስቀጠል አከራይዎ ተገቢ የሆነ ቅድመ ማሳወቂያ ሊሰጥዎ ይገባል፡፡ አለበለዚያ፤ ክሱ በፍርድቤት ውድቅ ይሆናል፡፡ ቅድመ ሁኔታዎቹም፡

 • እንዴት የመኖሪያ ቤቱን ወይምየሊዙንህግ እንደጣሱ በጣም ግልፅ የሆነ መረጃ መስጠት፤
 • የህግ ጥሰቱን እንዴት ማስተካከል እንደሚችል ግልፅ የሆነ መረጃ መስጠት፤
 • ለእርሶ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ቢያንስ የ30 ቀን ግዜ መስጠት፤ እና
 • ማስታወቂያው በእንግሊዘኛ እና በስፓኒሽኛ መፃፍ ይኖርበታል፡፡

ለ "ቅሬታው" የተወሰነ አይነት ቅድመ ሁኔታ አለ?

አዎ፡፡ አከራዮች ጉዳይዩ ወደ ቀጣዩ ሂደት እንዲያልፍ በአግባቡ የተሞላ የፍርድ ቤቱን መደበኛ ቅፅ መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡ አከራዩ ማድረግ ያለበት፡

 • ስምዎን እና አድራሻዎን በትክክል ይዘርዝሩ (የአፓርትመንት ወይም ካለው የክፍል ቁጥርን ጨምሮ)፡
 • በዝርዝር(ወይም ማሳወቂያውን ያያይዙ)እንዲወጡየተከሰሱበት ምክንያቱን(ኦቹን) እና
 • ለገንዘብ ብቻ ሳይሆን ለባለቤትነት ሊከስዎ ይችላል፡፡

የግድአከራዬ በሆነ መንገድ "ቅሬታውን" ሊሰጠኝ ይገባል?

አዎ፡፡ አከራይዎ የቅሬታውን ግልባጭ በራሱ ሊሰጥዎም ሆነ ሊልክሎ አይችልም፡፡ ሌላ ግለሰብ (የ"ሂደት አገልግሎት") ቢያንስ እድሜው 18 ዓመት የሆነ ግለሰብ "ሊሰጥዎ" ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ ከሚከተሉት በአንዱ ሊደርሶ ይችላል፡

 • የግል አገልግሎት- የቅሬታውን ግልባጭ በቀጥታ እንዲረከቡ ያደርጋል፡፡
 • ተቀያሪ አገልግሎት- በቤትዎ ውስጥ የሚኖር እድሜው ከ16 ዓመት በላይ የሆነ ግለሰብ ግልባጩን ይቀበልሎታል፤ ወይም
 • መለጠፍ እና መላክ - እርሶን በአካል አጊኝቶ ለመስጠት ሁለት(2) ግዜ ከሙከሩ በኋላአከራዩየቅሬታውን ግልባጭ በቤትዎ በር ላይ ማያያዝ ማጣበቅ ወይም መለጠፍ ይችላሉ፡፡ የማሳወቂያው ሌላ ግልባጭ በአንደኛ ደረጃ ፖስታ በሩ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉ በሶስት (3)ቀናት ውስጥ ለእርሶ የግድ ሊላክሎት ይገባል፡፡

ወደ ላይ ተመለስ

3. ወደ ፍርድቤት መሄድ

በሕጉ ለውጦች ምክንያት ይህ ክፍል እየተሻሻለ ነው.

በቀጠሮዬ ቀን ፍርድ ቤት መቅረብ ባልችል ምን ይፈጠራል?

 • በአፋጣኝ ለፍርድ ቤቱ ፀሀፊ በ(202) 879-4879 ላይ መደወል እና ለምን መገኘት እንዳልቻሉ ማብራራት ይኖርቦታል፡፡ ፀሀፊውን ስሙን ወይም ስሟን በመጠየቅ ይፃፉ፡፡
 • በአፋጣኝ ለቤት አከራዮወይምለቤት አከራይዎጠበቃም በመደወል በቀኑ መገኘት እንደማይችሉ ይንገሯቸው፡፡
 • ከፍርዱ ቀን በፊት ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ግዜ ካገኙ በእለቱ በፍርድ ቤት መገኘት የማይችሉበትን ምክንያት ጠቅሰው ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ፀሀፊው ተለዋጭ ቀን መስጠት ካልቻለ ወደ ፍርድ ቤቱ በተቻለ ፍጥነት በመሄድ ምን እንደተፈጠረ ያጣሩ፡፡
 • ለፍርድቤቱ በስልክ ያሳወቁ ቢሆንም እንኳ ዳኛውለአከራዮየባለቤትነት መብት ውሳኔውን ሰጥቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄም "ነባሪ ውሳኔ" ተብሎ ይጠራል፡፡

በፍርድ ቤት የመጀመሪያ ቀኔ ምን ይፈጠራል?

 •  በጥዋት 9፡00 AM በፍርድቤቱ ክፍል ደርሰው እየጠበቁ መሆኖን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ዳኛው ሂደቱ ምን እንደሚመስል እና ምን አይነት እገዛ እንደሚኖር ያስረዳሉ፡፡ እንግሊዘኛ የማይናገሩ ከሆነ ወይም መስማት የማይችሉ ወይም የመስማት ችግር ያለብዎ ከሆነ የፍርድ ቤቱ ክፍል ፀሀፊን ማስተዋወቅ ከመጀመሩ በፊት መንገሮን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡
 • በመቀጠል፤ ፀሀፊው የሁሉንም በቀጠሮው ቀን እንዲቀርቡ የተጠየኩ አካላትን ወይም ሰዎችን ዝርዝር ያነባል፡፡ ስምዎ ሲጠራ "እዚህ ነኝ" ወይም "ተገኝቻለሁ" በማለት እና ስሞትን በመጥራት መመለስ ይጠበቅቦታል፡፡ ፀሀፊውን በደንብ እንደሚሰሙ ያረጋግጡ፡፡ የማይሰማዎ ከሆነ እጅዎን በማውጣት ለፀሀፊው ያሳውቁ፡፡ ስምዎ ሲጠራ ካለፍዎ "ነባሪ ውሳኔ" እና ሳይመልሱ ከቀሩ በእርሶ ላይ ሊወሰን ይችላል፡፡
 • የሁሉም ሰው ስም በሚጠራበት ወቅት ስምዎ ካልተሰማዎ ወይም ፍርድ ቤት አርፍደው ከደረሱ እና ስምዎ መጠራቱን እርግጠኛ ካልሆኑ የስም መጥራ ሂደቱ እንዳለቀ በፀሀፊው ቢሮ(ክፍል110) ወደ መስኮት 4 በመሄድ ፀሀፊው መኖርዎን እንዳወቀ ያረጋግጡ፡፡
 • አንድ ግዜ ፀሀፊው ሁሉንም ጠርቶ ከጨረሰ በኋላ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ወይም ከዛ በላይ የሆኑትን ነገሮች ለማድረግ መወሰን ይችላሉ፡
  • ጉዳዩንከአከራይዎወይምከአከራይጠበቃ ጋር ይጨርሱ፡
  • ያሉትን አማራጭ የመከላከያ መንገዶች ተመልክቶ ለሁለት (2) ሳምንት ግዜ ሂደቱን ለማስቀጠል ጠበቃ ለማናገር እና "ምላሽ" ለመስጠት ይጠይቁ፡፡ ክሱን ለማስቀጠል በሚጠይቁበት ወቅት "ሁሉንም አይነት መብቶች ማስጠበቅ" በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ "ሁሉንም መብቶችዎን ካላስጠበቁ" አንዳነድ መብቶችን ሊያጡ ይችላሉ ለምሳሌ በፍርደ ሸንጎ የመታየት መብት፡፡
  • ከዳኛ ፊት በመቅረብ "የዳኛ ችሎት" መከላከያዎን ለማቅረብ ይጠይቁ፡፡ የሚያዘው ቀነ ቀጠሮም ከተጠየቀበት ቀን አንስቶ ከ2 (ሁለት) ሳምንት እስከ 2 (ሁለት) ወር ድረስ ሊፈጅ ይችላል፡፡
  • ምንም እንኳ በአብዛኛውበአከራይ ተከራይፍርድ ቤት ውስጥ "ምላሽ" መስጠት ባይጠበቅቦትም ግን ምላሽ ይስጡ፡፡ ምላሹ በፍርድ ቀነ ቀጠሮው እንደ መከላከያ የሚያቀርቡትን ሀሳብ በፅሁፍ ያስቀምጣል፡፡
  • ጉዳዮን ፍርድ ቤቱ በመደበው አደራዳሪ በኩል "ይደራደሩ"፡፡ አደራዳሪው በሁለቱም ወገኖች በኩል ያለውን ሀሳብ ሰምቶ ጉዳዩን እልባት እንዲያገኝ ይረዳል፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን ለመፍታት አይገደዱምእንዲሁም ከመደራደሪያ ነጥቦቹ ያልተረዱት ክፍል ካለ ወይምበአደራዳሪው የሚነገርዎ ነገር ካልገባዎ ከጠበቃ ጋር መነጋገር ይኖርቦታል፡፡
  • እርሶ ወይምአከራይዎ (ወይም የአከራይዎ ጠበቃ) ሁሉንም የወደፊት ክፍያውን በፍርድ ቤቱ መዝገብ እንዲሰፍር "የጥበቃ ትእዛዝ" እንዲወጣ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፡፡ ለበለጠ መረጃ"የጥበቃ ትእዛዝ"የሚለውን ክፍል ይመልከቱ፡፡

በፍርድ ቤት ስለሚኖርዎ የመጀመሪያ ቀን ቆይታ የበለጠ ለማወቅ እዚህ ጋይጫኑ፡፡

ወደ ላይ ተመለስ

4. መልሶች እና ሌሎች ምላሾች

"ምላሽ" ምንድ ነው?

ምላሹ በፍርድ ቀነ ቀጠሮው እንደ መከላከያ የሚያቀርቡትን ሀሳብ በፅሁፍ ያስቀምጣል፡፡ አከራይዎን ሊከሱ ከፈለጉ የሚሰጡት ምላሽ "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ""ማካካሻ"፣ እና/ወይም "መተኪያ"ን ሊያካትት ይችላል፡፡ ፍርደ ሸንጎን ከፈለገ (ከ "ፍርደ ዳኛ" ከዳኛ ፊት ከመቆም)፤ ምላሹ "የሸንጎ ጥያቄ" ንም ሊያካትት ይችላል፡፡

ተከራዩ ምለሹን በፅሁፍ ማስገባት ይጠበቅበታል?

 "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ" ፣ "ማካካሻ"፣ እና/ወይም "መተኪያ"፤ ወይም ፍርደ ሸንጎን (ከ "ፍርደ ዳኛ" ከዳኛ ፊት ከመቆም) እስካልጠየቁ ድረስ የጽሁፍ ምላሽ በአከራይ ተከራይ ፍርድቤት ውስጥ አይጠበቅም፡፡

"የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ" ምንድ ነው?

የቤት ኪራይ ሂሳብዎን ባለመክፈልዎ ቤቱን እንዲለቁ ተከሰው ከሆነ "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ" ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የሁለት አይነት የመልሶ ይገባኛል ጥያቄዎች አሉ፡፡

 1.  በመኖሪያ ቤት ሀግ ጥሰት ምክንያትለአከራይዎበቤት ኪራይ ከሚገባዎ በላይ ከከፈሉ እና ተመላሽ እንዲሆንልዎ ከፈለጉ "የገንዘብ መልሶ ይገባኛል ጥያቄ" ሊያስገቡ ይችላሉ፡፡ በቤቱ መኖር ከጀመሩበት ግዜ አንስቶ ያለውን ግዜ ወይም 3 (ሶስት) አመታት ከሁለቱ አነስተኛ የሆነውን ያክል ግዜ ተመላሽ እንዲደርግልዎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ በአብዛኛው ተከራዮች የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ የሚያቀርቡት የተከራዩት ቤት ሁኔታ በጣም የከፋ ሆኖ ለረዥም ግዜ የቆየ ከነበረ ብቻ ነው፡፡
 2. የአፓርትመንቶ ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ህግን የጣሰ በመሆኑ፣ ስለሁኔታውአከራይዎየሚያውቅ መሆኑ እና ችግሩን ለመቅረፍ በቂ ግዜ ቢኖረውምአከራይዎlባለማድረጉ የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ ሊያስገቡ ይችላሉ፡፡ አከራይዎእደሳዎችን እንዲያደርግ እንዲታዘዝ እየጠየቁ ነው፡፡

ማንኛውም አይነት የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ ለማቅረብ ፍርድ ቤቱ 10$ ክፍያ ይጠይቆታል፡፡

አስፈላጊ: የቅሬታ ማሳወቂያው በእጅዎ ካልተሰጥዎት የገንዘብ መልሶ ይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ ለእርሶ ትክክለኛ ውሳኔ ላይሆን ይችላል፡፡ ከተሸነፉ፤ አከራይዎ ከእርሶ በተቃራኒ የገንዘብ ውሳኔ (በተጨማሪም የቤት ባለቤትነት ውሳኔም ጭምር)ሊያገኝ ይችላል፡፡ የመልሶ ይገባናል ጥያቄ ከማቅረብዎ በፊት ከጠበቃ ጋር መማከር ይኖርቦታል፡፡ ለእድሳት የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ ማስገባት አከራይዎ የሚያገኘውን ነገር ሊቀይ አይችል ይሆናል፡፡

"ማካካሻ" ምንድ ነው?

ክፍያውን ባለመክፈሎ የተነሳ አከራይዎ ከቤቱ እንዲወጡ ከሶት ከነበረ፤ እርሶ የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት በመኖሩ የተነሳ በጣም ከፍተኛ የሆነ ወጪ በሌላ ቤት ኪራይ ሲያወጡ እንደነበር በመግለፅ "ማካካሻ" መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ማካካሻም የዚህ "ከፍተኛ ክፍያ" መጠን እርሶ መክፈል ካለቦት መጠን ላይ እንዲቀነስ ይጠይቃል፡፡ እስከዛሬ ድረስ በኪራይ ቤቱ ውስጥ የኖሩበትን ግዜ ታስቦ ከሁሉም ላይ እንዲቀነስ በቤቱ ውስጥ የኖሩት ከ 3 (ሶስት) በላይ ቢሆንም እንኳ ገንዘቡ ተቀናሽ እንዲሆንሎት ሊጠይቁ ይችላሉ፡ በአብዛኛው ተከራዮች የማካካሻ ጥያቄ የሚያቀርቡት የተከራዩት ቤት ሁኔታ በጣም የከፋ ሆኖ ለረዥም ግዜ የቆየ ከነበረ ብቻ ነው፡፡ ለማካካሻ ጥያቄ ክፍያ የለውም፡፡

"መተኪያ" ምንድ ነው?

ክፍያውን ባለመክፈሎ የተነሳ አከራይዎ ከቤቱ እንዲወጡ ከሶት ከነበረ፤ ቤቱን በሚጠበቅበት ደረጃ ለማቆየት የመኖሪያ ቤቱ ላይ እድሳት በማድረግ ወይም እቃ ለመግዛትዎ "መተኪያ" ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ይህም በተደጋጋሚ እድሳት እንዲደረግ ቢጠየቁም ባለማድረግዎ የተነሳ በራስዎ አዲስ ስቶቭ መግዛትን ወይም የመፀዳጃ ቤት እቃ መቀየርን ያካትታል፡፡ መተኪያ ለእድሳት እና ለግዢ በአጠቃላይ ያወጡትን ወጪ ለአከራይዎ መክፈል ከሚገባዎ ገንዘብ ላይ ተቀንሶ እንዲከፈልዎ ይጠይቃል፡፡ እነዚህን ወጪዎች ወይ በኪራይ ቤቱ ውስጥ ከኖሩበት ግዜ ላይ እየተቀነሰ ወይም በ 3 (ሶስት) ተከፋፍሎ እንዲከፈለው አጭር የሆነውን ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ መተኪያን ለመጠየቅ ምንም አይነት ክፍያ የለውም፡፡

ስለ ምላሾቹ "የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ"፣ "ማካካሻ"፣ ወይም "መተኪያ"ን የበለጠ ለመረዳት እዚህ ይጫኑ፡፡

ወደ ላይ ተመለስ

5. የጥበቃ ትዕዛዞች እና የፍርድ ቤት ክፍያዎች

"የጥበቃ ትእዛዝ" ማለት ምንድ ነው?

እርሶ ወይም አከራይዎ(የአከራይዎ ጠበቃ) ሁሉንም የወደፊት ክፍያውን በፍርድ ቤቱ መዝገብ እንዲሰፍር "የጥበቃ ትእዛዝ" እንዲወጣ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ ቀደም ያልከፈሉትን የኪራይ ዋጋ (ወይም አከራይዎ አልከፈሉም ብሎ የጠየቀውን መጠን) በፍርድ ቤቱ መዝገብ በጥበቃ ትእዛዝ ስር ማስቀመጥ አይጠበቅቦትም፡፡ የጥበቃ ትእዛዞች በጥሬ ገንዘብ ወይም በመኒ ኦርደር መከፈል ይችላሉ፡፡ ቤቱን የመልቀቅ አደጋ በራሶ ላይ ላለማምጣት የጥበቃ ትእዛዞን በወቅቱ መክፈል ይጠበቅቦታል፡፡

መክፈል የሚጠበቅብኝ ምን ያህል ነው?

በአብዛኛው ሙሉ የቤት ኪራዩን ዋጋ በየወሩ ጉዳዩ እልባት እስከሚያገኝ ድረስ እንዲከፍሉ ይጠበቅቦታል፡፡ የጥበቃ ትእዛዙ ወሩ ከተጀመረ በኋላ ከሆነ የተገባው፤ ዳኛው ለቀሪው የወሩ ቀናት ብቻ እንዲከፍሉ ሊያደርጎ ይችላል፡፡

 በአፓርትመንቶ ውስጥ የጎላ የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት ተፈጥሮ ከነበረ እና ሙሉ የቤቱን ክፍያ ማግኘት የማይገባው አይኘት ቤት ከሆነ የጥበቃ ትእዛዙን ዝቅ ባለ ዋጋ ላይ እንዲመሰረት ዳኛውን መጠየቅ ይችላሉ፡፡ በፍርድ ሂደቱ ወቅት ምን ያህል የቤት ኪራይ መክፈል እንዳለቦት ለመወሰን ዳኛው የተለየ "ቤል" የመስማት ችሎት ሊቀጥሩ ይችላሉ፡፡ የእርስዎ ጉዳይ ለቤል ችሎት ከተዘጋጀ፤ በአፓርታማ ውስጥ ችግር እንዳለ፣ ስለአፓርታማው ሁኔታ ለዳኛው መናገር ወይም ምስሎችን ወይም ምስክሮችን ወደ ፍርድ ቤት በማቅረብ ለዳኛው እና ለችሎቱ ለማሳየት መዘጋጀት ይኖርብዎታል፡፡ አከራዮ በቤት ውስጥ ስላሉ ችግሮች ቢያውቅም ሊያስተካክል እንዳልሞከረ ዳኛውን ሊያሳምኑ ይገባል፡፡

ሁሉንም ወይም የተወሰነውን ክፍያ የሚሸፍን ቫውቸር ካሎት እና ምን ያህል መከፈል እንዳበት ስምምነት ላይ ካልደረሳችሁ ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ አከራይዎ ለጥበቃ ትእዛዙ የእርሶ ድርሻ ከሆነው የኪራይ ዋጋ በላይ እየጠየቀ ከሆነ ለዳኛው መናገር ይችላሉ፡፡

ዳኛው ከመደበኛው የኪራይ ዋጋ ያነሰ እንዲከፍሉ ካዘዙ፤ ቀሪውን ገንዘብ ማስቀመጥ ጥሩ ሃሳብ ሊሆን ይችላል፡፡ ክሱ በሚጠናቀቅበት ወቅት፤ ጉዳዩ እየታየ በነበረበት ወቅት ምን ያህል መክፈል እንደነበረብዎ ዳኛው ወይም ፍርደ ሸንጎው የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡ ዳኛው ወይም ፍርደ ሸንጎው የጥበቃ ትእዛዙ በጣም ዝቅተኛ ነው ብለው ካመኑ ከቤቱ ላለመውጣት ልዩነቱን መክፈል እንዳለቦት ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ ዳኛው ወይም ፍርደ ሸንጎው የጥበቃ ትእዛዙ በጣም ከፍተኛ ነው ብለው ካመኑ ገንዘቡ እርሶ የቤት ኪራይ ሂሳብ ላይ እንዲደመር ወይም እንዲመለስልዎ ሊደረግ ይችላል፡፡

ሙሉውን ክፍያ ለጥበቃ ትእዛዙ ከፍለው የነበረ ከሆነ እና ቤቱ የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት ደርሶበት ከነበረ ጉዳዩ በሚጠናቀቅበት ወቅት የተወሰነውን ገንዘብ ተመላሽ ሆኖ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ዳኛው ቤቱ ከደረሰበት የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት አንፃር የጥበቃ ትእዛዙ ከፍተኛ ነበር ብሎ ካመነ፤ ተጨማሪ የከፈሉት ገንዘብ ወደ እርሶ የቤት ኪራይ ሂሳብ ይመለሳል ወይም ለእርሶ እንዲመለስ ይደረጋል፡፡

የ "ጥበቃ ትእዛዙን" መክፈል ባልችልስ?

እንደ ሁኔታው ይወሰናል፡፡ "የጥበቃ ትእዛዙ"ን ከቀነ ገደቡ በኋላ ለመክፈል የሚሆን ገንዘብ በአጭሩ ይኖረኛል ብለው ካመኑ ክፍያውን ለመፈፀም ጥቂት ግዜ እንዲሰጥዎ ወይም ሁሉንም ገንዘብ በሚኖርዎ ሰዓት አጠቃለው ለማምጣት እንደሚችሉ ፍርድ ቤቱን ለማሳወቅ "የጥበቃ ትእዛዝ መክፈያ ግዜ ማራዘሚያ አቤቱታ" ማስገባት ይችላሉ፡፡

 መቼም ቢሆን ይህንን የጥበቃ ትእዛዝ መክፈል እንደማይችሉ ካወቁ ምንም ከማለት ቢቆጠቡ እና ፍርድ ቤቱንም ሆነ የቤት አከራይዎን እንዲያውቁ ባያደርጉ ለእርሶ የተሸለ አማራጭ ነው፡፡ እርሶን ከቤትዎ ሊያስወጣ በሚችል ሁኔታ የቤት አከራይዎ "የክርክርአቤቱታ" ማቅረቡ የማይቀር ነው፡፡

የጥበቃ ገንዘቡን በተሰጠው ቀነ ገደብ መክፈል የማይችሉ መሆኑን ካሰቡ በአፋጣኝ ከጠበቃ ጋር መነጋገር ይኖርቦታል፡፡ .

ስለ ጥበቃ ትእዛዝ ለበለጠ መረጃ እዚህ ይጫኑ፡፡

የፍርድ ቤት ክፍያዎችን መክፈል ባልችል ምን ይፈጠራል?

አብዛኛው በአከራይ ተከራይ ፍርድ ቤት የሚያደርጉት ነገር ምንም ሊያስወጣዎ አይገባም፡፡ ለምሳሌ፤ ምላሽ ለመስጠት፣ ስምምነት ላይ ለመድረስ ወይም በጉዳዩ ላይ ለመደራደር፣ ወይም"ፍርደ ዳኛ" ከዳኛ ፊት ለመቆም ምንም አይኘት ክፍያ የለውም፡፡ ነገር ግን፤ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ክፍያ ወይም ዋጋ ሊኖራቸው እንደሚችል ማሰብ ያስፈልጋል፤ ለምሳሌ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ እና ፍርደ ሸንጎ መጠየቅ፤

ከአከራይ ተከራይ ጉዳዮ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ክፍያዎችን መክፈል ካልቻሉ "ካለ ቅድመ ወጪ፣ ክፍያ ወይም ጥበቃ የማመልከት ሂደቱን ማስቀጠል" በተለምዶ "IFP" "In Forma Pauperis."ወይም ማመልከት ይችላሉ፡፡ የፍርድ ቤቱን ቅፅ መሙላት እና ስለ ገንዘብ አቅሞ የተናገሩት በሙሉ እውነት ስለመሆኑ"ቃለ መሀላ"እንዲገቡ ይጠበቃል፡፡ ማመልከቻውን እና ምስክርነቱንአንድ ግዜ ከጨረሱ፤ ጥያቄዎን ሊፈቅድልዎ ወይም ሊከለክልዎ ከሚችል ዳኛ ፊት ይቀርባሉ፡፡ 

ወደ ላይ ተመለስ

6. ስምምነቶች

ጉዳዬን ለመጨረስ ከአከራዬጋር ምን ማወቅ አለብኝ?

ቤቱን እንዲለቁ ክስ ከተመሰረተብዎ በኋላ ያሎት አንደኛው አማራጭ ከአከራይዎ እና ከጠበቃው ጋር ነገሩን ለመፍታት መሞከር ነው፡ ጉዳዩን መፍታት አይጠበቅቦትም እንዲሁም እንዲህ ለማድረግ መገፋፋት የለቦትም፡፡ ማድረግ በማይችሉት ነገር ላይም ለመስማማት አይፈልጉም ይሆን ይሆናል፡፡

በስምምነት ላይ የተመሰረተ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ Form 4A

አብዛኞቹ የቤት አከራዮች በ "ይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ" ስምምነት ወይም "Form 4A" ስምምነቱን የሚጨርስ ተከራይ ይወዳሉ፡፡ ይህ ቅፅ አንድ ግዜ ከተፈረመበት እና በእርሶ በኩል ይሁንታን ካገኘ በአፋጣኝ ወደ "ይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ" በመተላለፍ በ"ቃለመጠይቅ እና ውሳኔ ፀሀፊው" ያፀድቀዋል፡፡ አሁንም፤ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ ማለት አከራይዎ እርሶን የማስወጣት መብት አለው ማለት ነው፤ ነገር ግን፤ እርሶ ህጉን አክብረው እስከኖሩ ድረስ ላለማስወጣት ከተስማሙ ውሳኔው ይዘዋወራል ወይም "በይደር" ይታለፋል፡፡ ይጫኑ እዚህ አትመው ከሞሉ በኋላ ፍርድ ቤት ለሚያስገቡት ለForm 4A ፡፡

በአብዛኛው፤ እነኚህ ስምምነቶች ያለቦትን ውዝፍ እዳ በተወሰነ ግዜ ልዩነት እንዲከፍሉ የክፍያ እቅድን ያወጣሉ፡፡ ነገር ግን፤ እርሶ በስምነቱ ላይ የተዘረዘረውን መጠን ሁሉንም በወቅቱ መክፈል ይኖርቦታል፡፡ ሙሉ ክፍያውን ካልከፈሉ ወይም ቢያንስ ለአንድ ቀን እንኳ ካዘገዩ፤ አከራይዎ ሊያስወጣዎት ይችላል፡፡ አንዳንዴ አከራዮች የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰቶችን በተወሰነ የግዜ ገደብ ውስጥ በማደስ ለማስተካከል ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን፤ ይህንን የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት ለማስተካከል በተስማሙበት ወቅት ሳይችሉ ቢቀሩ እርሶ አሁንም ቢሆን ሙሉ ክፍያውን በስምምነቱ መሰረት በሰዓቱ መክፈል ወይም ቤቱን መልቀቅ ይኖርቦታል፡፡

ይጫኑ እዚህ ለመፈረም ከተስማሙ እና አትመው፣ ሞልተው ፍርድ ቤት ከ Form 4A ጋር አብረው ሊያስገቡ የሚችሉትን ቅፅ ያገኛሉ፡፡ ይህንን ቅፅ በመጠቀም አከራይዎ እደሳ ሊያደርግባቸው የሚገቡትን ነገሮች መዘርዘር ይችላሉ፡፡

የስምምነት ውል/ Form 4B

እርሶ እና አከራይዎ የ "ስምምነት ውል" ውስጥ መግባት ወይም የክፍያ እቅድ የሚያወጣውን "Form 4B" መጠቀም ይችላሉ፤ ነገር ግን በራሱ ወደ "የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ውሳኔ" አይገቡም፡፡ ይህን ስምምነት መከተል ሳይችሉ ቢቀሩ፤ "የውሳኔ ይግባኝ" መጠየቅ እና የሆነውን ለማስራዳታ ሁለታችሁም ከዳኛ ፊት እንድትቀርቡ ይሆናል፡፡

ይጫኑ እዚህ ለForm 4B አትመው፣ ከሞሉ በኋላ፣ ፍርድ ቤት ለማያስገቡት፡፡ ይጫኑ እዚህ ይህንን ቅፅ ለመጠቀም እና አከራይዎ እደሳ ሊያደርግባቸው የሚገቡትን ነገሮች ለመዘርዘር፡፡

ሌሎች ስምምነቶች

እርሶ እና አከራይዎ ወይ በራሳችሁ በመወያየት ወይም ደግሞ በፍርድ ቤቱ -በተቀጠረ አደራዳሪ አጋዥነት የሆነ አይነት ስምምነት ላይ ልትደርሱ ትችላላችሁ፡፡ ፍርድ ቤቱ "ፕሮሱህፔስ" የተባለ ማንኛውንም አይነት ሌላ ስምምነት ከአከራይዎ ጋር ለመፈፀም የሚፅፉበት ባዶ ቅፅ ያቀርባል፡፡ ማንኛውም አይነት ስምምነት ለፍርድ ቤቱ ማስገባቶን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ አንዳንድ አይነት ስምምነቶች ከዳኛ ፊት ቀርበው መፅደቅ ይኖርባቸዋል፡፡

For more information about settling your case, click ጉዳዮን ከስምምነት ላይ ስለማድረስ ለበለጠ መረጃ፤ ይጫኑ እዚህ፡፡

ወደ ላይ ተመለስ

7. መከላከያዎች

ለቤት ኪራይ አመክፈል ጉዳይ መከላከያዎቹ ምንድ ናቸው?

አንዳንድ ግዜ ተከራዮች ስራ በመልቀቃቸው የተነሳ ወይም በህመም ምክንያት ያልታሰበ የህክምና ክፍያ መክፈል ኖሮባቸው የቤት ኪራይ መክፈል ያቅታቸዋል፡፡ እርሶ ለቤት ኪራይ መክፈል የሚችለት ገንዘብ የሌሎት የመሆንዎ እውነታ እንደ ህጋዊ መከለላከያ ነጥብ ሊሆንልዎ አይችልም፡፡

ነገር ግን፤ ክፍያውን ያልከፈሉበት ዋነኛ ምክንያት ባይሆንም እንኳ እርሶ ቤቱን ከመልቀቅ የሚያድኖት ህጋዊ የሆኑ መከላከያዎችን ማቅረብ ይችላሉ፤ የሚያቀርቡት የመከላከያ ነጥብ ከሌሎት ከእርሶ በተቃራኒ የባለቤትነት መብት ውሳኔ ሊወሰንቦ ይችላል፡፡

የተወሰኑት ህጋዊ መከላከያዎች የሚከተሉት ናቸው፡

 • የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት - ክፍያውን ያልከፈልኩበት ወቅትአከራዬየሚያውቀው ወይም እያወቀ ነገር ግን ማስተካከል ያልቻላቸው እንዲሁም በእኔ ወይም በቤተሰቦቼ ወይም በእንግዶቼ ምክንያት ያልተፈጠሩ ወይም ከባድ ችግሮችን ከሙቀቱ ጋር፣ ከሙቅ ውሀ ጋር፣ የወጥ ቤት እቃዎች፣ የመታጠቢያ ቤት ቁሳቁሶች፣ ፍሰቶች፣ ነፍሳት እና ፣ ወለሎች ግድግዳዎች እና የመሳሰሉት ጋር የተያያዙ ከባድ የሆኑ ችግሮች በተከራየሁበት ቤት ውስጥ ነበር፤፡፡
 • ልክ ያልሆነ መጠን - እኔ የሚባለውን ያክል ገንዘብ የለብኝምአከራዩያለውን ያክል ምክንያቱምአከራዩእየከሰሰኝ ያለው ከዚህ ቀደም ከፍዬ ስለነበረውም ጭምር ነው፡፡
 • ህገ ወጥ የክፍያ ደረጃ- እኔ የሚባለውን ያክል ገንዘብ የለብኝምአከራዬየሚለውን ያህል ምክንያቱምአከራዬእያስከፈለኝ ያለው ህገወጥ በሆነ የክፍያ መጠን ነው፡፡
 • "ኖቲስ ቱ ኩዊት" ወይም "ኖቲስ ቱ ኪዩር ኦር ቫኬት"
  • እንዲደርሰኝ ያለኝን መብት አልተውኩምኖቲስ ቱ ኩዊትን እንዲሁምኖቲስ ቱ ኩዊትለማስወጣት ከመሞከርዎበፊት እናበአቤቱታ ከመቅረቤ በፊት አልተሰጠኝም. ወይም
  • ማሳወቂያ ደርሶኛልየኖቲስ ቱ ኩዊትከመከሰሴ በፊት ከቤቴለማስወጣትእና የቅሬታ ማሳወቂያ ሳይደርሰኝ በፊት፤ ነገር ግን ማሳወቂያው ችግር ያለበት ነበር፡፡
   • ገንዘብ እኔ የለብኝምአከራዬየሚለውን ያክል፤ ወይም
   • ኖቲስ ቱ ኩዊትምን ያህል ገንዘብ መክፈል እንዳለብኝ አይገልፅም፤ ወይም
   • ኖቲስ ቱ ኩዊትአነስተኛ ቀን ነው የሰጠኝሊዙወይም ህጉ ከሚፈቅደው አንጻር ፤ ወይም
   • my አከራዬግልባጭ በትክክል አላደረሱልኝምየኖቲስ ቱ ኩዊት፤ ወይም
   • ሁሉንም የሚጠበቅብኝን ገንዘብ ከፍያለውበኖቲስ ቱ ኩዊቱየተጠየቀውን፡፡
 • ቅሬታ - የኔአከራይየቅሬታ ማሳወቂያውን ግልባጭ በትክክል አላደረሱልኝም፤ ወይም

ለ"ኖቲስ ቱ ኩዊት" ጉዳይ ለ ለሊዝህግ ጥሰት መከላከያዎቹ ምንድ ናቸው?

ከሚኖሩበት እንዲወጡ የተከሰሱት ክፍያ ካለመክፈል ጋር ተያይዞ ከነበረ ኖቲስ ቱ ኩዊት ወይም ኖቲስ ቱ ኮሬክት ኦር ቫኬት እንዲደርሶ መብት አሎት፡፡ የሚያቀርቡት የመከላከያ ነጥብ ከሌሎት ከእርሶ በተቃራኒ የባለቤትነት መብት ውሳኔ ሊወሰንቦ ይችላል፡፡

የሚከተሉት የተወሰኑ ሊያነሷቸው የሚችሏቸው ህጋዊ መከላከያዎች ናቸው

 • አልደረሰኝምኖቲስ ቱ ኩዊትየሚገልፅ የቤቴአከራይለምን ከቤቱ ሊያስወጣኝ እንደፈለገ ፡፡
 • ደርሶኛልኖቲስ ቱ ኩዊትለምን የቤቴአከራዬከቤቱ ሊያስወጣኝ እንደፈለገ የሚገልፅ፤ ነገር ግን፡
  • የተጠቀሰው ምክንያት እውነት አይደለም፡ ወይም
  • ችግሩን ፈትቼዋለው በማሳወቂያው ላይ ከተፃፈው የማስተካከያ ቀን ከማለቁ በፊት፤ ወይም
  • አከራዩእያማረረ ያለበት ጉዳይየሊሱንህግ ወይም የመኖሪያ ቤት ህግን የጣሰ አይደለም፤ ወይም
  • ምንም አይነት የተፃፈየሊስህግ የለኝም፤ ወይም
  • አከራዬበትክክል አልሰጠኝም ማሳወቂያውን ፤ ወይም
  • ማሳወቂያው ምን ስህተት እንደሰራሁ እናአከራዬለምን ሊያስወጣኝ እንደፈለገ አይገልፅም፤ ወይም
  • ማሳወቂያው ችግሩን(ኦቹን) እንዴት መፍታት እንዳለብኝ አይገልፅም፤ ወይም
  • ማሳወቂያው ችግሮቹን ለመፍታት ከ30 ቀናት በታች ነው የሰጠኝ፤ ወይም
  • ማሳወቂያው በእንግሊዘኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋ አልተፃፈም፤ ወይም
  • አከራዬክፍያውን የተቀበለው እኔ ማሳወቂያው ከደረሰኝ በኋላ ነው፡፡
 • ቅሬታ - የኔአከራይየቅሬታ ማሳወቂያውን ግልባጭ በትክክል አላደረሱልኝም፤ ወይም
 • በቀል-ትክክለኛ ምክንያትአከራዬከቤት ሊያስወጣኝ የፈለገበት ምክንያት
  • በመኖሪያ ቤቱ ላይ ቅሬታለአከራዬበማሰማቴ፤ ወይም፡
  • በመኖሪያ ቤቴ ዙሪያ ቅሬታዬን ለመንግስት ኤጀንሲ ወይም ለቤት ተቆጣጣሪ በመናገሬ፤ ወይም
  • ሌሎች ተከራዮችን የመኖሪያቸውን ወይም የህንፃውን አካባቢ ሁኔታ ለማስተካከል ስለረዳሁ ወይም ስላስተባበርኩ፡፡
 • መድልዎ-የአከራዬበኮሎምቢያ ዲስትሪክት እና/ወይም በፌደራል ህግ የተከለከለ መድሎ ውስጥ መግባት፡፡
  • ትክክለኛውአከራዬእንድወጣ የፈለገበት ምክንያት በ (እርሶ ላይ ተፈፃሚ የሖኑትን ብቻ ዘርዝር) ዘር፣ ቀለም፣ ሀይማኖት፣ የትውልድ አገር፣ ፆታ፣ እድሜ፣ የጋቢቻ ሁኔታ፣ የሰውነት አቋም፣ ፆታዊ ግንዛቤ፣ ፆታዊ ማንነት ወይም አገላለፅ፣ የቤተሰብ ሁኔታ፣ የቤተሰብ ሀላፊነት፣ አካልጉዳት፣ የትምህርት ሁኔታ፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ የገቢ ምንጭ(በሴክሽን 8 የሀውሲንግ ቾይስ ቫውቸር ላይ የተመሰረተውንም ጨምሮ)፣ ወይም የመኖሪያ ወይም የንግድ ቦታ ወይም
  • አከራዬከሌሎቹ ተከራዮች በተለየ መልኩ እኔን የሚያይበት ምክንያት፡ በእኔ ዘር፣ ቀለም፣ ሀይማኖት፣ የትውልድ አገር፣ ፆታ፣ እድሜ፣ የጋቢቻ ሁኔታ፣ የሰውነት አቋም፣ ፆታዊ ግንዛቤ፣ ፆታዊ ማንነት ወይም አገላለፅ፣ የቤተሰብ ሁኔታ፣ የቤተሰብ ሀላፊነት፣ አካልጉዳት፣ የትምህርት ሁኔታ፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ የገቢ ምንጭ (በሴክሽን 8 የሀውሲንግ ቾይስ ቫውቸር ላይ የተመሰረተውንም ጨምሮ)፣ ወይም የመኖሪያ ወይም የንግድ ቦታ፡፡
  • እኔ አካል ጉዳተኛ ከሆንኩ እናአከራዬሊያስወጣኝ ከሞከረ ምንም እንኳ በራሴ ፍላጎት ምክንያታዊ ለሆነ ለውጥ(ወይም መኖሪያ ቦታ) በፖሊሲ፣ በአካሄድ፣በሊዙውል ወይም በህንፃው ምክንያት እኔም መኖሪያውን የመጠቀም እና የመደሰት እኩል እድል አለኝ፡፡ (ለምሳሌ በዚህ መከላከያ አንድ ሰው የሚያገለግል እንስሳ ለምሳሌ መስማት ለተሳነውተከራይየበር ደውል፣ የስልክ ጥሪ ወይም የጭስ ጠቋሚ መሳሪያ ድምፅ በመስማት የሚያስታውስ) በእንደዚህ አይነት ጉዳይ፤አከራይበሚለው ህጉ ላይ በልዩ ሁኔታ ማየት መቻል አለበት እንዲሁምተከራዩበ "የቤት እንስሳ-አይፈቀድም" ውሻ ስላለው ከቤቱ ሊያስወጣው አይችልም፡፡)
  • አከራዬሊያስወጣ ያሰበው በቤቴ ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ብዛት የተነሳ ነው፤ ቢያንስ አንድ ልጅ ከእኔ ጋር የሚኖር ከሆነ እና በቤቱ ውስጥ በአጠቃላይ የሚኖሩት ሰዎች ብዛት ከሚከተሉት ካልበለጠ (ሀ) በቂ በሆነ አፓርትመንት ውስጥ 2 ሰው ወይም (ለ) አንድ ወይም ሁለት መኝታ ባለው አፓርትመንት ውስጥ በመኝታ ቤቶቹ ብዛት ሁለት እጥፍ የሆኑ ሰዎች ከሆንን፡፡

ወደ ላይ ተመለስ

8.የፍርድ ቀን

እዚህ ይጫኑ፡፡

ወደ ላይ ተመለስ

9. ፍርድ፣ ፅሁፍ እናየማስወጣትሂደት

ስለጉዳዬ ማሳወቂያ አልደረሰኝም እና አሁን ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ምን ማድረግ እችላለሁ?

የአከራይ ተከራይ ፍርድ ቤት ፀሀፊ ጋር በ(202) 879-4879 ላይ ከ8:30 AM እስከ 5:00 PM ባለው ግዜ ውስጥ በመደወል በአሁኑ ሰዓት ቤት ከሚለቁ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መሆን አለመሆንዎን ያጣሩ፡፡ በዝርዝሩ ውስጥ ሆኑም አልሆኑም፤ በአፋጣኝ ወደ አከራይ ተከራይ ፍርድቤት በመሄድ የማስወጣት ሂደቱን ለማስቆም ማመልከቻ ያስገቡ፡፡

ውሳኔው በኔ ላይ ከሆነ የተወሰነው ከቤት ለመውጣት ምን ያህል ግዜ ይኖረኛል?

አንድ ግዜ የቤት ባለመብትነት ውሳኔው ከእርሶ በተቃራኒው ከተወሰነ፤ እርሶን ከማስወጣቱ በፊት አከራይዎ "የንብረት ማስመለስመጠየቂያ" ያስፈልገዋል፡፡ የባለቤትነት ማረጋገጫውን ለማጠናቀቅ አከራይዎ የግድ ሁለት ሙሉ የስራ ቀናትን መቆየት ይኖርበታል፡፡ መጤቂያው ስራ የሚጀምረው ከተጠየቀ በኋላ ካሉ 3 የስራ ቀናት በኋላ ይሆናል፡፡ ይህ ሰነድ ህጋዊ የሚሆነው ለ75 ቀናት ብቻ ነው፤ ስለዚህ በማንኛውም ሰዓት ቤቱን ሊለቁ እንደሚችሉ መዘጋጀት አለብዎት፡፡

ቤትበሚለቁ ሰዎችዝርዝር ውስጥ እንደሆንኩ በምን ማወቅ እችላለሁ?

በህጋዊ መንገድ ቤቱን ከመልቀቅዎ በፊት፤ አከራይዎ የቅሬታ ማሳወቂያ ሊያደርስልዎ እና "የንብረት ባለመብትነት ውሳኔ" ማምጣት ይኖርበታል፡፡ አንድ ግዜ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ፤ አከራይዎ "የንብረት ማስመለስ መጠየቂያ" ማለት የዩ.ኤስ ማርሻልስ አገልግሎት ተከራይ የማስወጣት ስልጣኑን አውጥቶ ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡ አንድ ግዜ መጠየቂያው ከደረስዎ፤ የአከራይ ተከራይ ፍርድ ቤት ፀሀፊ ጋር በ (202) 879-4879 ላይ ከ8:30 AM እስከ 5:00 PM ባለው ግዜ ውስጥ በመደወል በአሁኑ ሰዓት ቤት በነገው ለት በሚወጣው የሚለቁ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መሆን አለመሆንዎን ያጣሩ፡፡

 ከቤትመውጣቴንአንድ ግዜመጠየቂያውከደረስኝ በኋላ ለማስቀረት ማድረግ የምችለው ነገር ይኖራል?

እንደ ሁኔታው ይወሰናል፡፡ ቤቱን እንዲለቁ የከሰሱት ክፍያ ካለመክፈሎ ጋር ተያይዞ ከሆነ፤ እናም በስምነት ወቅት ይህን መብቶን አሳልፈው ያልሰጡ ከሆነ፤ ማስወጣቱን የማስቆም መብት አሎት ወይም ያለበቦትን እዳ በሙሉ አጠናቆ ክፍያውን በመፈፀም ክፍያ ከከፈለበት ቀን ጀምሮ በቤቱ ውስጥ የመቆየት መብቱን ማስከበር ይችላሉ፡፡ ይህም ሁሉንም የቤት ኪራይ ዋጋ እና የፍርድ ቤት ክፍያዎችንም ይጨምራል፡፡ ይህንን የሚያክል ገንዘብ በጥሬ ወይም በመኒ ኦርደር መክፈል ይችላሉ፡፡ "በሙሉ ተከፍሏል" የሚል ደረሰኝ ከ "$0 Balance" ጋር ማግኘቶን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ እና ለዳኛው ደረሰኙን በማሳየትጉዳይዎበሙሉ በከፈለ ስር እንዲመደብ ማድረግ ይመከራል፡፡

የተከሰሱት በሌላ አይነት ህግ ጥሰት ከሆነ(ለምሳሌ፤ ሊዙ እያልፈቀደ ውሻ በማኖር) ወይም በሆነ ሌላ ምክንያት እንደ አከራዩ ንብረቱን ለሌላ አገልግሎት ሊጠቀምበት በማሰቡ ምክንያት ከሆነ የማስወጣት ሂደቱን ማስቆም አይችሉም አንድ ግዜ መጠየቂያው ከደረስዎ እና አከራዩ በተገቢው የህግ መንገድ ሄዶ ከነበረ ማሳወቂያም ደርሶታል የመሳተፍ እድልም ገጥሞታል፡፡

የገንዘብ ውሳኔ ምንድ ነው?

ለአከራዩ መክፈል ያለቦት ገንዘብ ካለ አከራይዎ ለሚቀረው ያልተከፈለ ገንዘብ ውሳኔ በርሶ ላይ ሊሰጠው ይችላል፡፡ አከራይዎ የገንዘብ ውሳኔ በእርሶ ላይ መብት እንዲኖረው የሚሆነው ለእርሶ መድረስ የሚገቧቸው ቅሬታዎች እና ትእዛዞች በቀጥታ ደርሰዎት ከነበረ እና የመልሶ ይገባኛል ጥያቄ፣ ማካካሻ ወይም መተኪያ ጠይቀው የነበረ ከነበር ነው፡፡

የገንዘብ ውሳኔ ማለት እርሶ በህጋዊ መንገድ ለአከራዩ የተጠቀሰውን ያክል ገንዘብ ከነወለዱ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ህግ ነው፡፡ ለአከራይዎ ገንዘቡን ካልከፈሉ በስራዎ ወይም በባንክ ደብተርዎ ላይ ያለውን እና የታገደውን ገንዘብ እንዲወስድ ይደረጋል፡፡ ይህም ደሞዝዎን ወይም የባንክ ደብተርዎን "ማስያዝ" ይባላል፡፡

አከራይዎ የገንዘብ ውሳኔ ከተወሰነለት በኋላ ደሞዝዎን ወይም የባንክ ደብተርዎን ለማስያዝ አስር(10) የስራ ቀናት እንዲጠብቅ ይገደዳል፡፡

አከራይዎ የገንዘብ ውሳኔውን በአከራይ ተከራይ ፍርድ ቤት ውስጥ ማግኘት ካልቻለ እና እርሶ ገንዘቡን ካልከፈሉት በአነስተኛ ጥያቄ ፍርድ ቤት ወይም በሲቪል እርምጃ ክፍል ሊከስዎ ይችላል፡፡

ከደምወዜ ላይ ወይም ከባንክ ደብተሬ ላይአከራዬገንዘቤን እንዳይወስድ ማድረግ የምችልበት መንገድ ይኖራል?

የገንዘብ ውሳኔው በእርሶ ላይ መወሰን የለበትም ብለው ካመኑ ውሳውን ለማስቀልበስ ጠበቃ ማናገር ይኖርቦታል፡፡

በአንዳንድ ጉዳዮች፤ የገንዘብ ውሳኔ ተወስኖም አከራይዎ ገንዘብዎን እንዳይወስድ ሊገደድ የሚችልባቸው የተወሰኑ የገንዘብ ምንጮች አሉ፡፡ ገቢዎ ከመያዝ የተጠበቀ እንደሆነ ካመኑ፤ አከራይዎን በአፋጣኝ ሊነግሩት ይገባል፡፡ ለፍርድ ቤትም አቤቱታ በማስገባት አከራዮ ገንዘብዎን ከመውሰድ እንዲቆጠብ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ በተቻለ መጠን በፍጥነት እርምጃ መውሰድ እና ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ ይጠበቅቦታል፡፡ ይህንን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ለማወቅ ከጠበቃ መነጋጋር ይኞርቦታል፡፡

የተጠበቁ የገቢ ምንጮች፡

 • የማህበራዊ ደህንነት
 • ተጨማሪ የደህንነት ገቢ (SSI)
 • የማህበራዊ ደህንነት የአካል ጉዳት ዋስትና (SSDI)
 • የቀድሞ ወታደር ጥቅማ ጥቅም
 • የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ የጡረታ ጥቅሞች
 • የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ የአገልግሎት ክፍያ
 • የአካል ጉዳት ጥቅማ ጥቅሞች
 • የማህበራዊ ድጋፍ/ TANF ጥቅማ ጥቅሞች
 • የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች
 • በጡረታ እና በድጎማ ፕላኖች ውስጥ የሚደረጉ ክፍያዎች*
 • አልሞኒ፣ ድጋፍ ወይም የተለየ እገዛ*
 • የሰራተኞች የካሳ ክፍያ
 • በሲቪል ወይም በወንጀለኛ ጉዳዮች ላይ በፍርድ ቤት የታዘዙ ክፍያዎች*
 • ከባቡር መንገድ የተረፉ የጡረታ ጥቅማ ጥቅሞች
 • የፌዴራል ዳኞች የካሳ ክፍያ
 • የሎንግሾር እና ሀርበር ሰራተኞች የካሳ ጥቅማጥቅሞች
 • የሲማንስ ወይም የማስተርስ ወይም የአሳ አጥማጆች ደመወዝ
 • የብላክ ለንግ ጥቅማ ጥቅሞች

*ገደብ ተፈጻሚ ሊሆን ይችላል፡፡

ስለ ውሳኔ እና ማቆምማስወጣቶችይጫኑ እዚህ.

ወደ ላይ ተመለስ

10. የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት እና የደህንነት ማስያዣ

አከራዬችግሮችን ወይም የቤት ውስጥ ህግ ጥሰቶችን እንዲያስተካክል ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?

ችግሮችን ለአከራይዎ በፅሁፍ ያሳውቁ፡፡ የእያንዳንዱን የላኩትን ማሳወቂያ ግልባጭ ያስቀምጡ፡፡ እንዲሁም፤ ከድርጅቱ አስተዳደር ወይም ከቤቱ ባለቤት ጋር ስለተከራዩት ቤት የጠወያዩአቸውን ነገሮች ማስታወሻ ይያዙ፡፡ ቀኑን እና ሰዓቱን እንዲሁም ከማን ጋር እንደተነጋገሩ መዝግበው ይያዙ፡፡ አሁንም የቤቱ ባለቤት ችግሮችን ለመፍታት ካልሞከረ ሌላ ብዙ አማራጭ አሎት፡፡

 • የቤት ተቆጣጣሪ ቤቱን እንዲጎበኝ እና አሉ የሚላቸውን የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰቶች እንዲያሳውቅ ይጠይቁ፡፡ ቀጠሮ ለማስያዝ በ (202) 442-4400. ይደውሉ፡፡ ቤቱ በሚታይበት ወቅት ለተቆጣጣሪው ያሉትን ችግሮች ለማሳየት በቦታው ቢገኙ ጥሩ ነው፡፡ ተቆጣጣሪው የጉብኝቱን ሪፖርት ለአከራይዎእና ያዛልአከራይዎእድሳት ማድረግ ያለበትን በተወሰነ የግዜ ገደብ ውስጥ እድሳት እንዲያደርግ ለመንገር ይልካል፡፡
 • ጉዳዮን በሀውሲንግ ኮንዲሽን የቀን መቁጠሪያ ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የሲቪል እርምጃዎች ክፍል የቤቱአከራይእድሳት እንዲያደርግ የሚጠይቅ የፍርድቤት ትእዛዝ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ በዚህ ፍርድቤት ተመላሽ ገንዘብ አያገኙም፤ ነገር ግን በልዩ ጉዳይ ትንንሽ ጥያቄዎች በሚታዩበት ፍርድቤት እስከ 10,000$ ድረስ ማመልከት ይችላሉ፡፡ ይጫኑ እዚህ ለበለጠ መረጃ ጉዳይን እንዴት በሀውሲንግ ኮንዲሽን ካሌንደር ላይ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 • በሲቪል እርምጃዎች ክፍልአከራይዎእድሳት እንዲያደርግ እና የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት በነበረበት ወቅት ለቤት ኪራይ ከተገቢው በላይ ወጪ በማውጣቶ የተነሳ ለኪራይ ያወጡትን ገንዘብ እንዲተካ መደበኛ የሆነ ጉዳዮን ማስገባት ይችላሉ፡፡ (ክሱየሚጠይቀው ገንዘብን ብቻ ከሆነ፤ በአነስተኛ ጥያቄዎች ፍርድቤት ከ10,000$ በላይ መጠየቅ ይኖርቦታል)
 • የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰቱ በጣም ከባድ ከሆነ(ለምሳ በክረምት ወቅት ሙቀት አለመኖር) በአፋጣኝ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲቪል እርምጃዎች ክፍል ለጊዜያዊ የእገዳ ትእዛዝእንደ ሀውሲንግ ኮንዲሽን ካሌንደሩ አካል ወይም እንደ መደበኛየሲቪል እርምጃማመልከት ይችላሉ፡፡
 • የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰቱ ያን ያህል ከባድ ካልሆነየተከራይማመልከቻ ለሬንታ አኮሞዴሽን ዲቪዥን (RAD) ማስገባት ይችላሉ፡፡ ይህ ኤጀንሲ ተከራዮችን በአከራዮቻቸው ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ይፈቅዳል፡፡ ደንቡ እና ሂደቱ መደበኛ ያልሆነ ሲሆን ይህንን ለማስኬድ ተከራዮች በአብዛኛው ጠበቃ አይፈልጉም፡፡ ነገር ግን፤አከራዮየታዘዘውን የማይፈፅም ከሆነ፤ ኤጀንሲው ትእዛዙን ለማስፈፀም ያለው አቅም ውስን ነው፡፡
 • እርምጃዎችን በትንንሽ ጥያቄዎች ፍርድቤት ያምጡ፡፡ አከራይዎቤቱን ላደሱበት ገንዘብዎን ተመላሽ ማድረግ አለበት ብለው ካመኑ ወይም ደግሞአከራይዎበመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት በነበረበት ወቅት ለቤት ኪራይ ከተገቢው በላይ ወጪ በማውጣቶ የተነሳ ለኪራይ ያወጡትን ገንዘብ እንዲተካ ከፈለጉ እርምጃዎችን በትንንሽ ጥያቄዎች ፍርድ ቤት በማምጣት እስከ 10,000$ ድረስ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 • የቤት ኪራዮን መክፈል ማቆም ይችላሉ፡፡ ጉዳይን ማምጣት የሚችሉት አከራዮች ብቻ በመሆናቸው ወደአከራይ ተከራይፍርድ ቤት ከዳኛ ፊት ለመቆም ብቸኛው አማራጭ የቤት ኪራዩን በመያዝ አከራይዎ ራሱ ወደ ክስ እንዲወስድዎ መጠበቅ ይሆናል፡፡ አንድ ግዜ በአከራይ ተከራይፍርድቤት ከደረሱ ዳኛውንአከራይቤቱ ላይ እድሳት እንዲደረግ ዳኛው ትእዛዝ እንዲሰጡ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ መክፈል ከሚገባዎ ክፍያ ላይ ቅናሽ ሊደረግልዎም ይችላል፡፡ የወር ክፍያዎን ከያዙ፤አከራዮንበመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰት ምክንያት የቤት ኪራይ ክፍያዉን መያዝዎን ያሳውቁ፡፡ ምንም እንኳ በቤት ውስጥ እድሳት እንዲደረግአከራይዎንፍርድ ቤቱ ቢያስገድደውም በዛው ልክ አደጋም አለው፡፡ በአከራይ ተከራይፍርድ ቤት ከተከሰሱ፤ የእርሶን ቤትመልቀቅሊያስከትል ይችላል እንዲሁም ለወደፊቱ ሌላ አፓርትመንት መከራየት ከባድ እንዲሆንብዎ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ሁሉንም የኪራይ ገንዘብ ማጠራቀምዎን እርግጠኛ ይሁኑ ምክንያቱም ቤቱንከመልቀቅ ለማምለጥ የተወሰነውን ወይም አጠቃላይ ክፍያውን ለመክፈል ይገደዱ ይሆናል፡፡

በቤቶች ህግ ስር መብቶን ለማስከበር የሚያግዙ ነፃ የህግ አገልግሎቶች ሰጪዎች አሉ፡፡ ወይ የአከራይ ተከራይ መረጃ ማእከሉን ይጎብኙ ወይም አንዱን የህግ አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲ ያግኙ፡፡ "የህግ ድጋፍ ይፈልጉ" ወደሚለው ትር ይሂዱ፡፡

የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰትን እንዴት ማመልከት እችላለሁ?

የቤት ተቆጣጣሪ ቤቱን እንዲጎበኝ እና አሉ የሚላቸውን የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰቶች እንዲያሳውቅ ይጠይቁ፡፡ ቀጠሮ ለማስያዝ በ (202) 442-4400. ይደውሉ፡፡ ቤቱ በሚታይበት ወቅት ለተቆጣጣሪው ያሉትን ችግሮች ለማሳየት በቦታው ቢገኙ ጥሩ ነው፡፡

ለደህንነት ማስያዣያስቀመጥኩን እንዴት ነው የማገኘው?

አከራይዎ ቤቱን ከለቀቁ በኋላ የደህንነት ማስያዣዎንወይ ሙሉውን(ወለዱንም ጨምሮ) ለመላክ ወይም ደግሞ የገንዘቡን የተወሰነ መጠን ወይም ሙሉውን ካስቀረ ያስቀረበትን ማንኛውም አይነት ምክንያት በአርባ አምስት(45) ቀናት ውስጥ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ አከራይዎ ከደህንነት ማስያዣዎ ላይ የተወሰነ ለማስቀረት ማሰቡን የሚገልፅ ማሳወቂያ ከደረስዎት በኋላ አከርይዎ ቀሪውን ገንዘብ አስልቶ ለመላክ ሰላሳ(30) ቀናት ይኖሩታል፡፡ ቤቱን ከለቀቁ በኋላ በአርባ አምስት(45) ቀናት ግዜ ውስጥ ከአከራይዎ ምንም አይነት ነገር ካልደረስዎት ጉዳዩን ወደ አነስተኛ ጉዳዮች ፍርድ ቤት በማምጣት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ ይመልከቱ ስለ ቤት ኪራይ የደህንነት ማስያዣ ተዘውትረው የሚነሱ ጥያቄዎች.

ወደ ላይ ተመለስ

Last Review and Update: Feb 16, 2018
Back to top