Website Survey

በሞግዚትነት እና ጠባቂነት ዙሪያ ተዘውትረው የሚነሱ ጥያቄዎች

Authored By: Kenneth Rosenau, Esq. and Evan Greenstein, Esq.

Contents

Information

በሞግዚትነት እና ጠባቂነት ዙሪያ ተዘውትረው የሚነሱ ጥያቄዎች

ሞግዚት ምንድ ነው?

ሞግዚት ማለት በፍርድ ቤት የተሾመ የጤና አገልግሎት ውሳኔዎችን እና በአብዛኛው ከገንዘብ ጋር ያልተያያዙ ውሳኔዎችን በጉዳት በህመም ወይም በስነት የተነሳ በራሳቸው ማድረግ ለማይችሉ ሰዎች ውሳኔ የሚሰጥ ግለሰብ ማለት ነው፡፡

ጠባቂ ምንድ ነው?

ጠባቂ ማለት በፍርድ ቤት የሚሾም የአንድን በጉዳት፣ በህመም ወይም በስነት የተነሳ በራሳቸው ማድረግ ለማይችል ወይም ለማትችል ግለሰብ ገንዘብ ነክ ጉዳዮችን የሚከታተል ግለሰብ ማለት ነው፡፡

የቤተሰቤ አባል ወይም ጓደኛዬ ሞግዚት ወይም ጠባቂ ሊያስፈልጋቸው ይችላል?

 • አንዳንድ ግዜ ህመም፣ መጎዳት ወይም ስነት ለአንድ ሰው ስለሚያገኘው የጤና አገልግሎት፣ ስለ ገንዘብ፣ ስለ መኖሪያ ሁኔታ ወይም ሌሎች የግል ጉዳዮች ውሳኔ ለመወሰን እማይችልበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ የሚከተሉት እንደ ምሳሌ ሊካተቱ ይችላሉ፡
  • ኮማ ውስጥ ያለ ሰው፡፡
  • የአእምሮ ችግር ያለበት ሰው፡፡
  • የመርሳት ችግር ወይም የሆነ ሌላ አይነት የአእምሮ ህመም ያለበት ሰው፡፡
  • ድንገተኛ ራስ መሳት አጋጥሞት የነበረ ሰው፡፡
  • በጭንቅላት ውስጥ ጉዳት ሲሰቃይ የነበረ ሰው፡፡
 • ፍርድ ቤት አንድ ግለሰብን ማንኛውንም ወይም የእሱን ወይም የእሷን አስፈላጊ የህይወት ውሳኔ መወሰን እንደማይችል ካወቀ ግለሰቡ ለውሳኔ አቅም የሌለው ሆኗል ማለት ነው፡፡
 • የአንድን ግለሰብ የውሳኔ አቅም ማጣት ለመወሰን ፍርድቤት ቃል የሚሰማበት እና እውነታውን የሚያጣራበት ሁኔታ ያዘጋጃል፡፡ ሁኔታው እሚያሳምን ሆኖ ካገኘው ግለሰቡ የውሳኔ አቅሙን በሚከተሉት ነገሮች ላይ መተግበር እንደማይችል ያረጋግጣል፡
  • ስለ ግለሰቡ የገንዘብ፣ የጤና አገልግሎት ውሳኔ ወይም የንሮ ሁኔታ በበቂ ሁኔታ በማንኛውም ወይም በሁሉም ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ላይ መወሰን ወይም
  • ስለ ፍላጎቱ እና ስለ ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች በግልፅ መነጋገር፡፡፡
 • ለዚህ የውሳኔ አቅም ለሌለው ግለሰብ ፍርድ ቤቱ ሞግዚት ወይም ጠባቂ ከመደበ ይህ ግለሰብ ዋርድ ይባላል፡፡

ፍርድ ቤት ሞግዚት የሚሾመው መቼ ነው ጠባቂስ?

 • በሁኔታዎች ላይ እና ዋርዱ በምን መልኩ አቅም እንደሌለው ይወሰናል፡፡ እያንዳንዱ ሁኔታ የተለያየ ነው፤ ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት የእያንዳንዱን ሁኔታ እውነታ ማየት ይኖርበታል፡፡
 • ጠባቂ መቼ እንደሚያስፈልግ ነገር ግን ሞግዚት እንደማያስፈልግ ምሳሌ፡ ሮኒ ኤች. በከባድ የመኪና አደጋ ውስጥ አልፎ መጠነኛ ጉዳት ጭንቅላ ላይ ደርሶበታል፡፡ ከአደጋው በኋላ፣ በቤተሰቦቹ የምድር ቤት ውስጥ ይኖራል፣ ቤተ ክርስትያን ይሄዳል፣ ቼዝ ይጫወታል እና ከተማ ውስጥ በራሱ በእግሩ ይዘዋወራል፡፡ ነገር ግን ሂሳብ የመስራት አቅም የለውም እና የኢንሹራንስ ሂደቱን ጠባቂው ሀላፊነት ወስዶ አስጨርሶለታል፣ ገንዘቡን ያወጣል፣ የቤት ኪራይ ይከፍልለታል እና በየወሩ የተወሰነ መጠን ያለው የኪስ ገንዘብ ይልክለታል፡፡
 • ሞግዚት መቼ እንደሚያስፈልግ ነገር ግን ጠባቂ እንደማያስፈልግ ምሳሌ፡ ዋንዳ ኤም. ከባድ የሆነ ራስን የመሳት ችግር አጋጥሟት ሙሉ በሙሉ የመናገርም ሆነ ስሜቷን የመግለፅ አቅም አጥታ ነበር፡፡ በዚህ የተነሳም በነርሶች ቤት ገብታ ነበር፡፡ ዋንዳ ምንም አይነት ከማህበራዊ ደህንነነቷ በቀር ምንም ንብረትም ሆነ ገቢ ስለሌላት የገንዘብ ነክ ውሳኔዎችን እንድትወስን ጠባቂ አያስፈልጋትም ነገር ግን የህክምና ውሳኔዎችን ለማድረግ ግን የግድ ሞግዚት ያስፈልጋታል፡፡
 • ለነዚህ ሀላፊነት ሌሎች ስቴቶች እንደ ተወካይ ወይም አስተማሪ ያለ የተለየ ቃል እንደሚጠቀሙ አስታውሱ

ፍርድ ቤት ሞግዚትም ጠባቂም ሊሸም ይችላል?

አዎ፤ ፍርድ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነ፡፡

አንድ ሰው በአንድ ላይ ሞግዚት እና ጠባቂ መሆን ይችላል?

አዎ፤ ነገር ግን ፍርድ ቤቱ የተለያዩ ሰዎችን እንደ ሞግዚት እና ጠባቂ እንዲያገለግሉ ሊሾምም ይችላል፡፡

ሞግዚት ገንዘብ ነክ ነገሮችን በሀላፊነት ሊያስተዳድር የሚችልበት አጋጣሚ ይኖረል?

 • ሞግዚት በጣም ትንሽ ገንዘብ ሊያስተዳድር ይችላል፤ ለምሳሌ ወርሀዊ አበል፣ የማህበራዊ ዋስትና ጥቅማ ጥቅሞችን፣ የቀድሞ ወታደሮች ጥቅማ ጥቅም እና የመሳሰሉትን፡፡
 • አንድ ሞግዚት በዓመት ከ24000 ዶላር በላይ ማስተዳደር ካለበት፤ በአብዛኛው ዳኞች ጠባቂ ይሾማሉ፡፡

ጉዳት የደረሰበት ሰውፍርድ ቤት ሞግዚትም ሆነ ጠባቂ እንዳይሾምበት ዘላቂ የውክልና ስልጣን መስጠት ይችላል?

 • አይችልም፤ ዘላቂ የውክልና ስልጣን ለመስጠት ውክልና ሰጪው ግለሰብ በግልፅ መረዳት የሚችል እና ምን እንደሚፈልግ ወይም እንደምትፈልግ በግልፅ መጥቀስ የሚችሉበት ደረጃ ላይ መሆን አለባቸው፡፡ አንድ ግዜ የመወሰን አቅማቸውን ካጡ እና ሞግዚት ወይም ጠባቂ የሚያስፈልጋቸው ደረጃ ላይ ከደረሱ በኋላ ግለሰቡ ትክክለኛ እና ዘላቂ የሆነ የውክልና ስልጣን መስጠት አይችሉም፡፡
 • ዘላቂ የሆነ የውክልና ስልጣን ሰነዱ ግለሰቡ በራሱ መወሰን በማይችልበት ጉዳት ላይ ሆኖ የፈረመው መሆኑን ከደረሰበት ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደርገዋል(በሌላ ቋንቋ ይሰርዘዋል)፡፡
 • ጠቅ ያድርጉ እዚ ጋ ዘላቂ ስለሆነ የውክልና ስልጣን በጤና አገልግሎት ላይ የበለጠ መረጃ ያገኛሉ፡፡
 • ጠቅ ያድርጉ እዚ ጋ አጠቃላይ የውክልና ስልጣን ላይ የበለጠ መረጃ ያገኛሉ፡፡

ግለሰቡ ጉዳት ሳይደርስበት በፊት ዘላቂ የውክልና ስልጣን ሰጥቶ ቢሆንስ?

 • የውክልና ስልጣኑ ግለሰቡ ውሳኔ መስጠት ባለበት ነገሮች ላይ ምን አይነት ውሳኔ መወሰን እንደሚፈልግ የገለፀ ከሆነ(ገንዘብ ነክ ነገሮች፣ የጤና አገልግሎት፣ ወዘተ) በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው ወኪል ውሳኔ የመወሰን ስልጣን ይኖረዋል፡፡
 • ግለሰቡ ዘላቂ የውክልና ሰነድ ለአንድ ጉዳይ እና ለሌሎች ነገሮች ያላዘጋጀ ከሆነ (ለምሳሌ ለጤና አገልግሎት ዘላቂ የውክልና ስልጣን ሰጥቶ ነገር ግን ገንዘብ ነክ ለሆኑ ነገሮች ካልሰጠ) በውክልናው ላይ ላልተካተቱ ነገሮች ፍርድ ቤቱ ጣልቃ በመግባት ሞግዚት ወይም ጠባቂ ሊሾም ይችላል፡፡

ፍርድ ቤት ማንን ነው እንደ ሞግዚት ወይም ጠባቂ አድርጎ የሚሾመው?

 • የፍርድ ቤቱ የመጀመሪያ ምርጫ የግለሰቡ የቅርብ የቤተሰብ አባል ሲሆን በአብዛኛው የትዳር አጋር ወይም አብሮ የሚኖር በትዳር ያልተሳሰረ ግለሰብ ወይም ደግሞ ትልቅ ልጅን ነው፡፡
 • ምንም አይነት የቅርብ ቤተሰብ ከሌለ ወይም አመቺ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ ሌሎች ዘመዶችን ወይም ጓደኞችን እንደ አማራጭ ያያል፡፡
 • ምንም አይነት የቤተሰብ አባል ወይ ጓደኛ ከሌለ፤ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ የሆና በልዩ ሁኔታ የሰለጠነ ጠበቃ ነገሩን በቋሚነት እንዲከታተል ይመድባል፡፡

ሞግዚትን ወይም ጠባቂን እንደ አማራጭ ማየት ይኖርብኛል?

 • እንደ ሁኔታው ይወሰናል፡፡ ሞግዚት ወይም ጠባቂ መሆን በእርግጠኛነት የሚወዱት ሰው በትክክል እንክብካቤ እያገኘ መሆኑን ለማረጋገጥ ያስችሎታል፡፡ ነገር ግን ከባድ ሀላፊነትም ጭምር ነው፡፡
 • እንደ ሞግዚት ወይም ጠባቂ ለፍርድ ቤቱ እንደ ኦፊሰር ኖት እንዲሁም መደበኛ ሪፖርት ለዳኛው ያቀርባሉ፡፡ ይሄም በጣም ግዜ የሚወስድ ነገር ሊሆን ይችላል፡፡
 • ሞግዚት ወይም ጠበቃ መሆን የረዥም ግዜ ሀላፊነት ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ የእርሶን ቦታ የሚተካ ሌላ ሰው እስካልተካ ድረስ የህመምተኛውን ቀሪ ዘመን ሙሉ ያካትታል፡፡
 • ሞግዚትነት ወይም ጠባቂነት በጣም አስፈላጊ ስራ ነው፡፡ ስራውን በእርግጠኝነት እንደሚሰሩ ካላመኑ በስተቀር ይህንን ስራ መውሰድ የለቦትም፡፡

ወንድሜ ወይም እህቴ እና እኔ ለቤተሰባችን እንደ ሞግዚት ወይም ጠባቂ ሆነን ማገልገል ብንፈልግስ?

 • ሁለት በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ሞግዚት ወይም ጠባቂ መሆን ከፈለጉ፤ ፍርድ ቤቱ የታማሚው የተሻለ ምርጫ ሊሆን የሚችለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ይመርጣል፡፡ ጥያቄ ያቀረበውን ሰው ብቃት እና ብህሪ ከታወቁ የህመምተኛው ፍላጎቶች ጋር አብሮ መሄድ መቻሉ ከግምት ውስጥ ይገባል፡፡
 • ፍርድ ቤቱ የሞግዚትነት ወይም የጠባቂነት ጥያቄው የቤተሰቡን ወይም የታማሚውን ግንኙነት ስር በሰደደ መልኩ እንደሚጎዳ ካሰበ ሀለቱንም ጥያቄ አቅራቢዎች በመዝለል ለሌላ ሰው ሀላፊነቱን ይሰጣል፤ ብዙውን ግዜ በደንብ ሩቅ ለሆነ ዘመድ ወይም ገለልተኛ ለሆነ እና እንዲ ያሉ ነገሮችን ለማስተዳደር በልዩ ሁኔታ ለሰለጠነ ሰው ይሰጣል፡፡

የምኖረው ዲ.ሲ ካልሆነስ?

የሚኖሩበት ቦታ ለውጥ አያመጣም፡፡ ፍርድ ቤቱ የሚያሳስበው የህመምተኛው መገኛ ቦታ ብቻ ነው፡፡

የቤተሰቤ አባል የሆነ ሰው ወይም ጓደኛዬ በዲ.ሲ. ሆስፒታል ውስጥ ቢሆኑ እና ግን የሚኖሩት በዚህ ዲስትሪክት ውስጥ ባይሆንስ?

 • የህመምተኛው መገኛ በዲስትሪክቱ ውስጥ ይሁን እንጂ የዲ.ሲ ፍርድ ቤት የሞግዚትነት ወይም የጠባቂነት ጥያቄዎን ሊሰማ ይችላል፡፡
 • ህመምተኛው የሚኖርበት ቦታ ለውጥ አያመጣም፤ ዋናው ነገር ጥያቄዎን በሚያቀርቡበት ግዜ እና በፍርድ ቤት በሚሰማበት ወቅት ህመምተኛው በአካል በዲስትሪክቱ ክልል ውስጥ መኖር ይኖርበታል፡፡

ለሞግዚትነት ወይም ለጠባቂነት የማመለክተው የት ሄጄ ነው?

የሞግዚትነት እና የጠባቂነት ማመልከቻ የሚገባው የእውቅና ክፍል በዲ.ሲ. የሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ አድራሻ ያገኙታል፤ 515 5th St. NW, 3rd floor, Washington, DC 20001፡፡

ለሞግዚትነት ወይም ጠባቂነት ለማመልከት ቀጠሮ ለማስያዝ ምን ያህል መክፈል ይጠበቅብኛል?

 • ለሞግዚትነት ለማመልከት ክፍያ የለውም፡፡
 • ለጠባቂነት ለማመልከት ግን 45 ዶላር ለማመልከቻ ያስከፍላል፡፡

የማመልከቻ ገንዘቡን መክፈል የማልችል ከሆነስ?

 • ፍርድ ቤቱ መክፈል ካልቻሉ ክፍያው እንዲነሳ ሊያደርግ ይችላል፡፡
 • በነፃ ለማመልከት፤ ያለቅድመ ክፍያ፣ ወጪ ወይም ደህንነት(በ ፎርማ ፓፔሪስ) ለመቀጠል የሚያስችሎትን መጠየቂያ ማስገባት ይኖርቦታል፡፡ ተገቢውን ቅፅ ማግኘት ይችላሉ እዚህ እና ኮምፒውተሮ ላይ መሙላት ይችላሉ፡፡ እሱንም ለፍርድ ቤት የግድ ማመልከት እና ለጉዳዮ ከሌሎች አስፈላጊ ወረቀቶች ጋር አብረው ይዘው መቅረብ ይኖርቦታል፡፡
 • የህዝብ ትቅማ ጥቅም (TANF፣ POWER፣ GAC፣ Food Stamps፣ IDA፣ SSDI፣ ወይም SSI) የሚያገኙ ከሆነ ፍርድ ቤቱ በአብዛኛው የማመልከቻ ክፍያውን ያነሳሎታል፡፡ አለበለዚያ፤ የማመልከቻ ክፍያውን መክፈል ከባድ የሚሆንቦትን ምክንያት ለፍርድ ቤቱ ማስረዳት ይጠበቅቦታል፡፡
 • ቅፁን ሞልተው ሲጨርሱ፤ በ500 Indiana Ave., NW, Room 4220 በሚገኘው ዋናው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንፃ ውስጥ ለፍርድ ቤቱ ዳኛ ማስገባት ይኖርቦታል፡፡
 • የፍርድ ቤቱ ዳኛ ጥያቄዎን ከተቀበለ፤ የዳኛውን ትእዛዝ የያዘ ግልባጭ ይደርሶታል፡፡ ለጠባቂነት በሚያመለክቱበት ወቅት ትእዛዙን ለማረጋገጫ ክፍሉ ከማመልከቻዎ ጋር በጋራ ይዘው ይሂዱ፡፡ የማመልከቻ ክፍያዉን መክፈል አይጠበቅቦትም፡፡
 • አስታውሱ ለሞግዚትነት ምንም አይነት ክፍያ መክፈል አይጠበቅቦትም፡፡

የማመልከቻ ወረቀቴን እና ሌሎች ወረቀቶችን ካስገባሁ በኋላ የግድ ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?

 • ማመልከቻዎን እና ሌሎች ወረቀቶችን ለፍርድ ቤቱ ሲያስገቡ የማረጋገጫ ክፍሉ ፀሀፊ የፍርድ ቤት መሰሚያ ቀን ማሳወቂያ ይሰጦታል፡፡
 • ታማሚው የፍርድቤት መሰሚያ ማሳወቂያው ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት ያስገቧቸው ወረቀቶችን ጨምሮ እንደደረሰው እርግጠኛ መሆን ይኖርቦታል፤ ይህም የመጥሪያውን መድረስ ማረጋገጥ ተብሎ ይጠራል፡፡
 • መጥሪያውን የሚያቀብለው ሰው በቀጥታ ለዋርዱ በእጁ መስጠት አለበት፡፡
 • እንደ አጋጣሚ ሆኖ መጥሪያውን የሚያደርሰው ሰው ዋርዱን በአካል ማግኘት ባይችል እና ነገር ግን ዋርዱ ቤት ውስጥ ቢኖር በታማሚው ቤት ለሚኖ ማንኛውም ትልቅ ሰው መስጠት ይቻላል፡፡ ነገር ግን የሚቻል ከሆነ መጥሪያውን በቀጥታ ለዋርዱ በእጁ መስጠት የተሻለ ነው፡፡
 • መጥሪያውን የሚያደርሰው ሰው በዋርዱ ቤት ለሌላ ሰው የሚሰጥ ከሆነ ለዳኛ የተቀበለው ሰው ከዋርዱ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ስለመኖራቸው ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

ለጓደኛዬ ወይም ለቤተሰቤ አባል መጥሪያውን ማን ሊሰጥ ይችላል?

 • ማንኛውም ግለሰብ እድሜው ቢያንስ 18 አመት የሞላው እና የጉዳዩ አካል ያልሆነ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ምንም ፍላጎት የሌለው ሰው ቢሆን ይሻላል፡፡
 • እርሶ በጭራሽ መሆን የለቦትም፡፡
 • ጓደኛ መሆን ይችላል ነገር ግን ዘመድ በጭራሽ መሆን የለበትም፤ ምክንያቱም ዘመድ ከሆነ ምናልባት ገና ባላወቁት ጉዳይ ላይ የገንዘብ ፍላጎት ሊኖረው ወይም ሊኖራት ይችላል፡፡
 • የግል ጉዳዮችን የሚያስፈፅም ሰው መቅጠር ይችላሉ (በቢጫው ገፅ ስር ላይ “ጉዳይ አስፈፃሚ” የሚለውን ይመልከቱ)
 • ጓደኛዎን ወይም የቤተሰቦን አባል የሚንከባከቡ ነርሶች ወይም ዶክተሮች መጥሪያውን መስጠት የለባቸውም፡፡

ጓደኛዬ ወይም የቤተሰቤ አባል ኮማ ውስጥ ሆኖ አንብቦ መረዳት የማይችል ቢሆንስ?

 • ምንም ለውጥ አያመጣም፡፡ ህጉ እንደዛም ሆኖ የወረቀቶቹ ግልባጭ ለዋርዱ እንዲደርስ ይጠብቃል እሱ ወይም እሷ ማንበብ ባይችሉም እንኳ፡፡
 • አንዳንድ ግዜ የመጥሪያ ወረቀቱን ማድረስ ማለት ኮማ ውስጥ ያለን ግለሰብ እጅ አንስቶ ወረቀቱን ከስሩ ማስቀመጥ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

መጥሪያውን በምን ያህል ግዜ ማድረስ አለብኝ?

 • ማመልከቻ ካስገቡ ቀን ጀምሮ ባሉ ሶስት ተከታታይ ቀናት ለዋርዱ የመጥሪያ ወረቀቱን ማድረስ ይኖርቦታል፡፡
 • በተባለው ግዜ ማድረስ ካልቻሉ ሶስቱ ቀናት ከመጠናቀቃቸው በፊት እውቅና መስጫ ወይም የማረጋገጫ ክፍሉ ፀሀፊ ቢሮ መሄድ አለብዎ፡፡ ተጨማሪ ሶስት ቀን ያለው አዲስ የፍርድ ቤት ማሰሚያ ማስታወቂያ ይሰጦታል፡፡
 • ከዚያ በኋላ ተጨማሪ ግዜ የሚፈልጉ ከሆነ፤ የፅሁፍ መጠየቂያ ማመልከቻ ማስገባት እና ዳኛው አይቶ ማፅደቅ ይኖርበታል፡፡
 • ዋርዱ መጥሪያውን ቢያንስ ከፍርድ ቤት መሰሚያ ቀኑ ከ15 ቀን በፊት ሊደርሰው ይገባ፡፡

የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ከተሰጠ በኋላ ምን ማድረግ አለብኝ?

 •  መጥሪያውን ለዋርዱ የሰጠው ግለሰብ የግለሰብ አገልግሎት መስጠት ምስክርነት መሙላት አለበት ቅፁን ለማውረድ እዚህ ጋ ተጫኑ ከዚያም ኮምፒውተር ላይ ይሙሉ፡፡ የግድ በወረቀት አትመው ለፍርድ ቤቱ ማስገባት ይኖርቦታል፡፡
 •  የአገልግሎቱ ምስክርነት ቀን፣ የአማካይ ሰዓት፣ እና መጥሪያው የተሰጠበት ቦታ፡፡ በተጨማሪም መጥሪያውን የሰጠው ሰው እድሜው ከ18 ዓመት በላይ መሆኑን እና የጉዳዩ አካል የሆነ ግለሰብ አለመሆኑን የሚጠቅስ መሆን አለበት፡፡
 • ለህመምተኛው መጥሪያውን ያደረሰው ሰው አገልግሎቱን ስለመስጠቱ የግድ መፈረም እና ማረጋገጥ አለበት፡፡
 • የተፈረመውን እና የተረጋገጠውን የአገልግሎት ምስክርነት ወረቀት ለፍርድ ቤቱ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡

ቀጥሎ ምን ይፈጠራል?

 • ዳኛው በሂደቱ ውስጥ እንዲያግዙት ወይም እንዲያግዟት በርካታ ሰዎችን ይመድባል፡፡
  • ለፍርድ ቤቱ መረጃ እና ሪፖርት የሚያቀርብ ሞግዚት፡፡
  • የህመምተኛውን ፍላጎት የሚጠብቅ ጠበቃ፡፡
  • ጎብኚ፣ በአጠቃላይ የማህበረሰብ ሰራተኛ፣ የአእምሮ ህመሙን የሚያጣራ ፡፡
  • ፈታኝ፤ የህመምተኛውን አቅም የሚፈትሽ አይነተኛ ዶክተር፡፡
 • በዳኛው የተመደቡት ሰዎች የማጣራት ስራውን ይሰራሉ ታማሚውን እና የቤተሰቡን አባል ጨምሮ እና ለዳኛው ሪፖርት ያደርጋል፡፡
 • ዳኛው ሞግዚት ወይም ጠባቂ ለመሾም የፍርድ ቤት መሰሚያ ቀን ይወስናል፡፡

የፍርድ ቤት መሰሚያው መቼ ይሆናል?

 • የፍርድ ቤት መሰሚያ ቀን ብዙውን ግዜ ከተመለከተበት ቀን ከአምስት ሳምንት በኋላ ነው፡፡
 • ፍርድ ቤቱ በሰሚያው ቀን ያገኞታል፡፡
 • የመሰሚያውን ቀን ለመቀየር ከፈለጋችሁ ለማረጋገጫ ክፍሉ ፀሀፊ በዚህ ቁጥር (202) 879-4800 በአፋጣኝ ይደውሉ፡፡
 • ለአደጋ ግዜ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ለማወቅ ከዚህ በታች ያለውን መረጃ ያንብቡ፡፡

ታማሚው በፍርድ ቤት መሰሚያ ቀን መምጣት አለበት?

 • የህመምተኛው የፍርድ ቤት- ተመዳቢ ጠበቃ የተሻለ የሚለውን ሀሳብ ለዳኛው ያቀርባል፤ ዳኛውም በአብዛኛው ሀሳቡን ያፀድቃል፡፡
 • ህመምተኛው ለፍርድ ቤቱ ሂደት የሚጨምረው ያን ያህል አስፈላጊ ነገር ከሌለ ወይም ደግሞ ግራ መጋባት ወይም ጉዳት ላይ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ባይመጣ ችግር አይኖረውም፡፡ በአብዛኛው ህመምተኛው በአየር ማቀዝቃዣ ላይ ከሆነ፣ የመናገር፣ ወይም የመንቀሳቀስ አቅም ከሌለው ወይም ከባድ ጉዳት ላይ ከሆነ አይገኝመም፡፡

በፍርድ ቤት መሰሚያ ቀን ምን ይፈጠራል?

 • የሞግዚትነት እና የጠባቂነት ጥያቄ በሚጠበቅበት ወቅት ችሎቱ በአብዛኛው ባዶ ነው የሚሆነው፡፡ ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ፍርድ ቤቱ ሰዎች መጥተው ማየት ቢፈልጉ እንኳ ሳይፈቅድ በዝግ ችሎት ነው የሚያካሂደው፡፡
 • በአብዛኛው የመስማት ሂደቱ መደበኛ ያልሆነ ነው፡፡ ሰዎቹ እና ጠበቆቻቸው ከችሎቱ ፊት በቀላሉ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ዳኛውን ያናግሩታል፡፡
 • ጠበቃ ካሎት ጠበቃዎ ጥያቄዎች ይጠይቆታል፡፡ ጠበቃ ከሌሎት ቀለል አድርገው ዳኛውን ለምን እንደ ሞግዚት ወይም ጠባቂ መመደብ እንደሚፈልጉ እና ለስራው ለምን ብቁ እንደሆኑ ያስረዳሉ፡፡
 • የህመምተኛው ጠበቃ ጥያቄዎች ሊጠይቖት ይችላል፤ ነገር ግን በአብዛኛው አይጠይቁም፡፡
 • በአብዛኛው የግድ አስፈላጊ ባይሆንም፤ እርሶ(ጠበቃዎ) እና የታማሚው ጠበቃ ለ ማመልከቻው የሚያግዝ የምስክርነት ቃል የሚሰጥ ሰው በማቅረብ የእርስ በርሳችሁን ምስክሮች ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 • ሰነዶችን ወይም ሌሎች ማስረጃዎችን ለዳኛው ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ሊያህዘኝ የሚችል ጠበቃ እንዴት ማግኘት እችላለለው?

 • ይጫኑ እዚህ ጋ ሊረዷችሁ ለሚችሉ ድርጅቶች ዝርዝር፡፡
 • እርሶን ወክሎ የሚቀርብ የግል ጠበቃ ሊያገኙ እና ፍርድ ቤቱን ከዋርዱ ሀብት ላይ ወይም ከልዩ ገንዘብ ላይ እንዲከፈል መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ይህ እንዴት እንደሚሰራ ለማወቅ የሚቀጥለውን ጥያቄ ተመልከቱ፡፡
 • ይጫኑ እዚህ ጋ የግል ጠበቃ ስለመቅጠር ጠቃሚ መረጃ፡፡

በእነዚህ መሰማቶች ወቅት ጠበቃዎች ክፍያቸውን የሚያገኙት እንዴት ነው?

 • ከመከፈላቸው በፊት ሁሉም ጠበቃዎች (የዋርዱ እና ካሎት የእርሶ ጠበቃ) የክፍያ ዝርዝራቸውን የሚገልፅ የክፍያ መጠየቂያቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ሁሉም አካላት የሌላኛውን ክፍያ ለመቃወም 21 ቀናት አላቸው፡፡ ከዚያ በኋላ፤ ዳኛው የጠበቃዎቹ ክፍያ እንዲፈፀም ትእዛዝ ያወጣል፡፡
 • የጠበቃ ክፍያ በአንድ ወይም በሁለት መንገድ ይፈፀማል፡
  • ዋርዱ በቀላሉ ሊወሰድ የሚችል ንብረት ካለው ጠበቃዎቹ ከዛ ላይ እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡፡
  • ጠበቃዎቹ በአብዛኛው የሚጠይቁት ኮንግረንሱ ካቋቋመው እና ከሰበሰበው የልዩ ሞግዚትነት ገንዘብ ላይ እንዲከፈላቸው ነው፡፡ ዋርዱ ምንም አይነት ገንዘብ ከሌለው ወይም ገንዘቡ መሸጥ ከማይቻል ቤት ጋር የተሳሰረ ከሆነ የጠበቃ ገንዘብ ከሞግዚትነት ገንዘቡ ላይ ይከፈላል፡፡

ምን ማለት ነው

 • እንደ ጠባቂ ከተመደቡ ማስያዣ ቦንድ ማቅረብ ይኖርቦታል፡፡
 • ሞግዚት ማስያዣ ቦንድ ማቅረብ አይጠበቅበትም፡፡
 • የፍርድ ቤት ቃል ከተሰማ በኋላ እና ጠባቂነቱ ከተፈቀደልዎ በኋላ ማስያዣ ቦንድ የሚያቀርቡት እርሶን ወክለው ቦንድ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች ጋ በመሄድ ይሆናል፡፡
 •  የማስያዣው አላማ ጠባቂው መስራት ያለበትን ስራ በአግባቡ ካልሰራ፣ የዋርዱን ንብረት ከጠፋበት ወይም ከሰረቀ የዋርዱ ንብረት ደህንነት የተጠበቀ ነው፡፡
 • የዋርዱ ንብረት በሆነ ምክንያት ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ ፍርድ ቤቱ የማስያዣ ድርጅቱን ያስያዘውን የቦንድ መጠን እንዲከፍል ያነጋግራል፡፡ ከዚያም የማስያዣ ድርጅቱ ለከፈለው ገንዘብ እርሶን በክስ ይጠይቃል፡፡ እንደ ቦንዱ ማስጠበቂያ ለድርጅቱ ያስያዙት ንብረት ቤት ከሆነ የማስያዣ ድርጅቱ ገንዘቡን ለማግኘት ንብረቶን ሊያሳግድ ይችላል፡፡
 • የጠባቂነት ጥያቄዎ በፍርድ ቤት በሚሰማበት ወቅት ፍርድቤቱ ማስያዣ ቦንድ ማቅረብ እንደሚችሉ ይጠይቆታል፡፡ ከፍርድቤቱ የችሎት ቀን ቀደም ብለው ለእርሶ ቦንድ ለማስያዝ ፈቃደኛ የሆነ የማስያዣ ድርጅት በመፈለግ ከድርጅቱ ደብዳቤ ይዘው መምጣት ይኖርቦታል፡፡
 • የቦንድ ማስያዣ ድርጅት ከቢጫ ገፆች ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የማስያዣ ቦንድ የሚሰጡ ድርጅቶች በአብዛኛው የራሳቸው በቤት ላላቸው ሰዎች እና ቋሚ የሆነ የስራ ቅጥር ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች ቦንድ ይሰጣሉ፡፡ ክፍያቸውም በንፅፅር ዝቅተኛ ነው፡፡

የቤተሰቤ አባል ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ስለሆነ አፋጣኝ ሞግዚት ያስፈልገዋል፡፡ የዚህ ሂደት በፍጥነት መሆን ይችላል?

 • በድንገተኛ አደጋ ግዜ፤ ፍርድ ቤቱ ለ90 ቀናት የሚቆይ ግዜያዊ የጤና አገልግሎት ሞግዚት ወይም ለ15 ቀና የሚቆይ የድንገተኛ አደጋ ሞግዚት ያዛል፡፡
 • ይጫኑ እዚህ ጋ የ15-ቀን የድንገተኛ ሞግዚት ለማግኘት እንዲመደብ ለመጠየቅ፡፡  ቅፁን በቀጥታ በድህረ ገፁ ላይ መሙላት ይችላሉ ነገር ግን የታተመውን የወረቀት ግልባጭ ለፍርድ ቤት ማስገባት ይኖርቦታል፡፡
 • የ90-ቀን ጊዜያዊ የጤና አገልገግሎት ሞግዚት እንዲመደብ ፍርድ ቤቱን ለመጠየቅ ተገቢውን ፎርም ለማግኘት እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡ ቅፁን በቀጥታ በድህረ ገፁ ላይ መሙላት ይችላሉ ነገር ግን የታተመውን የወረቀት ግልባጭ ለፍርድ ቤት ማስገባት አለቦት፡፡
 • ለጊዜያዊ ወይም ለድንገተኛ የምታመለክቱ ከሆነ የታቀደውን ትእዛዝ ፍርድ ቤቱ እንዲፈርምበትም ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ ለሚፈልጉት ቅፅ እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡ አሁንም ለፍርድ ቤት ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡
 • የግዜያዊ ወይም የድንገተኛ ማመልከቻ ለማስገባት በመጀመሪያ 515 5th St. NW 3rd Floor ላይ ወዳለው የእውቅና መስጫ ማረጋገጫ ፀሀፊ ቢሮ በመመሄድ ለቋሚ የሞግዚትነት ጥያቄ ማመልከቻ ያስገቡ፤ ከዚያም ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛው በማለፍ 500 Indiana Ave., NW, ቢሮ ቁጥር 4220 በመሄድ የድንገተኛ ጥያቄዎን ማመልከቻ ያስገቡ፡፡
 • በአብዛኛው ዳኛው ለጊዜያዊ ወይም ድንገተኛ የፍርድ ቤት ችሎት መስሚያ ቀን በ7 ቀን ግዜ ውስጥ እንዲኖሮት ያደርጋል፡፡ ሁኔታው በጣም አፋጣኝ ከሆነ በድንገተኛ ማመልከቻዎ ላይ መጥቀስ ያስፈልጋል፤ ዳኛው የመስሚያ ቀኑን የበለጠ ፈጠን ሊያደርግሎ ይችላል፡፡

የግዜያዊ ሞግዚት አገልግሎት የተሰጠኝ ግዜ የቋሚ ሞግዚት ጥያቄ መሰሚያ ቀኔ ከመድረሱ በፊት ቢያበቃስ?

በጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሚገኘው ዳኛ የግዜያዊው ሞግዚት አገልግቱ እንዲራዘም የሚጠይቅ አቤቱታ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡  ይጫኑ እዚህ ጋ አቤቱታውን ለማቅረብ ለሚፈልጉት ቅፅ፡፡ አሁንም ለፍርድ ቤት ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡

ዳኛው እንደ ሞግዚት ወይም ጠባቂ ከመደበኝ ምን ይፈጠራል?

 • የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ በፅሁፍ ይደርሶታል፡፡ ይሄንን ወረቀት ይዘው የእውቅና መስጫ ክፍሉ ወደሚገኝበት 515 5th St., NW 3rd Floor ወዳለው ውል መመዝገቢያ ቢሮ ይሂዱ፡፡
 • የውል መመዝገቢያ ቢሮው የዋርዱ ሞግዚት ወይም ጠባቂ ሆነው መመረጥዎን በመጥቀስ ደብዳቤ ያዘጋጅሎታል፡፡ ይህንን ደብዳቤ ለባንክ እና ለሌሎች ገንዘብ ነክ ነገሮች፣ ሆስፒታሎች፣ ለነርሲንግ ቤቶች፣ እና እርሶ ያን አይነት ስልጣን እንዳሎት ማረጋገጫ የሚፈልግ ቦታ ላይ ለቤተሰቦ አባል ወይም ጓደኛዎ ውሳኔ ለመወሰን ሲያስፈልጉ ያሳዩታል፡፡
 • የፍርድ ቤቱን ማዘዣ እና ከውል መመዝገቢያ የወሰዱትን ደብዳቤ በጥንቃቄ አስፈላጊ ከሆኑ ረጃዎችዎ መሀከል ያስቀምጡ፡፡

ሞግዚትነት ወይም ጠባቂነት ትእዛዝ በምን ያህል ግዜ ያልቃል?

አንድ ግዜ ፍርድ ቤቱ ሞግዚት ወይም ጠባቂ ከመደበ በኋላ ትእዛዙ የሚቆየው፡

 • ዋርዱ እስከሚሞት ድረስ
 • ከዚህ በኋላ ዋርዱ እንደበፊቱ አቅም ያነሰው መሆኑ ከቀረ እና ፍርድ ቤቱ ከደረሰበት(ለዚህ ዋርዱ ፍርድ ቤቱን መጠየቅ ይችላል)
 • ሞግዚቱ ወይም ጠባቂው ከሞተ ወይም ከለቀቀ፡፡
 • ለዋርዱ የተሻለ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል ፍርድ ቤቱ ሞግዚቱን ወይም ጠባቂውን ማሰናበት አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው፡፡

ዋርዱ ወይም መፐግዚቱ ወይም ጠባቂ ከዲስትሪክተ ለቀው ቢሄዱ?

ፍርድ ቤቱ ውድቅ እስከሚያደርገው ድረስ ሞግዚትነቱ ወይም ጠባቂነቱ በየትኛውም የዩናይትድ ስቴቶች ውስጥ እስካሉ ድረስ ችግር አይኖረውም፡፡

 

Last Review and Update: Jan 17, 2017
Back to top