ተቃውሞ የሌላቸው ፍቺዎች በዲሲ
Contents
Information
እርስዎ እና ባለቤትዎ የፍች ጉዳያችሁን በተመለከተ በሁሉም ነገር ከተስማማችሁ እና አስፈላጊዎቹን የፍች ሰነዶች ከፈረማችሁ የስምምነት ፍች ማግኘት ትችላላቸሁ። "በሁሉም ነገር" ማለት፣ ስለፍችው ከተስማማችሁ እና በተጨማሪም የልጅ አደራ፣ የልጅ ድጋፍ፣ አበል፣ እና የንብረት እና የዕዳ ክፍያን በተመለከተ እንዴት አድርጋችሁ መፍትሄ እንደምታገኙ ከተስማማችሁ ማለት ነው። በሌላ መንገድ፣ ፍርድ ቤቱ በእናንተ መካከል ስላለው ክርክር መግባት እንደሌለበት ተስማምታችኋል ማለት ነው።
የስምምነት ፍች ጉዳይ እንዴት አድርጌ መጀመር እችላለሁ?
ሰለጉዳይዎ ጠበቃ ማማከር ይችላሉ፣ ወይም እራስዎ ማመልከት ይችላሉ። አስፈላጊዎቹን የፍርድ ቤት ሰነዶች በwww.dcbar.org/pleadings ወይም በዲ.ሲ. ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቤተሰብ ፍርድ ቤት መካክለኛው የመመዝገቢያ ማዕከል ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ8:30 a.m. እስከ 5:00 p.m.ማግኘት ይችላሉ።
ለፍችው ማንኛችንም ብናመለክት ለውጥ ያመጣል?
እርስዎ ወይም ባለቤትዎ ጋብቻውን እስከመጨረሻው ለማቆም መጠየቅ ትችላላችሁ። ሌላው ወገን የስምምነት መልስ ያስገባል። አቤቱታውን ያቀረበው ሰው ከሳሽ ሲሆን ሌላው ወገን ተከሳሽ ይሆናል። ፍችው በስምምነት ከሆነ ከሳሽ ፍርድ ቤት ሄዶ በችሎት ምስክርነት ይሰጣል። ተከሳሽ ፍ ርድ ቤት መቅረብ ላይኖርበትም ይችላል።
ሰነዶቹን የት ነው የማስገባው?
Tአቤቱታውን ለማስገባት ወደ ዲ.ሲ. ከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ የቤተሰብ ፍርድ ቤት መካክለኛው የመመዝገቢያ ማዕክል (500 Indiana Avenue, NW)፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ8:30 a.m. እስከ 5:00 p.m. መሄድ ይችላሉ::
ሌላ ምን ማስገባት ያስፈልገኛል?
ከእርስዎ የአቤቱታ ማመልከቻ እና ከባለቤትዎ የተፈረመ የስምምነት መልስ በተጨማሪ የፍርድ ቤት የቀጠሮ ቀን እንዲሰጣችሁ በእርስዎ እና በባለቤትዎ የተፈረመ የስምምነት ሰነድ ማስገባት አለባችሁ። በተጨማሪም የቤተሰብ ፍርድ ቤት የማንነት ማረጋገጫ ቅጽ መሙላት ይኖርብዎታል።. እነኝህን ቅጾች በመካክለኛው የመመዝገቢያ ማዕክል ማግኘት ይችላሉ። ቅጹን ሲያስገቡ፣ ከፍርድ ቤቱ ፀኃፊ ቀን የታተመባቸው ግልባጮች ለግል መዝገብዎ መቀበልዎን ያረጋግጡ። የፍርድ ቤት ቀጠሮው ቀን መቼ መሆኑን የሚያመለክት ማስታዎሻ በፖስታ ቤት በኩል በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ይደርስዎታል።
ምን ያህል ገንዘብ ያስከፍላል?
$80 የማመልከቻ ክፍያ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በማኒ ኦርደር) ያስፈልግዎታል። መክፈል የማይችሉ ከሆነ በዲ.ሲ ክፍያ ማስቀሪያ የሚለውን መረጃ ያንብቡ።
ስምምነት ላይ ደርሰን ከሆነስ?
የተፈረመ የውሳኔ ስምምነት ካላችሁ እርስዎ እና ባለቤትዎ ከፍች ትዕዛዙ እንደ አንድ ክፍል አድርጋችሁ ለማያያዝ መስማማት ትችላላችሁ። ዳኛው ከጨመረው የትዕዛዙ አካል ይሆናል፣ ስለዚህ በኋላ ለቤተ ሰብ ፍርድ ቤት ማመልከቻ በማስገባት ውሳኔ ይደረሳል። ዳኛውን እንዲጨምሩት እርስዎ ካልጠየቁ፣ የትዕዛዙ አካል አይሆንም እና ወደፊት ሊወሰን የሚችለው ሌላ ማመልከቻ በማስገባት ብቻ ነው።
ተከሳሽ ለፍርድ ቤት ቀጠሮው መምጣት አለባቸው?
የለባቸውም። ሆኖም፣ አንዳንድ ዳኞች ተክሳሽ በበፊት ስማቸው እንዲጠሩ ከፈለጉ ወይም ከሳሽ ዲ.ሲ. ውስጥ የማይኖሩ ከሆኑ እና ተከሳሽ የዲ.ሲ. ተቀማጭ ከሆኑ ተከሳሽ ቢገኙ ይመርጣሉ።
ፍችው የሚያበቃው መቼ ነው?
ዳኛው ፍችውን ከፈቀዱ የፍች ትዕዛዙን ግልባጭ ወዲያውኑ ወይም በፖስታ ቤት በኩል ያገኛሉ። የፍችው ትዕዛዝ በፍርድ ቤቱ “ፋይል ገብቷል” ተብሎ ቀን ከታተመበት ከ30 ቀኖች በኋላ፣ (ይህም ከቀጠሮው ቀን ጥቂት ቀናት በኋላ ሊሆን ይችላል)፣ ፍችው የመጨረሻ ይሆናል። ሁለቱም ወገኖች በተባሉት 30 ቀኖች ውስጥ ይግባኝ በማቅረብ ፍርድ ቤቱ የፍችውን ትዕዛዝ እንዲያራዝም መጠየቅ ይችላሉ። የማራዘም ይግባኙ ከተፈቀደ፣ የይግባኙ ጥያቄ እስከሚፈታ ድረስ ትዕዛዙ የመጨረሻ አይሆንም። ማራዘሙ ካል ተፈቀደ፣ አቤቱታው በ ውሳኔ ላይ እያለ ትዕዛዙ ጽኑ ይሆናል። ሁ ለታችሁም የዳኛውን ትዕዛዝ ይግባኝ ላለመጠየቅ ከተስማማችሁ፣ በጋራ “የይ ግባኝ ማስቀሪያ ” ማስገባት ትችላላችሁ። ስለዚህ የ30 ቀን የመቆያ ጊዜ አይኖርም እና ትዕዛዙ ወዲያውኑ ጽኑ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ፣
በዲ.ሲ.ከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ የ ቤተ ሰብ ፍርድ ቤት ራስ አገዝ ማ ዕክል500 Indiana Avenue, NW, ክፍል ቁጥር JM-570 ያለቀ ጠሮ ለነ ጻ አ ገል ግሎት መሄድ ይችላሉ። ማዕከሉ ከሰኞ እስከ ዓርብ 8:00 am እስከ 5:30 p.m. ክፍት ነው። ማዕከሉ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ይገልጽልዎታል፣ ተገቢዎቹን የህግ ሰነዶች ይሞላልዎታል፣ እና ወደ ሌሎች ነጻ የህግ አገልግሎት የሚሰጡባቸው ቦታዎች ይመራዎታል። ለበለጠ መረጃ በድረ ገጽ www.lawhelp.org/dc ይመልከቱ፣ ነጻ የህግ አገልግሎት ሰጪዎችን ለማግኘት ወይም ስለጉዳዩ የተቀዳ መልእክት ለመስማት የዲሲ ባር የህግ መረጃ መስመር በ202-626-3499 ይ ደ ውሉ።
በስምምነት የፍች ቀጠሮ ቀን ዳኛው ምን ዓይነት ጥያቄዎች ይጠይቁኛል?
-
እባክዎን ለመዝገቡ ስምዎን፣ አድራሻዎን እና የልስክ ቁጥርዎን ይናገሩ።
- ለደህንነትዎ ከፈሩ ወይም በሌላ ሰው ውካቤ ወይም ጉዳት ይደርስብኛል ብለው ከፈሩ፣ ሌላ አድራሻ በምትኩ መስጠት እንደሚፈልጉ ለዳኛው ይንገሩ፣ ወይም ከመዝገቡ ውጭ ለዳኛው በቀጥታ ለመስጠት መጠየቅ ይችላሉ።
- በኮሎምብያ ዲስትሪክት ለስንት ጊዜ ኖረዋል?
- በዚህ ጉዳይ ተከሳሽ ማን ነው?
- ተከሳሽ ባለቤትዎ ናቸው።
- እርስዎ ወይም ባለቤትዎ የአንድ ዓይነት ፆታ ፍች በሚፈቅድ ስቴት ውስጥ ትኖራላችሁ?
- ባለቤትዎ በዚህ አድራሻ ለስንት ጊዜ ኖረዋል?
- የት እና መቼ ነው የተጋባችሁት?
- ዛሬ እዚህ የመጡት ፍች ለመጠየቅ ነው?
- የጋብቻ ሰርትፊኬትዎን አምጥተዋል? ይህ ግልባጭ ነው?
- የጋብቻ ሰርቲፊኬትዎን ለዳኛው እንዲያስተላልፉ ለዳኛው ፀኃፊ ይስጡ።
- የወለዳችኋቸው ወይም የጉዲፈቻ ልጆች አሏችሁ? ዕድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች ነው?
- መልስዎ አዎንታዊ ከሆነ፣ ዳኛው ከሚከተሉት ጥያቄዎች አንዳንዶቹን ሊጠይቁዎት ይችላሉ፣
- እባክዎ የልጅዎን(ጆችዎን) ስም(ሞች) እና የልደት ቀን(ኖች) ይናገሩ
- እያንዳንዱ ልጅ(ጆች) አሁን ይሚኖሩት የት ነው?
- ስለ ልጅ(ጆች) ከማንኛውም ፍርድ ቤት የልጅ አደራ፣ ጉብኝት ወይም ድጋፍን በተመለከተ ከዚህ በፊት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነበረብዎት?
- እርስዎ እና ባለቤትዎ ስለ ልጅ(ጆች) አደራ ተስማምታችኋል?
- እርስዎ እና ባለቤትዎ (የጋራ የልጅ አደራ ተቀባይነት ቢኖራችሁ) ሁለታችሁም ምቹ እና ተገቢ ነን ብላችሁ ትስማማላችሁ? እርስዎ እና ባለቤትዎ (የጋራ የልጅ አደራ ተቀባይነት ባይሰጣችሁ) አደራ ተቀባይ ምቹ እና ተገቢ ነው/ናት ብላችሁ ትስማማላችሁ?
- እንደስምምነታችሁ ሁኔታ፣ ዳኛው በተጨማሪ የሚቀጥለውን ሊጠይቋችሁ ይችላሉ፡ እርስዎ እና ባለቤትዎ የልጅ ጉብኝትን በተመለከተ ስምምነት አድርጋችኋል?
- የልጅ ድጋፍ ስምምነትን በተመለክተ ዳኛው በተጨማሪ የሚቀጥለውን ይጠይቋችሁ ይሆናል፣ እርስዎ እና ባለቤትዎ የልጅ ድጋፍ ስምምነት አድርጋችኋል? ሰለ ዲ.ሲ. የልጅ ድጋፍ መመሪያ ታውቃላችሁ? የእርስዎ እና የባለቤትዎን የቀጣሪዎች ስሞች እና አድራሻዎች፣ የስልክ ቁጥሮች ምንድናቸው? የሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥራችሁ ስንት ናቸው? የወር ከታክስ በፊት ገቢያችሁ ስንት ነው? ለልጆቹ የጤና እንክብካቤ እና የልጅ እንክብካቤ ወጭያችሁ ስንት ነው?
- እርስዎ እና ባለቤትዎ ሳታቋርጡ ተለያይታችሁ አንድ ቤት ውስጥ ሳትኖሩ (የግብረ ስጋ ግንኙነት ሳይኖራችሁ) ለስንት ጊዜ ቆይታችኋል?
- ከስድስት ወሮች በላይ ግን ከአንድ ዓመት በታች ተለያይታችሁ ከኖራችሁ ዳኛው የሚቀጥለውን ሊጠይቋችሁ ይችላሉ፣ እርስዎ እና ባለቤትዎ በጋራ እና በፈቃደኝነት አንድ ቤት ውስጥ ሳትኖሩ ተለያይታችሁ ለስድስት ወሮች ኖራችኋል?
- ዛሬ ውሳኔ መሰጠት ያለባቸው የግል እና የንብረት መብቶች (እንደ ቤት፣ መኪና፣ ጡረታ፣ እዳዎች) አሉ?
- በቀድሞው ስምዎ እንዲጠሩ (ሲወለዱ የተሰጠዎት ስም) ይጠይቃሉ?
- መልስዎ አዎንታዊ ከሆነ የጠየቁበት ምክንያት ሀጋዊ ላልሆነ ወይም የማጭበርበር ምክንያቶች ነው?
REMEMBER TO…
- በሥነ ሥርዓት ከሆነ ያገቡት በህግ የተረጋገጠ የጋብቻ ሰርትፊኬት ያምጡ፣
- በስምምነት የተፈፀመ ጋብቻ ከሆነ ሌሎች ማረጋገጫዎች (የእርስዎ ምስክርነት አንድ ማረጋገጫ ነው) ያምጡ፣
- የዲ.ሲ ተቀማጭ ካልሆኑ እና የባለቤትዎን የዲ.ሲ. ተቀማጭነት ማመልከቻውን ለማስገባት ከተጠቀሙበት፣ ባለቤትዎን ይዘው ይምጡ ወይም የባለቤትዎን የዲ.ሲ ነዋሪነት የሚያሳይ ሌላ ማስረጃ ያምጡ፡፡
- በጊዜ ይድረሱ (አንዳንድ ጊዜ ፍርድ ቤት ለመግባት ፍተሻው ጊዜ ይወስዳል)፣ በተጨማሪም ዳኛው እርስዎ ከመጠራትዎ በፊት የሌሎች ጉዳይ መጨረስ ስለሚኖርበት ለተወሰነ ጊዜ ለመቆየት ይዘጋጁ።
- ፍርድ ቤት እንደደረሱ ፀኃፊውን ያነጋግሩ (ፀኃፊው ከዳኛው አጠገብ ክፍሉ ውስጥ ፊት ለፊት ይቀመጣል)።
የ D.C. Bar Pro Bonoፕሮግራም አጠቃላይ መረጃዎች ብቻ ይሰጣል። ይህ የህግ ምክር አይደለም። የህግ ምክር ማግኘት የሚችሉት ከጠበቃ ብቻ ነው። ለተወሰነ ጉዳይ የህግ ምክር ከፈለጉ ጠበቃ ያማክሩ። ወቅታዊ የሆኑ የህግ ትምህርታዊ ሰነዶችን ለማስቀመጥ የተቻለንን ጥረት እናደርጋለን። ሆኖም ህጎች በየጊዜው ይለወጣሉ። ሰለዚህ፣ የ D.C. Bar Pro Bono ፕሮግራም የነዚህን መረጃዎች ትክክለኛነነት ሊያረጋግጥ አይችልም።